ከ60 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር በላይ ውሀ የምትሰጥ አገር ለም አፈሩ እየታጠበ እየሄደበት ያን በብሶትነት የማያነሳ ህዝብ
እውን የሚከፈለው ይሄን የመሰለ ትእቢትና ዛቻ ይሆን
አንዲት ጠብታ ውሀ ቢነካብን ደማችንን አፍሰን ደሙን እናፈስለታለን በአሸባሪና በታጣቂ እናጋየዋለን ይሄ ሁሉ ካልሰራ
ደግሞ እንወረዋለን የሚባለው ህዝብ
ግብጽ ውሀ መጠቀሟ ሳያንስ ሀገሩን በየጥጋጥጉ ሰላም ለመንሳት በሶማሌ ይሁን በኤርትራ በሱዳን በኩል ለመፍጠር የምትሞክረውን የማሸበር የማስታጠቅ ስራ የሚዘነጋ አደለም
ግብጽ ውሀ መጠቀሟ ሳያንስ ሀገሩን በየጥጋጥጉ ሰላም ለመንሳት በሶማሌ ይሁን በኤርትራ በሱዳን በኩል ለመፍጠር የምትሞክረውን የማሸበር የማስታጠቅ ስራ የሚዘነጋ አደለም
ያም ሆኖ ግን የሆዱን በሆዱ ይዞ በሰላምና በመቻቻል ውሀውን መጠቀም የሚሻ ቀና አገር ቀና ህዝብ
ዛሬም የግብጾቹ ችግር የሚገባን ቢሆንም ውሀውን የመጠቀም መብታቸውን የምናከብር ቢሆንም እንዲህ ያለውን አዋራጅ እና
የረከሰ የፖለቲካ ጨዋታቸውን ግን ይቅርታ አናደርግለትም
ጥርሳችንን ነክስን የተከፈለው ዋጋ ተከፍሎ ግድቡ በማንኛውም አማራጭ መጠናቀቅ እንዳለበት የምናምነው እንዲህ ያለውን
ስግብግብና ውለታቢስ የፖለቲከኞቻቸውን ቁመራ ስንረዳ ነው
በድርቅ ምክንያት ህዝብ ሲረግፍባት የነበረች አገር ውሀዋ ግብጽ ተሻግሮ የሚያበረክተውን የጥጥ ምርት የሚያንቀሳቅሰውን
ኢንደስትሪ የመሰረታቸውን ከተሞች ያለማቸውን በርካታ ማሳዎች ስለማንረዳ አደለም
የለመደብን በመቻቻል በመካፈል መንፈስ ተፈጥሮን የመጋራት እምነት ይዞን እንጂ ህዝባችን ጠላት የማይረታው ሁሌም ጦርነት
የሚገጥመው እንዲህ በጥጋብ ተነፋፍተው ከሚመጡ ቆማሪዎች ጋር በመሆኑና በጥልቅ ምሬት ሊረታው የሚገባበት ጦርነት በመሆናቸው
ነው
ግብጽም ብትሞክር ያኔ እንደሆነው ዛሬም ያለወሬ ነጋሪ እንደሚቀሩ እነሱም አያጡትም ሰውየው በህይወት እያለም አስታውሷቸዋል
መለስ በመሄዱ ረስውት ከሆነም እኛ እናስታውሳቸዋለን ጀግኖቹ ቢሞቱም ጀግና የምትፈጥረው ሀገር ዛሬም ቀና እንዳለች አለች እንላቸዋለን
ይሄ ጠብታ ውሀ በጠብታ ደማችን እንጠብቃለን የሚለው ተረክ የትም እንደማያደርስ ልናስታውሳችሁ እንወዳለን ጦርነት በርካታ
ወንድሞቻችንን የነጠቀን በመሆኑ አስከፊ ውጤቱን እናውቃለንና
እሱው አማራጭ ሆኗችሁ ከመረጣችሁትም ሰትየዋ እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር የማይሰጥ ዜጋ የለም እንዳለችው ለኢጣሊያ
ወራሪ ሀይል የጠገቡቱ የግብጽ ፖለቲከኞችም የሚመጥናቸውን ውርደት ተከናንበው እንደሚመለሱ እናበስራቸዋለን
እነሱ ጠብ የሚያደርጉት ደም እዚህ አገር የሌለ ከሆነ ያዩታል ለማንኛውም ግን እኛ ለሰላማዊ መፍትሄ ሁሌም ዋጋ ስለምንሰጥ
መወያየቱን እንዲመርጡ እንመክራቸዋለን
መፍትሄው ድርድር ነው በጦርነት መፍትሄ ለሚሻም በመረጠው መንገድ አስተምሮ የመመለስ ልምድ ስላለን የፎከሩበትን ደማችንን
አፍሰን እንደሚያፈሱት ከነገሩን ደም በከበረ መስዋእትነት ፍታዊ ድርሻችንን እናስከብራለን
ኢትዮዽያ ለዘላለም ትኑር
No comments:
Post a Comment