በቁምነገሩ በየለቱ በሬ ወለደ ማለታቸው
የጀግነታቸው ሀውልት ሆኖ በየወቅቱ ሚዛኑን ያልጠበቀ ወቀሳቸው ለሀገራቸው የሚያበረክቱት ትልቅ ፋይዳ ሆኖ እነሱ እንጂ ሌላ ጀግና
እዚህ አገር እንደሌለ እንዳወጁ ይኖራሉ$ ቀሽም ቁምነገራቸው ነው$
ባላገሩ አፍ ያለውና ያወራ አደለም$ ባለጉዳዩ የወቀሰና የተቸው አደለም$
እውነትም እየተወራጨ ከሚያወራና ከሚያለቃቅስ ጋር ትሆናለች ማለት አደለም$ የኛ የከተሜዎች ጫጫታ ሲደራ አንዳንዴ ይሄ አገር የአርሶ
አደር አገር መሆኑ ይጠፋኛል$
እዚህ አገር የጠናው ችግር የትኛው ነው? ዋናው የሀገሬው እሮሮ የሀይ አትበሉን
የእንዳሻን እንሳደብ እንጻፍ እና እናጣጥል ዝንባሌና ተግባር ነው ወይስ የባላገሩ መሰረታዊ ጉዳዩች?
እኔ ጋዜጦቻችን መጽሄቶቻችን እና አብዛኛው ሚድያ ሲልም የተማረ የሚባለው
ኢትዩዽያዊ ሀገሩን ያውቃል ወይ የሚል ጥያቄ አለኝ$ እቺ አገር የገጠሬ አገር እቺ አገር የአርሶአደርና የአርብቶአደር አገር መሆኑዋን
በቅጡ እናውቃለን? እናም የገጠሬው ችግር እኛ ድዳችንን የምናለፋበት ወልካፋና ቀርፋፋ ጉዳይ
ስለመሆን አለመሆኑ አስበን እናውቃለን?
