አፍሪካ የተበተነች ትልቅ አህጉር ሆና ከርማለች$ ሀብትዋ ያለጠያቂ ሲዘረፍ ኖሯል አልመች ሲል በዲሞክራሲና በሰብአዊ መብት ስም ጦርነት
ሁሉ እንዲቀሰቀስ በማድረግ ስትታለብ የኖረች ናት$ ወተቷን አልበው ሌሎች ሲጎነጩት እሷ የራሷን ወተት ተነፍጋ ኖራለች$
ከነጻነት ቀጥሎ በነበረው ግዜ ደግሞ የምእራባውያኑ እጅ መጠምዘዣ መሰራርያ ሆነው በስፋት
ያገለገሉት ችግር ሁነኛ በሆነ መንገድ ፈተው የማያውቁት የእርዳታ ድርጅቶች ነበሩ$ ምእራባውያኑ እጆቻቸውን በነዚህ በጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል ከስማቸው የራቀ የፖለቲካ
ስራቸውን እየሰሩ አህጉሪቱን እያመሱ መንግስታቱን እጃቸውን እየጠመዘዙ የሚሹትን ሀብት ሲቦጠቡጡ ኖረዋል$
እንደነ መለስ ዜናዊ እና ፖል ካጋሜ ያሉ መሪዎች በዋናነት ከሰሩት ስራ ውስጥ መጠቀስ
ያለበት ይህን የምእራባውያኑን መጠምዘዣ ሆኖ ያገለግል የነበረውን የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኔትወርክ መበጠስ ነበር$ ከዚያም አልፎ መለስ ዜናዊ አፍሪካ የፖሊሲ ነጻነት እንዲኖራት በእርዳታ ስም የማይጠቅማትን
ፖሊሲ ምርጫ በምእራባውያን መጋት የለባትም በሚል የዋሺንግተን ኮንሰንሰስ በመባል የሚታወቀውን የገበያ አክራሪነት ፍልስፍና በአፍጢሙ
ደፍተውታል$
መለስ ያንን ስብሰባ ለማድመቅ ያክል አልነበረም የሚያቀነቅነው በርግጥም የሀገሩን የፖሊሲ
ነጻነት አስጠብቆ እና ውጤታማነቱን በተግባር አረጋግጦ ነው አፍሪካ ለአጋዥ ግን ወሳኝ ላልሆነ እርዳታ ስትል መጻኢ እድሎችዋን የሚወስኑ
ጉዳዮችን ለውጪ አካላት አሳልፋ መስጠት እንደሌለባት ሲሞግቱ ቆይተው ውጤቱንም ማየት ችለዋል$
በዚህ ረገድ የመለስ ቁርጠኝነት ከ97ቱ ምርጫ ለጥቆ ምእራባውያኑ ሊፈጽሙ የፈለጉትን እጅ
ጥምዘዛ ባለማግኘታቸው እርዳታ ላለመስጠት ሲያስፈራሩ የመለስ መልስ ቀላል ነበር$ እስከ ዛሬ
የሰጣችሁን እርዳታ ጠቅሞናል ዛሬም ቢመጣ ይጠቅመናል$ ሆኖም ግን እርዳታቸው ህልውናችንን የሚወስን ሳይሆን ልንደርስበት የምንችለውን ርቀት
የመጨመር የሚፈጅብንን ግዜ የማሳጠር ሚና ነው የሚኖረው$ ለስከዛሬው ድጋፋችው እናመሰግናለን ባለመስጠታቸውም አይከፋንም$ የሚል ይዘት ያለው መልስ በመስጠት ምእራባውያኑ የተኪነት ሚና ሳይሆን የአጋዥነት ፋይዳ
ብቻ እንዳላቸው በመጥቀስ ጉዳዩን ቋጭተዋል$
እንዳሉትም ምእራባውያኑ ሚናቸውን በአግባቡ በማወቅ የልማት ድጋፋቸውን አጠናክረውና ጨምረው
ተመልሰዋል$ በዚህ ረደግ የልማት አጋሮቻችን እቺ አገር የእርዳታ ገንዘብ አጠቃቀሟ ዲስፕሊን አኩሪ
መሆኑን መስክረዋል$ መለስ በዚህ ሳያበቁ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች በኩል የሚገባውን እጅ እንደማንኛውም የምእራብ
ሀገር ህግ በመደንገግ ቆርጠውታል$
በወቅቱ ያ እርዳታን አስታኮ የሚገባው የፖለቲካ እጅ ሲቆረጥ የነበረውን ጫጫታ ያስታውሷል$ በየምርጫው ወቅት ማጨማለቁ እንደሚቀርባቸው በማወቃቸው ነው$ የሀገራችንን ዴሞክራሲ የመገንባት ሰራ የኛ እንጂ የለባጭ ጥቅም አሳዳጅ ወዳጆቻችን አደለም$ በርግጥ እኛም ብንሆን ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ነው የምንሰራው$
ተመሳሳዩን እንደ ካጋሜ ያሉ ሌሎች መሪዎችም ተከትለውታል$ አሁን አፍሪካ የውጭ ሀይሎች እንዳሻቸው እጃቸውን የሚከቱባት የመሆኗ ጉዳይ በእጅጉ እየጠበበ
መጥቷል$ ከዚህም በላይ አፍሪካ በተለያዩ ጉዳዩች ላይ አንድ አቋም በመያዝ በአለማቀፍ መድረኮች
መብቷን ለማስጠበቅ እየሰራች ነው$
እንደ ኢጋድ ያሉ አካባቢያዊ ትስስሮችና ህብረቶች በአካባቢያዊ ችግሮቻቸው ዙርያ ራሳቸው
መፍትሄ መፈለግ መጀመራቸው ማሳያ ነው$ ለምሳሌ የሳድክ የዚምባብዌን ጉዳይ በውይይት መፍታት ኢጋድ የሱዳንን እና የሶማሌን ጉዳይ
የፈታበት እና እያደራደረ ያለበት አፈጻጸም ኤኮዋስ በቀጠናው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚሰራው ስራ የዚህ ማሳያ ናቸው$
ከዚህ በተጨማሪም አካባቢያዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለመፍጠር እየተካሄዱ ያሉ የመሰረተልማት
ስራዎች ምስራቅ አፍሪካን ጨምሮ አኩሪ ናቸው$ በዚህ ረገድ ኢትዮዽያ ቀጠናውን በመንገድ እና በኤሌክትሪክ ለማያያዝ የምታደርገው ጥረት
ተጠቃሽ ነው$ ከዚህ በተጨማሪም ከቀድሞው በተለየ አፍሪካ በጂ8 እና በጂ20 የምታደርጋቸው ተሳትፎዎች
እና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ የምታደርገው ጥረት አኩሪ ነው$
በወርልድ ኢኮኖሚክ ፎረም ወይም በአለምአቀፉ የኢኮኖሚ መድረክ አፍሪካ እንደ መለስ ባሉ
ልባም መሪዎች ታቀርባቸው የነበሩ አማራጮች ውጤታማ ነበሩ$ አፍሪካም ከቀድሞው በተሻለ ተሰሚ እና ተፈላጊ እየሆነች ሄደች$ አፍሪካ
ባለፉት አስርት አመታት ያላት ሁኔታ በተለይ ባለፈው አስር አመት ተስፋ ሰጪ ነው$ እነ ቻይና አውሮፓ ህብረት ጃፓን ህንድ ቱርክ አሜሪካ በተናጠል አፍሪካ ጋር ኢኮኖሚያዊ
ትስስር ለመፍጠር የሚያደርጉት ጥረት የዚሁ አካል ነው$
እየተነሳች እየገነነች ያለች አህጉር መሆኗን እየመሰከሩ ያሉት ለኛ ብለው ሳይሆን እየተነሳ
ካለው አህጉር በመጎዳኘት የድርሻቸውን ለመጠቀም ነው$ ይሄ ደግሞ በአንድም በሌላም መልኩ የአህጉራዊውን ህብረት መጠናከርም ያሳያል$ ቻይና የሰራችው የህብረቱ ህንጻ የዚህ መሰሉ የአህጉሪቱ መፈለግ ማሳያ ነው$ ትስስሩም የአፍሪካን ጥቅሞች ያስጠበቀ እንዲሆን እየተሰራ ነው$
በተናጠልም ሀገሮች ከቀድሞው በተሻለ ጥቅሞቻቸውን ማስከበር እየቻሉ መሆኑ እየታየ ነው$ በርግጥ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነን ባይ ቅጥረኛ ድርጅቶች እንደ ኢትዮዽያና ሩዋንዳ
ሁሉን አቀፍ ለውጥ በማምጣት ላይ ያሉ ሀገሮችን በማጣጣል ሴኔጋልን እና ላይቤሪያን የመሳሰሉ ያሻቸውን ሊያደርጉባቸው የሚችሉ አገሮችን
የማመስገን ጠኔ ቢኖርባቸውም አፍሪካ ከነችግሮቿ ከትላንት እጅግ በተሻለ ጥንካሬ እና ህብረት ዙርያ እያደገች መሆኗን መካድ አይቻልም$
እናም የአፍሪካ ህብረት በአላማም ይሁን የአህጉሪቱን ጥቅም በማስከበር ረገድ ባለፉት አስር
አመታት የሚደነቅ ለውጥ ታይቶበታል$ ለዚህም ነው አፍሪካ ከምእራቡ ሚድያ እስከ ምስራቁ ሚዲያዎች ድረስ እየተመነደገች ያለች
አህጉር በመባል የምትወደሰው$ ተስፋዬ እጥረቶችሽን የበለጠ አሻሽለሽ የተሻለ አፍሪካ እንደምትሆኚ ነው$
እሰይ የተጫጫነሽ ድብርት እየለቀቀሽ ነው አብቢልን አፍሪካችን!
No comments:
Post a Comment