ከሰሞኑ ህገመንግስቱ እንዲከበር የሚጠይቁ ድምጾች በርክተዋል$ የምር እንዲህ ያለው ጥረት መደገፍ ያለበት ነው$ መብታችን ሳይሸራረፍ እንዲከበር መታገል ይኖርብናል$ በዚህ የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ ጥቂት ግለሰቦች የምር ህገመንግስቱ ተሙዋልቶ እንዲከበር
እንደሚፈልጉ አምናለሁ$
ይሄን ዘመቻ በዋናነት የሚያቀነቅነው ቡድን ግን ሊያስተውላቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች
በመኖራቸው እነዚያን ማንሳት የግድ ይላል$ ሲጀመር መከበር ያለበት መብት አንቀጽ 30 ብቻ አደለም$ መከበር ያለበት ሁሉም አንቀጽ ነው- 106ቱም አንቀጽ$
ይሄ ህገመንግስትን የማክበር ጉዳይ በተቀመጠው ህጋዊ መንገድ እስካልተቀየረ ድረስ የተቃዋሚዎቻችን
ራስ ምታት ለሆነው አንቀጽ 39ም የሚሰራ ይሆናል ማለት ነው$
ይሄ የሰላማዊ ሰልፍና ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ጉዳይ በተናጠል ለምን
እንደሚቀነቀን አይገባኝም$ መብታችን ሳይሸራረፍ የሚከበረው ህገመንግስቱ በምልአት ሲከበር እንጂ ለወቅታዊ አጅንዳ
የምትፈለግን አንቀጽ በማንጠልጠል አይመስለኝም$
መንግስት ህገመንግስቱ ይከበር ብሎ ሲሰራ ህገመንግስቱን ህገ አራዊት የሚሉትና ሰላማዊ
የትግል አማራጮች በመዳፈናቸው ያለን አማራጭ አመጽ ብቻ ነው የሚሉን ወዳጆቻችን ደርሰው ለህገ መንግስቱ ተቆርቁዋሪ ሲሆኑ ከበስተጀርባው
ያንጠለጠሉት ህገወጥ አንቀልባ እንደሚኖር ብንጠረጥር የሚነወር አይመስለኝም$
በዚያ ላይ መብታችን ሳይሸራረፍ ይከበር በሚል አጀንዳ ስር የተሸረፉ ሁለት አንቀጾቻችንን
አንጠልጥሎ ያለወትሮው ለህገመንግስቱ ቀንደኛ ደጋፊ ሆኖ ለመታየት የሚሞክርን ቡድን ቆም ብሎ መገምገም በምንም መስፈርት ከበቅሎ
ራስ ቀንድ እንደ መፈለግ የሚቆጠር አይመስለኝም$
ደግ ይሁን ይሄም የህገመንግስቱ አካል ነውና እንዲከበር መስራት ይገባል$ ግን ይሄ ቡድን ከቀናት በፊት ሲፈጽም የነበረውን አዋራጅ ተግባሩን እንዴት ዘንግቶት
ነው ለሀገርና ህገመንግስት እንደሚቆረቆር ሀገር ወዳድ ብቅ ያለው? አባይ ፕሮፖጋንዳ ነው አይሰራም እየተሰራም
አደለም ይልቁንም ባለስልጣኖቹ ኪሳቸውን ሊያደልቡ የፈጠሩት ማወናበጃ ነው ያሉን አደሉም ወይ?!
አይናችን ስር እየበቀለ ያለውን ከደማችን የወፈረውን የአባይን ጉዳይ የካዱንና ያንኑ ለመገንባት
የሚሰባሰበውን ገንዘብ ለማስቆም ያልተሳካ ግን አዋራጅ የሀገር ክህደት ከሚፈጽሙ ቡድኖች ጋር ይሰራ የነበረ ቡድን መሆኑን ስናስብ
የዚህ አላማ ያልተሳካውን በፌስቡክና በትዊተር አመጽ ለመፍጠር ሲደረግ የነበረውን ጥረት ለማንሰራራት የሚደረገው ጥርጊያ አካል እንደሆነ
አንስተውም$
ብዙዎቹ ይሄንን ጥረት የሚያቀነቅኑት ግለሰቦችና ይሄ መልእክት የሚተላለፍባቸው የፌስቡክ
አካውንቶች በሀገሩ ላይ ክህደት ለሚፈጽመውና ከግብጽ ጋር ለመስራት ከሚጥሩ ቡድኖች ጋር በመተባበር የሚያሰራጫቸውን ሀሳቦች ስናስታውስ
አጀንዳው ህገመንግስት የማስከበር ጉዳይ ሳይሆን አመጽ ለመፍጠር ቀዳዳ ይፈጥሩልናል የሚሉዋቸውን ህገመንግስታዊ ድንጋጌዎች ለነውጥ
የማመቻቸት ጉዳይ መሆኑን መገመት ከባድ አደለም$
ይሄን የምለው አንዴ የተሳሳተ አይታረምም የሚል ደንጋራ አተያይ ስላለኝ ሳይሆን ይሄን
አቁዋም ባራመዱበትና ሀገራዊ ክህደት በፈጸሙበት የሳምንት እድሜ በማይሆን ግዜ ከስህተታቸው ትምህርት ወስደው አተያይና ስነምግባራቸውን
የመቀየር በቂ ግዜና አጥጋቢ ምክንያት ስለማይታየኝ ነው$
እንዲያውም አዋራጁን ሀገራዊ ክህደታቸውን ለማረሳሳትና አጀንዳ ለመቀየር የሚያደርጉት ጥረት
አካል አድርጌ ነው የማየው$ በአባይ ግድብ ላይ የፈጸሙት ክህደት ታሪክ የማይረሳው ሆኖ ይቀጥላል$ ይቅርታ የምናደርግላቸው ቢሆንም የተግባራቸው አዋራጅነትና የፈጸሙት የሀገር ክህደት ግን
የማይዘነጋ ክስተት ሆኖ ይኖራል$
ወዳጆቻችን ቁምነገሩ አጀንዳ ማስቀየር አደለም$ በተግባር የባህርይ እና የአመለካከት ለውጥ ማድረግ ነው$ የተከናነባችሁት ኪሳራም አጀንዳ በመቀየር የሚጠግግ አይነት እንዳደለ እናንተም አትስቱትም$ ይሄን አንድና ሁለት የማይዋጥላቸውን አንቀጽ ጠቅሰው ህገአራዊት የሚሉትን ህገመንግስት
እንዴት ደርሰው ተቆረቆሩለት የምንለው ይሄን በተደጋጋሚ ሀገር የካደ አካሄድና አመለካከት ስለምናውቅ ነው$
ይሄ ህገመንግስት በመቃብሬ ላይ ካልሆነ በቀር በአመጽ ማንም አየቀይረውም እያለ ኢህአዴግ
ለህገመንግስቱ ያለመሸራረፍ መከበር ሲከራከር እኒህ የህገመንግስት ነቢያት እውን የት ነበሩ?! ወይስ የሚደግፉት ፓርቲ ስለተቃወመው ያኔ አንገታቸውን ደፍተው ነው!?
የህገመንግስቱ ጠበቃ ኢህአዴግ የህገመንግስቱ ባለቤት ኢህአዴግ በህጉ ተጠቃሚው ኢህአደግ
አድርገው የሚስሉት ተቃዋሚዎች ደርሰው ዛሬ በአመዛኙ ቃል አቀባዮቻቸው በሆኑ የፌስቡክ ወዳጆቻችን በኩል ይሄን ህገመንግስታዊ ጥብቅናቸውን
ሲያሰሙን ያ ለ20 አመት የጸና ደንዳና ተቃዉሞ እንዴት ተኖ ነው ብንል አይፈረድብንም$
ለነገሩ ቁምነገሩን አልሳትነውም መብታችን ተሙዋልቶ ይከበር የሚሉን አንድና ሁለት አንቀጽ
ጠቅሰው መሆኑን ስንታዘብና እነዚያንም አንቀጾች አምነውባቸው ሳይሆን ሊበሉዋት የፈለጉዋትን ቆቅ ሆኖባቸው እንደሆነ
ይገባናል$ እነሱ ሲሰለፉ ሀገር ለመጉዳት ያልተጋበዙበትን ስብሰባ ለመበጥበጥ ጭምር ሲሰለፉ መብታቸው ሆኖ ሌላው አቁዋሙን በሰልፍ
ሲገልጽ ሆዳምና ተገዶ የወጣበት ሆኖበት እንዲሚያደርጉት እና ያኔ እንደሚቃወሙት አንስተውም$
ይሄ የፌስቡክ ዘመቻ ህገመንግስታችን ሳይሸራረፍ በምልአት ይከበር በሚልና ሁሉንም አንቀጾች
በሚያንጸባርቅ መልኩ ሲካሄድ እንደ ኢህአዴግ ሁሉ ሁሉም ቡድን በመቃብሬ ላይ ካልሆነ ይሄ ህገመንግስት በአመጽ አይቀየርም የሚል
የጸና አቁዋም ሲያራምድ ያኔ ድመቱዋ የመነኮሰችው ጥፍሩዋን የምር ቆርጣው መሆኑ
ይገባናል$
እቺ ማጨናበሪያ የአባዩን መዋጮ ለማስቀረት ሞክሮ የበለጠ መገለል የገጠመው አክራሪ ተቃዋሚ የፈጠራት የተጠናች ዘመቻ
መሆኑዋን ስለምናውቅና ስለምታውቁት ግድየለም በሽፍንፍን ትቅርባችሁ$
በርግጥ ግን የምር ሁላችንም የህገመንግስታችን ተቆርቁዋሪ ብንሆን የሚያኮራ ይሆናል$ ይሄ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ$ ይቆየን!