አሸናፊነትን ሰበብ አይረታውም
ሰበብ ሽንፈትን በጸጋ ማጣጣም የማይችሉ ግለሰቦች ለህሊናቸው ማሞኛነት የሚጠቀሙበት ማደንዘዣ
እንጂ ድርጊቶች ላለመሳካታቸው የሚቀርብ አሳማኝ ምክንያት ወይም መነሻ አደለም$ አሸናፊነት
እኮ ያው በሰበብነት የቀረበውን አስቸጋሪም ነገር መሻገር መቻልና ያሰቡበት መድረስ እንጂ ሌላ ምንም አደለም$ ይቆየን$
አሸናፊነት ያለሙትን ማሳካት እመረጡበት መድረስ መቻል ነው$ አሸናፊነት እንደ ኳስ ይነጥራል እንጂ እንደ ረጠበ ስፖንጅ እመሬት አይጠፈጠፍም$ አሸናፊ ልምድ በሚወጣም በሚወርድም እርግጫ አይረበሽም$ በቁምነገሩ በራሱ ህይወት ሂደት ሌሎች ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ሚና እንደሌለው ብቻ ሳይሆን ወሳኙን ሚናውን የሚጫወተው ራሱ ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል$
አሸናፊ ልምድ ለውድቀቶቹ ሰበብ አይቆጥርም ራሱ እንጂ ሌሎች ሰበቦች ለውድቀቱ መሰረታዊ ፋይዳ እንደሌላቸው ስለሚረዳ$ ሰው ልምድን እንደሚመስል ጠንቅቆ ያውቃል$ ሁዋኝ እንጂ ተደራጊና ተሰሪም እንዳልሆነ አይስትም$ ይሄን ቢስት እንኳ ሀቁ እንደማይቀየር ያውቀዋል$
ህይወት ምርጫ እንደሆነና ያን ምርጫ የማካሄድ ጉዳይ የራሱ ስለመሆኑ እርግጠኛ ነው$ የተሳሳተ ምርጫ በማካሄድ ወይም የመረጠውን ምርጫ በአግባቡ ባለመተግበሩ የሚመጡበትንም ጣጣዎች በጸጋ ዋጥ ያደርጋል እንጂ እነ እገሌ ይህን አድርገው ባይሆን ኖሮ ይሄ ባልሆነ ነበር የሚል ሰበብ አያውቀውም$ እነ እገሌ የማይገባ ነገር እያደረጉም ቢሆን የራሱን ከባቢና ምርጫ የሚያበላሹበትን ሁኔታዎች መቆጣጠር የሱ እንጂ የማንም ሀላፊነት እንዳልሆነ አሳምሮ ያውቃልና$
ሰው አቅሙ የሚችለውን ሁሉ ከሞከረና አቅሙ አሁን ያልደረሰበትንና ለስራው አስፈላጊ የሆነ ብቃት ያለማቋረጥ እስከገነባ ድረስ ሽንፈትን እንደገዛ ራሱ ሽንፈት ለመቀበል አይቸገርም$ ሽንፈትን መቀበል የሚያስፈልገው ትክክለኛውን የችግሩን ምንጭ ማከም አስፈላጊ በመሆኑ
ነው$ ችግሩ እውስጥ ሆኖ ሳለ በተደጋጋሚና በቸልተኝነት ችግሩን ውጫዊ ማድረግ ለተወሰነ ግዜ
ጫናውን ለሌሎች ለማጋራትና ራስን ተጠያቂ ላለማድረግ ያንደፋድፍ ካልሆነ በቀር ፋይዳ ቢስ ነው$
ሰላምነኝ እረ አልታመምኩም እያሉን በሽታ ገዘግዞ እንደሚገላቸው ድብብቆሽ ተጫዋቾች የራሳችንን
ችግሮች በመካድ ለሌሎች እጥረቶችን እያጋቡ ለመኖር መሞከር አደገኛ ነው$ እንዲህ
ያለው ክፉ ባህሪ ሳይደነድን በግዜ ካልታረመ ምነው እናቴ ሳንቲሞቹን ሳነሳ በከለከልሺኝ እንዳለው ሌብነት ሱስ ሆኖ ለውድቀት እንደዳረገው
ግለሰብ መሆን ይከተላል$
አሸናፊዎች የተመቸ ሁኔታ ከሌለ ሁኔታውን በማመቻቸት አስፈላጊ ቁሳቁሶች ካልተሟሉ በማሟላት
ደንቃራ በየመንገዱ ከተኮለኮለ ያን በማጥራት የሚመኙትን ነገና የሚሹትን ጉዳይ ከማሳካት ወደኋላ አያውቁም$ ይሄ ማለት ሁሉን ጉዳይ እዚያውና ወዲያው ካልፈታሁ ይላሉ ማለት አደለም፡፡ ይልቁንም
ከነሱ የሚጠበቀውን እያሟሉ የሚወስደውን ግዜ ወስደው ምርጫቸውን ለማሳካት ሳያሰልሱ ይሰራሉ$
ይሄ ማለት ለጉዳዩች ለግለሰቦችና ማህበረሰቦች የተመረጡ አላማዎች መክሸፍ ከነሱ ውጭ የሆኑ
ውጫዊ ምክንያቶች የሉም ማለት አደለም$ አሸናፊ ግለሰቦች አሸናፊ ማህበረሰቦች ያንን የመሳሰሉ እንቅፋቶችን በመለኝነት ተሻግረው
ነው ህልማቸውን የሚያሳኩት የሚለውን ተፈጥሯዊ ሀቅ ለማመላከት ነው$
አሸናፊነታቸውን በተሟላ ካፒቴንነት ይመሩታል፡፡ ለእድል የሚተው ነገር የለም፡፡ እድል
ካለች የምትቀርጸው እነሱ መገመት ማቀድ ያልቻሉትንና በነሱ ቁጥጥር ስር ያልሆነ ነገር የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው$ ሰበብ በአሸናፊ ግለሰቦች ልምድ ቦታ የለውም$ በህሊናቸው ስለማይከሰት አደለም መርጠው ትተውት እንጂ$
No comments:
Post a Comment