በሀገራችን ከሚሰሙ ፖለቲካዊ ወቀሳዎች መካከል አንዱ ኢህአዴግ የቁጥር ጨዋታ ስለሚወድ ካልሆነ በቀር ይሄ አገር አላደገም የሚለው ጉልሁ ነው።ሌላው ባለፉት 20 አመታት የሚጣጣለው ጉዳይ ሀገሪቱ በዴሞክራሲያዊ መብቶች ረገድ የረባ ለውጥ አላደረገችም እንዲያውም ከምርጫ 97 ቀጥሎ ባሉት አመታት ለውጡ የሁዋሊት ተንሸራቷል የሚለው ወቀሳ ነው። እነዚህን ክሶች ከመሰረታዊ ጉዳዮች አንጻር መገምገም ይሆናል የዚህ ጽሁፌ ቁምነገር።
በመሰረቱ እነዚህን አቤቱታዎች ለመቃኘት
የመረጥኩት በትምህርት ዘርፍ እየሆ ካለው ነገር በመነሳት ነው። መረጃዎች እንደሚያመላክቱትና የተለያዩ
አለማቀር ተቁዋማትም ግምገማዎች እንደሚያሳዩት የሀገራችን የትምህርት ሽፋን በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች መቶ በመቶ ተሳክቷል
ሊባል በሚችልበት ደረጃ ደርሷል።
ቁምነገሩ የትምህርት ሽፋኑ መቶ በመቶ መሆኑ ግን አደለም። እኔም በዚህ ቀደዳዬ ማሳየት የፈለኩት
ይሄን ስራ የሚመራው ፓርቲ አጀንዳ ይሄን መሰሉን ስራ በመምራት እና በማሳካት ረገድ ምንድነው የሚለውን ማጠየቅ ነው።
ትውልዱ ወይም የዚህ ሀገር ዜጋ መብቶች በዋናነት የሚከበሩት ከአዲስ አበባ ወይም ከክልል በሚስፈነጠሩ ሬድዮኖች ቴቪዎች ወይም ጋዜጦችና መጽሄቶች አደለም።በመሰረቱ የህዝባችን መብት የሚከበረው መብቱን መጠየቅ የሚያስችለው ንቃትና እውቀት ያለው እንደሆነ ነው።በመሆኑም ህዝቡ እንዳይጠይቅ እና አፉን ዘግቶ እንዲኖር የሚፈልግ መንግስት ማድረግ ያለበት በቀላሉ በትምህርት የማስፋፋት ስራ ላይ በጎልማሶች ትምህርት ላይ እና በአጠቃላይ የማህበረሰቡን ንቃት በሚያሳድጉ ስራዎች ላይ መለገም ነው።
ትውልዱ ወይም የዚህ ሀገር ዜጋ መብቶች በዋናነት የሚከበሩት ከአዲስ አበባ ወይም ከክልል በሚስፈነጠሩ ሬድዮኖች ቴቪዎች ወይም ጋዜጦችና መጽሄቶች አደለም።በመሰረቱ የህዝባችን መብት የሚከበረው መብቱን መጠየቅ የሚያስችለው ንቃትና እውቀት ያለው እንደሆነ ነው።በመሆኑም ህዝቡ እንዳይጠይቅ እና አፉን ዘግቶ እንዲኖር የሚፈልግ መንግስት ማድረግ ያለበት በቀላሉ በትምህርት የማስፋፋት ስራ ላይ በጎልማሶች ትምህርት ላይ እና በአጠቃላይ የማህበረሰቡን ንቃት በሚያሳድጉ ስራዎች ላይ መለገም ነው።
በኛ ሁኔታ እየሆነ ያለው በአንድ
በኩል የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋን መቶ በመቶ ማድረስ የሚያስችል ጥድፊያ በሌላ በኩል ደግሞ የጎልማሶችን ትምህርት በማጧጧፍ
የማንበብና መጻፍ ክህሎታቸውን ብቻ ሳይሆን ጥቅል የህይወት ክህሎታቸውን የሚቀይር ትምህርት ለማድረስ የሚተጋ ርብርብ ነው።
ይሄ በየትኛውም መስፈርት ህዝቡ
እንዳይጠይቀው የሚፈልግ ባህሪ ነው ሊባል የሚችል አደለም። እንዲያውም በስልጣን ላይ ያለው
ፓርቲ ህዝቡ መረጃዎችን መከታተል የሚችልበት የማንበብና የመጻፍ ክህሎት በማዳበር ህትመቶችን መከታተል የሚችልና ከሚዲያ የሚደርሰውን
መረጃ መገምገምና መተንተን የሚችል ማህበረሰብ ለመፍጠር እምነት ያለው መሆኑን የሚያሳይ መሆኑ አጠያያቂ አደለም።
ይሄ የትምህርት ስራ ባለፉት
15 አመታት ከ100 ሺ በላይ የነበረውን የመምህራን ብዛት ከ300 ሺ በላይ ያሳደገ የትምህርት ቤቶችን ብዛት ከ11 ሺ ገደማ ወደ
30 ሺ በላይ ማድረስ የቻለ ለእያንዳንዱ ተማሪ መጽሀፍ ለማዳረስ የተማሪና የክፍል ጥምርታን ለማሻሻል የሚተጋ መሆኑ ሲታይ የፈጠረውን የስራ
እድል ትተን ገጠሩን መረጃ ቀመስ ማህበረሰብ በማድረግ ረገድ መብቱን መጠየቅ የሚችልበት እውቀት እንዲኖረው ለማድረግ የሚሰራው ስራ
አካል መሆኑ አይሳትም።ይሄ ወሳኝ የሚሆነው ሀገራዊ ዴሞክራሲና መብት በጥቂት የተማሩ ከተሜዎች ትጋት የማይፈታ በመሆኑ ነው።
ከዚህ ውጭ በይዘትም ረገድ ዜጋው
ህገመንግስታዊ መብቱን እንዲያውቅ እና መጠየቅ እንዲችል ስነዜጋ የትምህርት ስርአቱ አካል መደረጉ መንግስትን የሚመራው ፓርቲ በዚህ
ሀገር ዴሞክራሲን በምልአት ለመተግበር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳብቅ ነው።በርግጥ እንዲህ ያለው ሀገር በቀል
እውቀት በቀል የዳበረ ዴሞክራሲ ግዜ መውሰዱ ባይቀርም በሳል እና የዳበረ ዴሞክራሲ እና ልማት ማምጣቱ ግን የሚጠረጠር አይሆንም።
በባህሪው አንድን ሰው በትምህርት
አብቅቶ እንኳ ለማስመረቅ ወደ 16 አመታት ገደማ የሚወስድ ከመሆኑ አንጻር ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመላው ሀገሪቱ በሚፈለገው መልኩ
ማስከበር የሚችሉ ብቁ ዜጎች አሁንና ወዲያው መፍጠር እንችላለን ባይባልም በአስርት አመታት ያላሰለሰ ጥረት ግን በርግጠኝነት ይህን
ማድረግ እንደሚቻል እርግጠኛ መሆን ይቻላል።
ምንም ሌላ ነገር መጥቀስ ሳያስፈልግ
ይሄ አገር የትምህርት ስራውን ከሚያከናውንበት ጥድፊያና ፍላጎት አንጻር የምር ማህበረሰቡን ለሚፈለገው ሀገራዊ ልማት በክህሎትና
በእውቀት ብቁ ከማድረግም ባለፈ መብቱን ማስከበር የሚችልበት ግለሰባዊና ማህበረሰባዊ አቅም በመፍጠር ረገድ ሁነኛ ቦታ እንዳለው
ማስተባበል የሚቻል አይመስለኝም። ይቆየን
No comments:
Post a Comment