ኢህአዴግ እጥረቶች እንዳሉበት በርካታ ወዳጆችና ተቃዋሚዎች ይናገራሉ! እውነት ነው:: አሸናፊ ጥንካሬውን ግን አያሳጡትም!!!
እጥረቶች እንዳሉበት እንረዳለን ችግሩ እነሱ ችግር የሚሉት ነው ወይስ ሌላ የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ የሰዎች ማህበር በመሆኑ እጥረቶች እንደሚኖሩበት ግልጽ ነውና::
ኢህአዴግን ወይም ሌላ የትኛውንም ፓርቲ የምንደግፈው ስህተት ሰለማይሰራ ሳይሆን በመሰረታዊነት ርእዮተ አለሙ ፍልስፍናዎቹ ፖሊሲዎቹ እና የሚከተላቸው የማስፈጸምያ ስትራቴጂዎች በርግጥም ችግሩን ይፈታሉ ብለን ያመን እንደሆነ ነው:: እየደገፍን ያለነውም ይህንኑ ስለምናምን ነው ማለት ነው::
በመሆኑም ፓርቲዎች መመዘን ያለባቸው አገራዊ ችግሮችን ጠንቅቆ መረዳት፣ መፍትሄዎቻቸውን መለየት፣ የሚፈጸሙበት ስትራቴጂ መተለም እና ያን በቁርጠኝነት መተግበር በመቻል አለመቻላቸው ነው:: ባለፉት 20 አመታት ኢህአዴግ በቅጡ ባልዳበረ ልማታዊ አቅም፣ በደካማ ፋይናንስ እና ከውጭም ከውስጥም ይካሄድ በነበረ የሰላ የርእዮተ አለም ተቃውሞ መሀከል በተለይ ባለፉት አስር አመታት አገሪቱ ያስመዘገበችው ውጤት በርግጥም ኢህአዴግ አገራዊ ችግሮቻችንን በተሳካ መንገድ መፍታት የሚችል ፓርቲ መሆኑን ያመላክታል::
አንዳንዴ አንዳንድ አስተያየቶች ሲሰጡ እንዴት ይህን አይነት ስህተት የሚሰራ ፓርቲ ትደግፋላችሁ የሚል አይነት አንድምታ አላቸው:: እስከሚገባኝ ድረስ አባላቱም ይሁኑ ደጋፊዎቹ ፓርቲው መፍትሄ ማስገኘት እና መምራት የሚችል መሆኑን አይተው እንጂ እጥረቶች የሌሉበት ስለሆነ ነው የሚል የዋህ እምነት የለኝም::
ያም ሆኖ በባህሪው የሰዎች ማህበር በመሆኑ ከሚታዩበት እጥረቶች ባለፈ ሲመዘን የህዝብ ወገንተኝነት የተላበሰ፣ ለህዝብ ጥቅም መስዋእትነት እየከፈለ የመጣ፣ ብቁ ፖሊሲዎች የቀረጸ እና በአግባቡ ፖሊሲዎቹን በመተግበር አንጸባራቂ ድሎችን ማጣጣም የቻለ ፓርቲ መሆኑን የሚገመግም የመፍትሄ ፓርቲ የለውጥ እና የውጤት አጋር መሆኑን መረዳት ይቻላል::
ህዝቡም ለፓርቲው ድጋፉን ሲሰጥ በየምርጫው ካርዱን ሲያበረክት እጥረት የሌለበትን ፓርቲ እየመረጠ አደለም:: ያም ሆኖ የላቀ ብቃትና የመሪነት ሚና ያለውን ፓርቲ እየመረጠ መሆኑን ግን ይገነዘባል:: በኢህአዴግ ደረጃ አገራዊ ችግሮቹን እና መፍትሄዎቹን ቀይሶ ያን መተግበር የሚችል አቅም አጎልብቶ የሚገኝ እዚህ ግባ የሚባል ፓርቲ እንደሌለም ይረዳል::
ፓርቲው ላለፉት ሀያ አመታት የሰራቸው ዝርዝር ስራዎች አደሉም የሚያጓጉት:: ይሉቁንም በሚቀጥሉት አስርት አመታት እንደሚመዘገቡ የሚጠበቁት ዉጤቶች እንጂ:: እኚህ ደግሞ በወጉ እና በላቀ ጥንቃቄ ከተቀመሩት ፖሊሲዎችና ባለፉት አስር አመታት ከታዩት አንጸባራቂ ድሎች የሚመነጩ ናቸው:: በትንሹ እንኩዋ ባለፉት ዘጠኝ አመታት ባለ 10.6 በመቶ እድግት አገራችን ማስመዝገቡዋ በአለማቀፍ ተቁዋማት መታመኑን መጥቀስ ይቻላል::
አገሪቱ አህጉራዊና አለማቀፋዊ ተሰሚነቱዋ እንዲያድግና የፖሊሲ ነጻነቱዋን እንድታሰጠብቅ የተደረገው ጥረት አይነኬዎቹ ለምሳሌ የአባይ ግድብ ጉዳይ መቁዋጫ የተበጀለት መሆኑ ኢህአዴግ እንደ ፓርቲ ይቻላልን በህዝቡ ውስጥ በማስረጽ የላቀ የሀብት ፈጠራ መንፈስን ያቀጣጠለ ድርጅት መሆኑን ያስመሰክራል::
የእጥረቶችን መኖር ስለሚገነዘብም ነው ፓርቲው በመደበኛነት ግምገማ የሚያካሂደው:: አንዱ ጥንካሬው እንደውም እትረቶቹን በራስ ተነሳሽነት ገምግሞ የእርምት ርምጃ የሚወስድ መሆኑ ነው::
ገለጻው ኢህአዴግ ለማደግ የሚደረገውን ጦርነት በአሸናፊነት እንደሚወጣው የሚያሳይ እንጂ በያንዳንዱ አውደ ውጊያ ሳይቆስል ለድል የበቃ መሆኑን አያትትም:: በቁምነገሩ ግን አሸናፊ ፓርቲ ነው:: ቁስለትና እጥረቶች ከትልቅ አገራዊ ተጋድሎዎቹ ዘወር እንደማያደርጉት በላቀ ቁርጠኝነትና ውጤት ያስመሰከረ ነውና:: የልማትና የሰላም ተጋድሎዎቹ አይን የማይነቀልባቸው ተግባሮቹ መሆናቸውን በቃል ሳይሆን በተግባር አትሟቸዋልና ::
እናም ሲጠቃለል ኢህአዴግ የሚደገፈው እጥረቶች ስለሌሉት ሳይሆን የመፍትሄው መሪ የመፍትሄው ቁልፍ ክፍል በመሆኑና ለምንናፍቀው የልማት እና የእድገት ድል የላቀው አማራጭ በመሆኑ ነው::

No comments:
Post a Comment