Monday, June 17, 2013

ተቃዋሚዎች የግብጽን የቤት ስራ እየሰሩላት ይሆን?-1

አንዳንድ ዜጎቻችን ግብጽ የሰጠችንን የቤት ስራ በአግባቡ እንድንፈጽም ይወተውታሉ$ ለግብጽ እጆቿ ሆነው ተልእኮ ለመፈጸም እያቅማሙ ያሉ እንዳሉ አያለሁ$ በኛ ይሁንባችሁ ግብጽን አንችላትም አርፈን እንቀመጥ ከሚሉን የመክሸፍ ፖለቲከኞች ጀምሮ የኢትዮዽያ ሰራዊት ግብጽን ከግምት ያስገባ ዝግጅት አላደረገም እስከሚሉን ድረስ ተረኩ አንድና ያው ነው$

ኢህአዴግ ለፖለቲካ ትርፍ እንዳይጠቀም ብሎ መፈክር ማስነገሩ እራሱ ለፖለቲካ መጠቀም መሆኑ ገሀድ ሆኖ ሳለ ለግብጽ የረጋ ያልረጋ መግለጫ ያልሰጠውን ኢህአዴግን ባልበሰለ ፖለቲካዊ ቁመናው አንድነት ሊመክረው መከጀሉን ሳይ ሳቅ ቢጤ ከጅሎኝ ነበር$ ምንም ያክል ልዩነት ቢኖር ይሄን አይነቱን የግብጽ ፖለቲከኞች አጉራ ዘለል ባህሪ ለመተቸት በቀጥታ መናገር እንጂ ነጥብ ለማስመዝገብ በማሰብ የአባይንና የግድቡን ጉዳይ በዚያ መልኩ አውገርግሮ ማቅረብ የወረደ የፖለቲካ ቁመና ማሳያ ነው$ ይበስላሉ ተብለው ከሚጠበቁ በወጉ ካልተደራጁ ፓርቲዎች በመስማቴ በርግጥ እምብዛም አልገረመኝም$

ያለበቂ ዲፕሎማሲና ውይይት ያልተጀመረ ግድብ?

Wednesday, June 12, 2013

ወርቅ ላበደረ ጠጠር- የአባይን ግድብ በግብጸቹ አይን 2

ከ60 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር በላይ ውሀ የምትሰጥ አገር ለም አፈሩ እየታጠበ እየሄደበት ያን በብሶትነት የማያነሳ ህዝብ እውን የሚከፈለው ይሄን የመሰለ ትእቢትና ዛቻ ይሆን

አንዲት ጠብታ ውሀ ቢነካብን ደማችንን አፍሰን ደሙን እናፈስለታለን በአሸባሪና በታጣቂ እናጋየዋለን ይሄ ሁሉ ካልሰራ ደግሞ እንወረዋለን የሚባለው ህዝብ 
ግብጽ ውሀ መጠቀሟ ሳያንስ ሀገሩን በየጥጋጥጉ ሰላም ለመንሳት በሶማሌ ይሁን በኤርትራ በሱዳን በኩል ለመፍጠር የምትሞክረውን የማሸበር የማስታጠቅ ስራ የሚዘነጋ አደለም

ያም ሆኖ ግን የሆዱን በሆዱ ይዞ በሰላምና በመቻቻል ውሀውን መጠቀም የሚሻ ቀና አገር ቀና ህዝብ

እውን ከወርቅ የሚቆጠር ውሀ ያጠጣ ህዝብ ግብጽ ሆንኩ ለምትለው ነገር ሁሉ የሚሆነውን ውሀ ያበረከተ ሀገር የሚከፈለው ወሮታ ማጋየት እና ጦርነት ነው

Friday, June 7, 2013

የአባይን ግድብ በግብጸቹ አይን 1

ግብጽና ናይል ናይልና ግብጽ አንድና ያው ናቸው እየተባለ ያደገ ህዝብ$ በዚህ ረገድ አደጋ የምትሆን ታሪካዊ ጠላት ኢትዮዽያ እንጂ ሌላ ማንም አደለም እየተባለ የኖረ ህዝብ ለማመን ቢያመነታ አይገርምም$ በውል መወያየት ጉዳዩን በወጉ ማሳየት ያለባቸውና እውነቱን የሚያውቁት የግብጽ ፖለቲከኞችና ሚዲያው ሲቆምር ግን ይደብራል$

እያወራን ያለነው ግብጽ ቅኝ ገዢዋን እና ጎረቤቷን ሱዳንን በማስማማት ለሀገራችን አንድ ጣሳ ውሀ ያስፈልጋታል ሳትል በስግብግብነት ስለፈጸመችው የዛገ ውልና ይህንኑ አሳፋሪ ስምምነት ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መብቴ እያሉ ስለሚደሰኩሩት ለዚህ ዘመን ስለማይመጥኑ ፖለቲከኞች ነው$

60 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር ዉሀ የምታበረክተው ምድር ህዝብ ጥምና ርሀብ ይፍጅህ ተብሎ 56 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር የሚጠጋውን ውሀ ያለማቅማማት የኔ መብት ነው ስትል ለሱዳን ደግሞ ከ20 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር በላይ ውሀ ትታላታለች$ ለኢትዮዽያዬ የቀራት ግን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጠላት የሚል ቅጥያ ነው$

ግብጽ ውሀ አጠር አካባቢ ከመሆኗ አንጻር ከሁሉም አገሮች የተለየ ውሀው እንደሚያስፈልጋት እናምናለን ይሄ ማለት ግን እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚል የቀረርቶ ፍቃድ ይኖራታል ማለት አደለም$ ሀገሬ ግብጾቹ ሲያሻቸው በሱማሌ በኩል ሲያሻቸው በኤርትራ በኩል በሚያደርጉት የማመስ ስትራቴጂ ዋጋ ስትከፍል መኖሯ የአደባባይ ሚስጥር ነው$

Thursday, June 6, 2013

Ethiopia better get prepared for the worst in case Egypt….



I don't understand when some so called patriotic Ethiopians ask me to think twice before keeping constructing the dam in the face of continuing threat to attack or sabotage it.

Some of them even reckon that Ethiopia shouldn't lose a single life to keep the construction happening. I tell thou you never know the nation and the blood you are. while we respect our neighbors and any country related to us in anyway, we didn't, haven't and won't fail to defend our sovereignty.

Thursday, May 30, 2013

Time to give Egypt a lesson


I am saddened to see such arrogance on the part of Egyptian politicians and media. They know for a fact that the dam doesn't harm their interest, they know Ethiopia has all the right to use the water responsibly even for irrigation let alone for electric generation. Yet they try and insight violence where there is none. 


Striking the dam, preventing Ethiopian ships not to use the canal or any other violent option doesn't give Egypt what it wishes. The best solution is to take the negotiations from where they got stalled and move them forward in a way they can come up with win-win solutions. Cooperation is the way out not a single bullet and weapon. 

Friday, May 24, 2013

አፍሪካና ህብረትዋ - እሰይ የተጫጫነሽ ድብርት እየለቀቀሽ ነው አብቢልን አፍሪካችን!

አፍሪካ የተበተነች ትልቅ አህጉር ሆና ከርማለች$ ሀብትዋ ያለጠያቂ ሲዘረፍ ኖሯል አልመች ሲል በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ስም ጦርነት ሁሉ እንዲቀሰቀስ በማድረግ ስትታለብ የኖረች ናት$ ወተቷን አልበው ሌሎች ሲጎነጩት እሷ የራሷን ወተት ተነፍጋ ኖራለች$
 
ከነጻነት ቀጥሎ በነበረው ግዜ ደግሞ የምእራባውያኑ እጅ መጠምዘዣ መሰራርያ ሆነው በስፋት ያገለገሉት ችግር ሁነኛ በሆነ መንገድ ፈተው የማያውቁት የእርዳታ ድርጅቶች ነበሩ$ ምእራባውያኑ እጆቻቸውን በነዚህ በጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል ከስማቸው የራቀ የፖለቲካ ስራቸውን እየሰሩ አህጉሪቱን እያመሱ መንግስታቱን እጃቸውን እየጠመዘዙ የሚሹትን ሀብት ሲቦጠቡጡ ኖረዋል$

እንደነ መለስ ዜናዊ እና ፖል ካጋሜ ያሉ መሪዎች በዋናነት ከሰሩት ስራ ውስጥ መጠቀስ ያለበት ይህን የምእራባውያኑን መጠምዘዣ ሆኖ ያገለግል የነበረውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኔትወርክ መበጠስ ነበር$ ከዚያም አልፎ መለስ ዜናዊ አፍሪካ የፖሊሲ ነጻነት እንዲኖራት በእርዳታ ስም የማይጠቅማትን ፖሊሲ ምርጫ በምእራባውያን መጋት የለባትም በሚል የዋሺንግተን ኮንሰንሰስ በመባል የሚታወቀውን የገበያ አክራሪነት ፍልስፍና በአፍጢሙ ደፍተውታል$

Wednesday, May 22, 2013

አሸናፊነትን ሰበብ አይረታውም


አሸናፊነት ያለሙትን ማሳካት እመረጡበት መድረስ መቻል ነው$ አሸናፊነት እንደ ኳስ ይነጥራል እንጂ እንደ ረጠበ ስፖንጅ እመሬት አይጠፈጠፍም$ አሸናፊ ልምድ በሚወጣም በሚወርድም እርግጫ አይረበሽም$ በቁምነገሩ በራሱ ህይወት ሂደት ሌሎች ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ሚና እንደሌለው ብቻ ሳይሆን ወሳኙን ሚናውን የሚጫወተው ራሱ ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል$

አሸናፊ ልምድ ለውድቀቶቹ ሰበብ አይቆጥርም ራሱ እንጂ ሌሎች ሰበቦች ለውድቀቱ መሰረታዊ ፋይዳ እንደሌላቸው ስለሚረዳ$ ሰው ልምድን እንደሚመስል ጠንቅቆ ያውቃል$ ሁዋኝ እንጂ ተደራጊና ተሰሪም እንዳልሆነ አይስትም$ ይሄን ቢስት እንኳ ሀቁ እንደማይቀየር ያውቀዋል$

ህይወት ምርጫ እንደሆነና ያን ምርጫ የማካሄድ ጉዳይ የራሱ ስለመሆኑ እርግጠኛ ነው$ የተሳሳተ ምርጫ በማካሄድ ወይም የመረጠውን ምርጫ በአግባቡ ባለመተግበሩ የሚመጡበትንም ጣጣዎች በጸጋ ዋጥ ያደርጋል እንጂ እነ እገሌ ይህን አድርገው ባይሆን ኖሮ ይሄ ባልሆነ ነበር የሚል ሰበብ አያውቀውም$ እነ እገሌ የማይገባ ነገር እያደረጉም ቢሆን የራሱን ከባቢና ምርጫ የሚያበላሹበትን ሁኔታዎች መቆጣጠር የሱ እንጂ የማንም ሀላፊነት እንዳልሆነ አሳምሮ ያውቃልና$