===========================================
እነዚህ
ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ የጎላ ድርሻ ያላቸው ናቸው ማለት ይችላል። ልዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ፓርቲዎቹ አንድ ነገር
በወሳኝነት ያመሳስላቸዋል - በወሳኝነት በአማራ የፖለቲካ ኢሊቶች የሚመሩ መሆናቸው። ያ ሆኖ ሲያበቃ ግን ፓርቲዎቹ ከብአዴን ጋር
መሰረታዊ የሚባል ልዩነትም ያላቸው መሆኑ አይሳትም።
በርግጥ
መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ አንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ይሄ ነው የሚባል የጎላ የፖሊሲ እና የፕሮግራም ልዩነት ያላቸው አደሉም። ይልቅ በተጠቀሱት
የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚታየው ልዩነት የግለሰቦችን ቅሬታ እና ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው። ፌደራላዊ ስርአቱን፣ የብሄር ብሄረሰቦችን
እኩልነት እና ሀገራዊ አንድነትን በተመለከተ የሚያቀነቅኑት አቋም አንድና ያው ነው። መንግስታዊ ባህሪው ምን መሆን አለበት በሚሉና
መሬትን እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በተመለከተ የሚያቀነቅኑት አቋምም ተመሳሳይ ነው።
ብዙ
ግዜ እነዚህ አማራዎች የሚበዙባቸው ቀኝ ፖለቲከኞች የቀድሞውን ስርአት እና የአማራን የበላይነት ለመመለስ ይሰራሉ በሚል የሚወነጀሉበት
በሌላ ገጹ ደግሞ ብአዴን/ኢህአዴግ ደግሞ የህወሃት ጥገኛ ተደርጎ የሚሳልበት ክስ ይሄ ጽሁፍ ከግምት
የሚያስገባቸው ጉዳዩች ናቸው። ስለሆነም በጹሁፌ ማየት የምፈልገው
ቁምነገር እነዚህ አማራ ኤሊቶች የሚመሯቸው ፓርቲዎች በፌደራላዊ ስርአቱ እና በአንድነት/መገንጠል ጉዳይ ላይ ያላቸውን ልዩነት እና
እነዚህ ፓርቲዎች ያላቸው አቋም በሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አባሎቻቸው ላይ ያለውን ተጽእኖ ነው።
ፌደራላዊ ስርአቱ
==================================================
ፌደራላዊ
ስርዓቱን በተመለከተ መኢአድ ኢዴፓና አንድነት ያላቸው አቋም ህዝቦች እንደ አስፈላጊነቱ ቋንቋቸውን እና ባህላቸውን የሚጠቀሙ መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ ለአስተዳደር እንዲመች ተደርጎ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥን ከግምት ባስገባ መልኩ መከናወን አለበት የሚል ነው። በብሄረሰብ
ላይ የተመሰረተ ከሆነ ይላሉ እነዚህ ቡድኖች ሀገራዊ አንድነቱ እና የህዝቡ ትስስር ይላላል። እንዲያውም ያ አይነቱ ፌደራሊዝም አንድነቱን
እየሸረሸረው ይሄዳል የሚል ስጋት ያነሳሉ። እነዚህን ቡድኖች ብሄረሰባዊ ፌደራሊዝሙን የሚደግፉ እና ተገቢ ነው የሚሉ ሀይሎች የቀድሞውን
ስርዓት ለማምጣት የሚተጉ፥ በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ፌደራሊዝም ሰበብ ህዝቡን ከፋፍለው ድምጹን ከፍ አድርጎ ማሰማት እንዳይችል ለማድረግ
የሚሰሩ ናቸው የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። ኦነግን የመሳሰሉ ቡድኖች ደግሞ እነኚህ ሰዎች "የአያቶቻቸውን ስርዓት" ለማስቀጠል እና የህዝቦችን ትግል ለማዳከም እንጂ የህዝቦች መብት አሳስቧቸው አደለም
በሚል ይወነጅላሉ።
ብአዴን/ኢህአዴግ
የሚያቀርቡት አማራጭ ደግሞ አዎን ህዝቦች ብሄራዊ አንድነታቸውን ተከትለው ፌደራላዊ መንግስት ማቋቋም ይችላሉ። በሀገራችን ታሪክ
ቀድመው የነበሩ ስርአቶች ሆን ብለውም ይሁን ባለማወቅ ያደረሷቸው ጭቆናዎች ፍትህ የማጣት የመበዝበዝ ብቻ ሳይሆን ብሄረሰባዊ ጭቆናም
የነበረባቸው ናቸው ብለው ያምናሉ። በመሆኑም ብሄሮች ማንነታቸው ለጥቅምም ለበደለም ታርጋ የማይሆንበት ሁኔታ ለመፍጠር መስራት አለብን
ይላሉ። ለአንድነት ምክንያት የሚሆነን እና አንድነቱን የሚያቋቁሙት መሰረታዊ ጉዳዩች ግን የፌደራል ስርአቱ አከላለል ሳይሆን ለአንድነት
መነሻ የሚሆኑን ጉዳዩች ናቸው በማለትም ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። አንደኛ ህዝቦቿ በታሪክ
ሂደት ያፈሩት የጋራ ቅርስ እና መቻቻል ሁለተኛ ደግሞ ከጦርነት እና ከጸጥታ ስጋት ጸድቶ በማያውቀው ቀጠና ጥቅሞቻችንን በተሻለ
ለማስጠበቅ እና ደህንነታችንን ለመጠበቅ ከጠንካራ አንድነት የተሻለ አማራጭ የሌለን መሆኑ ነው። ስለሆነም ይላል ብአዴን/ኢህአዴግ
ህዝቦች አንድነቱን የሚመርጡት ባለንበት ቀጠና እና ባለን ታሪክ አንድነቱ የተሻለው እና የማያወላዳው አማራጭ በመሆኑ እንጂ እንዳንገነጣጠል
በሚል ስጋት ብሄሮች ወዲያና ወዲያ በክለላ ስለተሰፉ አደለም ይላል። ይሄን በወሳኝነት የሚቃወሙት ደግሞ መኢአድ አንድነት እና ኢዴፓን
የመሳሰሉ ፓርቲዎች ናቸው። ሰማያዊ ፓርቲም ከሰሞኑ ይሄንኑ ጎራ የተደባለቀ መሆኑ አይዘነጋም።