ስጀምር
ለተመለጠ አማርኛዬ ይቅርታ! ለቡዝንናቸው፣ ለእርግዝናቸው፣ ለውስለታቸው፣ ለውሽማነታቸውና ለሴተኛ አዳሪነታቸው
ሁነኛ አነሳሽ ምክንያት ከሚባሉት ተርታ ቀዳሚው ሚና የኛ የወንዶች ብልሹ ባህሪ እንደሆነ አምናለሁ።
አንዲት
ሴት ራሱዋን የመጠበቅ ሀላፊነት እንዳለባት ስለምዘነጋ ሳይሆን ዛቻችን፣ ውትወታችን፣ ዱላችን፣ አንፈልግም ያሉንን ሴቶች ለማንበርከክ ያለን ትምክህት እና ለዚህ ድርጊት ማስፈጸምያነት የምናውለው ገንዘብ በሴቶቻችን ውሳኔ ላይ ከፍ ያለ ድርሻ እንዳለው ስለማምን ነው። ጎበዝ ለአንድ አዳር ወሲብ እኮ ከ500-1000
እየከፈልን ነው ይህን የምናደርገው ሚስቶቻችንን ቤት የዶለትንና የልጆቻችንን የትምህርት ቁሳቁስ ያላሙዋላን አባቶች ስንሆን እንዴት
እንደሚጎመዝዝ ለናንተ ልተወው።
በሚገርም ሁኔታ ከፓንታቸው ስር ለመዋል ያለን ፍላጎት በአንዳች ሁኔታ ሃላፊነት የሚያስከትል ሲሆን አበድኩልሽ ያልናትን እና ወትውተን ያለፍላጎቱዋ ሁሉ የፍትወታችን ቅርጫ ያደርግናትን ሴት የራስሽ ጉዳይ ለማለት ምንም ያክል ግዜ አይወስድብንም።
ባለ
ትዳር እንደሆኑ እያወቅን ልናወስልታቸው መረብ የምንጥልባቸው ሴቶች፤ ጉዋደኛ እንደላቸው እያወቅን የሴስኝነታችን እቃ ልናደርጋቸው
የምንለክፋቸው፤ በለጋ እድሜያቸው ደብተራቸውን አንብበው ሳይጠግቡ የወሲብ ሱሳችን ሜኑ አካል የምናደርጋቸው ሴቶች ቁጥር ቀላል አደለም።
የሚገርመው
ደግሞ ውትውት አድርገን ሳይፈልጉ ተንኩሰን ጎትተን ስመን አስገድደን ደፍረን ስናበቃ፤ ያን ሁሉ ርካሽ ተግባራችንን
ዘንግተን “ሸርሙጣ፣ ባለጌ፣ ስድ፣ ዋልጌ፣ ሴሰኛ” የሚሉ ቅጽሎችን
ለነዚያው ሴቶች ስንጠቀም ትንሽ እፍረት አይሰማንም። ያንን ገፋፊና አሸርሙዋጭ ሚናችንን እንዴት እንደምንዘነጋው አይገባኝም። ቢያንስ
የነሱ እዳ እንዳለብን ማወቅ አልፈጠረብንም።
የምሽቱና
የሌቱ ቅዝቃዜ አጥነታቸውን እየሰበራቸው ያስደቀልናቸውን ሊያሳድጉ ያበላሸንባቸውን ህይወት ሊያስተካክሉ በልተው እና ለብሰው መኖርን
ሽተው በቀደድንላቸው ወሲብ ንግድ ውስጥ የሚኖሩ ስንቶቹ እንደሆኑ እናውቃለን!
ሽንት
የሸናን ያክል ዘር አቀብለናቸው የወር አበባዬ ቀረብኝ ሲሉን በዚያው የምንቀር ሽቅርቅሮች ሌላ ባለእዳ የምንፈልግ ሴሰኞች በመሆናችን
ባለእዳ መሆናችንን መዘንጋት የለብንም።
መርጨት
እንጂ ተቀብሎ ሰው መፍጠር የሚችል ተፈጥሮ ስለሌን ብቻ ያላጋጠመንን ችግር ልክ በጥንቁቅነታችን ያገኘነው ይመስል እርግዝናው ፓንቱዋን
ስታወልቅ ትዝ አይላትም ነበር እያልን ማሽሙዋጠጥ ያምረናል። ኮንዶም እያለ ስንት የጥንቃቄ መንገድ እያለ ምን ነካት እንላለን።
ባክህ ላረግዝ የምችልበት ቀን ነው ኮንዶም አድርግ ስንባል እሺ በጀ ብለን የምንተባበር ይመስል።
እየሸኑ
ዞር ማለትማ የነሱም ተፈጥሮ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ከኛ ባላነሱ ነበር። እናም ወንዶች የምር ለተሻለ ኑሮ ጥሩ ተማሪ መሆን ያለባቸውን
ልጆች ህይወት ላለማበላሸት፤ ለብዙ ትዳር መፍረስ ምክንያት ላለመሆን፤ ለበርካታ ጉዋደኛሞች መለያየት ምክንያት የሆነውን ሴሰኝነታችንን
ልጉዋም ብናኖርለት ጥሩ ነው።
ለፈረሰው ቤተሰብ፣ ጎዳና ለወጣች ወጣት፣ ለተለያዩ ፍቅረኛሞች፣ በዚህ ሁሉ ምክንያት ለሚከሰተው ማህበራዊና የጤና ችግር ድርሻ እንዳለብን
እንወቅ። ከሁሉም በላይ ግን ይህንን አሸርሙዋጭ አፍራሽ እና የሚያሴስን
ሚናችንን እንቀይረው።
ስንቶቹ
እህቶቻችን ናቸው የኛን ዲቃሎች የሚያሳደጉት፤ ስንቶቹ ሴቶች ናቸው ለጎዳና የተዳረጉት፤ ስንቶቹ ሴቶች ናቸው ዳግም ማፍቀር የማይችል
የተሰበረ ልቡና እሹሩሩ የሚሉት፤ ይህም ሁሉ ሆኖ የሴቶቹም ሚና ለዚሁ ሁሉ መፈጠር ቀላል እንዳልሆነ እረዳለሁ።
ወንዶች
ለብዙው የሴቶቻችን ችግሮች ትልቅ ሚና አለንና ቢያንስ ወንዶቹ የኛን ድርሻ እንወጣ!!! አቤት
የወሲብ ወጌሻ ቢኖርና ይህን ስብራታችንን ቢጠግንልን እንዴት ጥሩ ነበር!?
ለሴሰኝነታችን
እንዴት ለጉዋም እናኑረለት? እንወያይ ጎበዝ!!!
No comments:
Post a Comment