Tuesday, February 26, 2013

ችግር ካለ እድገት የለም!


ዘርይሁን ካሳ

"በዝናብ እጥረት የተነሳ ዛሬም የምግብ እህል እጥረት የሚያጋጥማቸው ቦታዎች ቀላል አደሉም  ትልቅ ችግር ነው አገራችን በርካታ መንገድ የሌለው አካባቢ አላት ይህ ችግር ነው በቅርብ የጤና ጣብያ የሌላቸው በርካታ ቦታዎች አሉ ይሄም ችግር ነው ቀላል የማይባል የትምህርት ቁሳቁስና የጥራት ችግር አለ ፍትሀዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች በፍርድ ቤትም በሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት ይስተዋላሉ የችግሩ ዝርዝር ይቀጥላል።"

"ይሄ ሁሉ ችግር ባለበት ታዲያ እቺ አገር አድጋለች ሲሉ አያፍሩም! ኢቲቪ ነው ደግሞ የባሰበት መንገድ ተሰራ ምርታማነት ጨመረ ጤና ጣቢያ ተመረቀ እያለ ሌላ አገር ያለን ይመስል የሚዋሸን።እንደ ኢቲቪ ዘገባ ቢሆን ይሄ አገር የት በደረሰ!"

ይሄ አስተሳሰብ እድገት አለ የሚባለው ሁሉም መንገድ ተሰርቶ ሲያልቅ ምንም የምግብ እህል እጥረት ያልተከሰተ ማንኛውም የጤና እክል የተፈታ እንደሆነ ያመላክታል በየትኛውም አለም ክፍል እያደጉ ያሉ አገሮች ወይም የበለጸጉ የሚባሉ አገሮች ችግሮቻቸውን ፈተው የጨረሱ አደሉም።ሊሆኑም አይችሉም!

ይልቅም ለምተዋል የሚባሉት አገሮች ትልቁ ልማት ችግር መፍታት የሚያስችል ግለሰባዊ እና ተቋማዊ ብቃት መፍጠራቸው ነው

እንዲህ ያለውን ችግር የመፍታት አቅም በተከታታይ ሳይንሳዊ ምርምርና በማያቋርጥ ቀጣይነት እያላቁት መሄዳቸው ነው።ይህን የመሰለውን ችግር የመፍታት አቅማቸውን ደረጃ በደረጃ ችግሮቻቸውን እየፈቱበት የሚሄዱ በመሆኑ በርካታ የስራ እድል መፍጠር ስኬታማ ተቋሞችና ምርቶች የሚፈልቁበት አዙሪት መፍጠር ችለዋል።

በማንኛውም አገር ትልቁ ቁምነገር ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ፈጠራዎች በማያባራ አዙሪት በላቁ ህሊናዎች እና የተቡ ግለሰቦች ተቋማዊ ቅርጽ ይዘው እየተመረቱ መሄዳቸው ነው ሌላው ጉዳይ ችግር በመፍታት ሂደት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቆሶች ወይም ቱልስ ዲዛይን ማድረግና ማምረት መቻል በዚህ የችግር አፈታት ሂደትና እድገት ውስጥ ቋሚ ገጽታዎች እና ልማታዊ አቅሞች እየሆኑ ይሄዳሉ ማለት ነው

አደግን ለማለት ችግር ጠፋ መባልን የምንመኝ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ሁኔታ በወዲያኛው አለም ካልሆነ እዚህ አናገኘውም ሆኖም አያውቅ ወደፊትም አይሆንም ችግር ሲጠፋ ስራ ይጠፋል በቀላሉ ችግር በሌለበት አገር መንግስት አያስፈልግም

ኢቲቪ አልዋሸም አገራችን እያደገች ነው@ እዚህ አገር ችግሮች አሉ የሚሉ ሰዎችም አልዋሹም አዎ በርካታ ችግሮች አሉ@ ይሄ ማለት ግን ችግሮች እየተፈቱ አደለም ማለት አይሆንም ችግሮች እየተፈቱ ከሆነ ደግሞ በተፈቱበት ልክ እድገት አለ ማለት ነው

መንገድ እየተሰራ ነው ማለት ሁሉም ቦታ መንገድ አለ ማለት አደለም@ ጤና ጣብያ ተገነባ ማለት የጤና እክሎች የሉም ማለት አደለም@ የትምህርት ሽፍናንና መሰረተ ልማት ተሳስፋቷል ማለት የጥራት ችግር የለም በሽፋንም ረገድ ቢሆን ገና የሚሰራበት ነገር የለም ማለት አደለም@ የእህል እጥረት አለ ማለት ምርታማነት የጨመረባቸው አካባቢዎች የሉም ማለት አደለም

ሲደመደም አድገናል ለማለት ምንም ችግር የለም መባል የለበትም! አለማደጋችንንም ለማሳየት ችግር መጠቆምም በቂ አደለም!

No comments:

Post a Comment