Wednesday, December 12, 2012

አቤቱ የሚሰሩና የሚለውጡ ጀግኖች ስጠን


                                                       በዘርይሁን ካሳ
ቴዎድሮስ ተወደደም ተጠላም ያመነበትን አሳምኖ ቡድን አደራጅቶ የመሰለውን ታሪክ ሰርቶ አልፍዋል የሗንስም እንዲሁ::

ምንይልክም በግዜው እምነቱን ሰብኮ ጦሩን አደራጅቶ ያመነበትን ሰርቶ አገርና ታሪክ ትቶልን ተሰናብቱዋል:: ትልቁ ነገር ዳር ቆሞ ሲቆዝም ወይም ሲቦጭቅ አልነበረም እምነቱን ሌሎችን አሳምኖ ጭምር ኖሮታል:: 
አንዱ ደማቅ ገድሉ የጥቁር ነጻነት ምልክት የሆነበት አድዋ ነው እማይወደዱ ታሪኮችም ይኖሩታል በቁምነገሩ ግን ዘመኑን እምነቱን ኖሮበታል::
ዳር ቆሞ ሲያላዝን በጁ የያዘውን አላባከነም አለያም ደግሞ ሰዎች የያዙትን ሲያጠቁር ግዜው አልረፈደበትም::

ሀይለስላሴም ታሪክ ያለውን ሊል ይችላል ይሉኝን ፈርተው ፍላጎታቸውን እና እምነታቸውን ሳይኖሩ የቀሩ አልነበረም:: የወደደም ወደደ የጠላም ጠላ አቁዋማቸው አገር መርቱዋል ምንም ይስሩ ትክክልም ይሁኑ አይሁኑ ሰርተዉታል::
የሳቸው አመራር ያላማራቸው ተማሪዎች ደግሞ ንጉስ ሆይ መንገዱ ለህዝባችን አይጠቅምም ብለው ታግለዋቸዋል::
ወታደሮቹም ያግኙትን አጋጣሚ ለበጎም ይሁን ለመጥፎ አላባከኑትም እሚያነሳት ያጣችውን የተማሪ አብዮት የፈጠራትን ለውጥ ቀልጠፍ ብለው በመነሳት አገር መርተዋልም ገለዋልም:: ቁምነገሩ ደፈር ብለው ሀላፊነት መውሰዳቸው ነው::

ለውጡ ያላረካው የተወሰነ ተማሪ ትግሉን ከትምህርት ቤት ወደ ደፈጣ ውግያ ቀይሮ ጫካ ገብቶበታል::
ያላሳመነውን ለውጥ በዳር ቁዋሚነት እንደማያሳካው ተገንዝቦ የሚያምንበትን ለውጥ ለማምጣት ህልሙን ትቶ ዲንጋይ ተንተርሶለታል:: መስዋእትነት የሚጥይቀውን ለውጥ በጫጫታ ለመመከት አልሞከረም ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ለይቶ ለአመታት ከፍሎታል::

ትግሉ ወጤት ካስገኝም በሁዋላ የድሮዎቹ ተማሪዎች አገር መርተዋል:: እየመሩም ነው:: እምነታቸውን እሚጋራም እማይጋራም አለ:: ያ ለውጥ የለውም:: ቁምነገሩ እምነታቸውን አላማቸውን ከመፈጸም ያልቦዘኑ መሆናቸው ነው::

ቁጥሩ አስማማም አላስማማም አገር እያደገ ነው:: እቺ አገር ግን የትላንቱን ችግር ብትሻገርም ዛሬም ችግሮች አሉባት መቼም ይኖራሉ::  ዳር ቁዋሚ አዝማሪዎች ግን ችግር አይፈቱም:: አገር አይቀይሩም:: ቀይረውም አያቁም::

ዛሬም አገር የምትሻው  ጨለማን የሚረግም ዳር ቁዋሚ አዝማሪ አደለም:: በገባውና ባመነበት ልክ እምነቱን የሚኖር ለለውጥ ዋጋ የሚከፍል እሚችለውን ታክል ደግሞ አስተዋጾ እሚያበረክት ጎበዝ ነው::
በርግጥ ሂትለርም መሪ ነው ማንዴላም ያው መሪ ነው:: ሙሶሊኒም ጋንድሂም ያው ስማቸው መሪ ነው:: በረከታችን ግን የማንዴላንና የጋንድሂን አይነት እንዲሆን ከመተለም እና ቁርጠኛ ከመሆን ጋር ሲሆን የበለጠ ህዝብ ይጠቅማል ቢያንስ ደግሞ አይጎዳም::

ከሁሉም ግን የከፋው ዳር ሆኖ ማጨብጨብ ነው:: ነጋ ጠባ ላይፈይድ ማንቦጫረቅ::

የቅርቡን እንኩዋ አብነት ብንወስድ ሰው እንዲወደውም እንዲጠላውም አደለም የሚውዱትን ያክል  የሚጠሉትም እንዳሉም ያውቃል ግን ለሀገሬ ይበጃል ያለውን  እስከህቅታው ድረስ አንድ ጎበዝ ኖሮታል::

ተወደደም ተጠላም ምጡቅ ስብእናው እና ብቃቱ ግን አነጋጋሪ አደለም መላውን አለምና አፍሪካን በተግባራዊ ፍልስፍናዎቹ ተጽእኖ አሳርፎባቸዋልና::

ቢያንስ ከማላዘን በሁሉም ጉዳይ ላይ ከሁሉም ጋር የሚግባባውን ያልተወለደውንና መቼም የማይወለደውን ጸአዳ መሪ ከመጠበቅ እምነታችንን እና ግቦቻችንን ባመንበት አማራጭና መንገድ እንኑረው::  የዘመኑ ባለምጡቅ ስብእና መለስ ዜናዊ ትቶልን ያለፈው አብነት ይኸው ነው::

መላእክትን አደለም ስህተት ሰርቱዋል ምርጥ ሰው ግን ነው አንጸባራቂ ድሎች ለኛና ለሀገራችን ትቶልን አለፉዋል::

አትፍራ ከፊሉ ያደንቅሀል ከፊሉ ይኮንንሀል እምነትከህን ግን በምልአት ኑረው ትርፉን ታሪክ ይተርከው::
ይቆየን:: 

No comments:

Post a Comment