አንዳንድ ሰዎች እውነት ይነገር ይሉናል ብዙም
ሳይርቁ ግን በሚሹት ጉዳይ ብቻ ካልሆነ በተቀረው ይክዱናል$
እውነት ነው መለስ ንጹሃ ባህሪ አደለም ያንም
የሚል እብድ የለም የላቀ የአመራር ብቃቱ ግን በምንም መልኩ አጠያያቂ
አይሆንም$
ለምሳሌ የአባይ ግድብ ጉዳይ ሲነሳ አንዳንድ ወዳጆቻችን
የለም ይሄ ፕሮፖጋንዳ ነው ታስቦበት የሆነ አደለም ይሉና የዚህን ጀግና አስተዋጾ ሊያሳንሱት ይሞክራሉ$ በርግጥ በቁምነገሩ ከዚህ ገለጻቸው ዋሾነታቸውን ካልሆነ በቀር የሚያሳብቅላቸው ሌላ ነገር
ያለ አይመስለኝም$
ለመሆኑ መለስ ዜናዊ ምን አስልቶ ነበር ከአስርት
አመታት በላይ የፈጀ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በናይል ኢኒሼቲቭ ዙርያ ሲያካሂድ የነበረው የአካባቢውን ሀገሮች አስተባብሮ ሲሰራ የነበረውና
በፍትሀዊ የውሀ ክፍፍል ዙርያ የቀጠናውን አገሮች የሚያስማማ ውል ለማሰር ውጤታማ ስራ የሰራውን ምርጥ የዲፕሎማሲ ስኬቶቹን የትኛው
ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ጥለን ነው አባይ ፕሮፖጋንዳ ነው ብለን ልንናገር የሚቃጣን$
በርግጥ ይህን የሚከራከሩ ግለሰቦች የዚህ ምጡቅ
ስብእና ቁመና በሞትም በኋላ እንደሚያስፈራቸው በቅጡ ያልታነጸች ፖለቲካዊ አተያያቸውን እንደሚንጣት እረዳለሁ$ ያም ሆኖ ግን እውነን እውነት ማለት እኮ ለራስ ነው$ ጎበዝ በትግል ሂደት ትልቁ ነገር ሊታመን የሚችል ስብእና እኮ ነው ማለቴ መለስ ጻድቅ
ነው ማለት ውሸት የሚሆነውን ያክል የመለስን የተራራ ያህል የገዘፉ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ስኬቶችም መካድ ያው ወሸት ነው ማለቴ ነው$
በምን ሂሳብ ነው ግብጾቹ ስለተራበሹና አመጹ ወደኛም
እንዳይጋባ በመስጋት ነው ተብሎ የሚወራው በርግጥም ይሄ ታታሪ መሪ ለህዝቡ ከምርጫው ማግስት የገባውን የላቁ ልማቶች የማሳካት አጀንዳ
እና በወንዙ ላይ ለአመታት የተደረጉ ድርድሮቹን ተከትሎ የሰራው ታሪክ በደማቅ የሚመዘግብለት ግዙፍ ስኬቱ ነው$
ሌላው የሚሰማው ደግሞ ኢህአዴግ መለሰን በማሞካሸት
ባዶ መቅረቱን እያወጀ ነው የሚለው ነው$ ይሄም ያው የዚህን ታላቅ መሪ ስብእና መደነቅ በመጥላት የሚናፈስ ጠማማ ወሬ ነው የሰራው
ከሆነ የተወራለት ምን ችግር አለው ሁለተኛ ደግሞ በአመዛኙ በሁሉም ስራዎች ላይ አሻራው አለ ማለት ሌሎቹ ብቃት የሌላቸው እቃዎች
ናቸው ማለት ነው ያለው ማነው$
እንደው ደርሰን ቋሚዎቹን ለማድነቅ የፈለግን በማስመሰል
የዚህን ትጉህ መሪ ስኬቶች ላለመስማት የምናደርገው ሌላው ጥረት ነው$
በየትኛውም ሚዛን በለስን እና ተከዜን በራሱ ወጪ
አቅዶ በራስ አቅም ግድብ መስራት እንደሚቻል ያሳየና ያን ልምድ ይዞ ወደላቀው ስራ የተሸጋገረን ልሂቅ ማጣጣል ለዚያውም አንጸባራቂ
ስኬቱን እያጣጣሉ የምር ይደብራል ማለቴ ዋሽቶ ከመቃወም በትክክልም ደካማ ጎኑን በመጥቀስ መርታት አይሻልም$
ለነገሩ ፖለቲካዊ ፍልስፍናዎቹ በአግባቡ የተቀመሩ
በመሆኑ ለመርታት አይመቹም እሱ የተለየ ፍጡር ስለሆነ ሳይሆን መርታት ያልተቻለው በርግጥም ፖለቲካዊ አስተምሮዎቹና ፖሊሲዎቹ በትክክል
የዚህችን አገር ችግሮች በአስተማማኝ ሁኔታ መፍታት የሚያሰችሉ በመሆኑ ነው$
ለነገሩ ለሀገሩ አስቦ የሚቃወም ሰው ሲገባው የሚቃወመውን
እና የሚያቀርበውን የተለየ አማራጭ እያጠራ ይሄዳል ያን እረዳለሁ$ የማይገባኝ በቃ እንዲያው ለመቃወም እንዲያው ለማጠልሸት በመፈለግ የሚዋትቱት ወዳጆቼ
ጥረትና ግዜ መባከኑ ነው ይሄ ጥረታቸው በርግጥም አገር በምትጠቀምበት ጉዳይ ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ ምንኛ አገር በጠቀመ ነበር$
ከተከዜ እስከ 200 ከበለስ እስከ 460 ከስካሁኖቹ
ጊቤዎች ከሁለት ሺ በላይ እና ከአባይ እስከ 6000 ሜጋ ዋት ሀይል ለማመንጨት የሰራ ሰው በስኬቱ ማጣጣል የጤና ነው ይሄ እኮ
ሲደመር የንፋስ ሀይሎችን ጨምረን ወደ ዘጠኝ ሺ ሜጋ ዋት እኮ ነው ጎበዝ$
በየትኛውም የአፍሪካ ሀገር ይቅርና በየትኛም አለማቀፍ
መስፈርት ቢታይ ይህ መሪ በርግጥም የውጤት ሰው ህዝቡን መውደዱን በቃሉ ሳይሆን በተግባር ያሳየ የስራ ጀግና ነው$ ቆራጥ መሪነቱን በጥይት እብሪት ሳይሆን በሚቆጠሩ የልማት ስኬቶቹ የከተበ የህዝብ ልጅ
የህዝብ ልጅነቱን ችግር አለ እያለ በመዘመር ሳይሆን ለባሰው ችግር ለወሳኞቹ ችግሮቻችን መፍትሄ እየቀመረ እየተገበረ ከተግባር እየተማረ
ስህተቱን በአደባባይ እየገመገመ ለሀገር እየነገረ ሀገርን ወደማይቀለበስ የእድገት አዙሪት ያስገባ ጀግና ነው$
ስኬቶቹን የምንቆጥረው ዛሬ ላይ ችግር እንዳይኖር
አድርጓል በሚል መንፈስ አደለም ሊሆንም አይችልም ስኬቶቹን የምንተርከው መፍትሄ ካበጀላቸው መሰረታዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎቻችን
አንጻር ነው እንዲህ ያለ ጀግና ስኬቶቹ ዛሬ ላይ የሚመዘኑ ብቻ አደለም የላቁ ዘመን ተሻጋሪ ስኬቶቹ ገና በመጪው ግዜ እየተተነተኑ
የሚገላለጡ ናቸው$
ይሄን የምንለው አፈር እንዲቀለው ወይም አንዳንድ
ወዳጆቻችን እንደሚሉት ይሄን ስላልን ሆዳችንን ልንሞላ ብለን አደለም ይሄን የምንለው የጀግኖቻችንን ስኬቶች በመካድ የሚገኝ ሀገራዊም
ግለሰባዊም ፋይዳ ስለለ እንዲያውም ይህን ከመሰሉ ትጉሀን የምንማራቸውን ውብ ልምዶች እንዳናጣ በማሰብ ነው$
እሱማ ጊዜውን በመረጠው አላማ ኖሮት ተሰናበተን
ቁምነገሩ ለቋሚዎቹ ነው$ የምር ቁምነገሩን ለማወቅ ከሆነ እየተወያየን ያለነው አዎን መለስ አባይን የደፈረ አዎን
መለስ አይቻልምን የደፈረ አዎን መለስ በውጭ ብድር ካልሆነ በቀር አይሞከርም የተባለውን የዘመናት ካቦ የበጠሰ ጀግና ነው አዎን
መለስ በምርጥ ተደራዳሪነቱና ንግግር አዋቂነቱ የአካባቢውን ሀገራት ለፍታዊ ውሀ ክፍፍል ያበቃ ጀግና ነው ያን ተከትሎም የተጋለትን
ሀገራዊ ኢላማውን አባይን ለጥቅም የማዋል አጀንዳ 6000 ሜጋ ዋት ከሚያመጨው የህዳሴ ግድባችን ያስጀመረው$
አዎን ባለ2000 ሜጋ ዋቶቹን ሌሎች የአባይ ግድቦች
ደግሞ ይሄን ስንጨርስ እኛ እንሰራቸዋለን ምሳሌህ ተማሪዎች አሉት አብዝተው አስፍተው ይተግብሩታል የምር የስካሁኑን ስኬት ያጣጣመ
አገር የቀሩ የድህነት ምሬቶቹን ለመቀልበስ ይተጋል አስተምሮህ ከኛ ጋር ይኖራል ላንተ ብለን ሳይሆን ነገን የተሻለ ለማድረግ አዎን
ያንተም አላማ መለስ ዜናዊ ደረትህ እንዲቀላና ሆድህ እንዲሞላ አልነበረም እና ይሄ የተጋህለት ህዝብ የተመኘውን እስኪያሳካ የሚተጉ
ጎበዞች እንዳሉ እናምናለን$
No comments:
Post a Comment