Wednesday, May 15, 2013

እምነቴ ከሆዴ ስር ውሎ አያውቅም ሆዴም ሀሳቤን እንዲጫነው አልፈቅድም

ይቺ ዬኖክ ስጦታው ስለጋዜጠኝነት ገለልተኝነትና ስለኔ አድርባይነት ለጻፋት የፌስ ቡክ አስተያየቱ ያሰፈርኩለት ማረሚያ ናት፡፡ ኄኖክ ስጦታው ምን መሰለሽ ማወቅ ያለብሽ ገለልተኛ የሚባል ጋዜጠኝነት የለም፡፡ ማረጋገጫ አቅርቢም ቢሉሽ ማጠፊያው ያጥርሻል ለነገሩ ለአሁን አትጨነቂ አላፋጥጥሽም፡፡ እቺን የምትማሩት ከተሳሳተው የጋዜጠኝነት ሀሁ ነው፡፡ 

አቋም ኖሮህ ሲያበቃ ግን ሚዛናዊ መሆን ደፋር መሆን በጨዋ ደንብ ሀሳቦችህን ማቅረብ የሚታየውን እውነት መናገር ይጠይቃል፡፡ የሚመርህን የዚህን አገር ለውጥና የኢህዴግን ስኬቶች ጭምር፡፡ 

በርግጥ አንተ የተቃዋሚዎችን የላሸቀ ቁመና መግለጥና የኢህአዴግን ስኬቶች መናገር ቢቀፍህም፡፡ አንተ የምትተቸው ይሄ ሲቀር ነው፡፡ ለአቋምህና ለአጀንዳህ ማራመጃነት ስለማይሆን፡፡ 

እኔ ሄንዬ በአደባባይ ስህተቶቹን አውጀ ለመታረም የሚጥር ድርጅት ደጋፊ በመሆኔ እጥረቶችን እንዲለወጡ በማሰብ ከመናገር ዞር ብዬ አላውቅም ላንተ ማረጋገጫ አቅርቤ ባላውቅም፡፡ ኢህአዴግን ሲያስፈልግ በደንብ እተቸዋለሁ በአሰራሮችና በአባላት ስነምግባር እንዲሁም በሌሎች የአፈጻጸም ችግሮች፡፡ ፖሊሲዎቹ ለኔ ስለሚያሳምኑኝ አልቃወማቸውም፡፡

በርግጥ እንዳንተ የማጣጣል አባዜ እንዲለክፈኝ እና የእርግማን ዘፋኝ እንድሆን አልመኝም፡፡ ፈጽሞ ሄንዬ ታዞ ነው አይፈረድበትም ብለህ አትዘንልኝ፡፡ የምር አምኜበት ነው የምሰራውን የምፈጽመው በፍቅር፡፡ 

ስትፈልግ ሆዳም ስለሆንክም ነው በለው የምርም አላማው አሳምኖት ታውሮም ነው በል ለእምነቴ ነው የምሰራው፡፡ ይሄን የታዘዘውን ነው የሚሰራው የሚለውን ሀዘንህን ለሌሎች ቆጥበው አይለቅብህ፡፡ 

የኔ ጌታ ነፍሴን ካወኩበት ግዜ ጀምሮ አብረውኝ የተማሩና የሰሩ እንደሚያውቁት አቋሜን ከማራመድ ፈቀቅ ብዬ አላውቅም፡፡ እንዳንተ አይነቱንም ለመቃወምም 
ጭምር ቢሆን ማለቴ ነው፡፡ 

አሁን ፖስት ያደረከው ጽሁፍ ስራ እየሰራሁ መሆኔን ከማሳየቱ በቀር ወዳጆችህ ላይክና ኮሜንት ስላደረጉበት ያወርደኛል ያወጣኛል ብዬ ስለማልጨነቅ ነው የመሰለኝን አቋም የማራምደው፡፡

አንተ የምትሰራው ጨለምተኛ ተግባር ነፍሴ የምትጸየፈው በምርጫ የተውኩት እንጂ እኔ ደክሜበት ባንተ እንዳልተነሳ ላርዳህ፡፡ ባዶ ጨለምነተኝነት ምርጫዬ አደለም፡፡ በመረጃ የጎለመሰ ሀቀኛ የማረም ታጋይነትን ግን መርጬ እሸነፍለታለሁ፡፡ ካንተ ማረጋገጫ እስካሁን ባይሰጠኝም ያንን ምርጫዬን እየነኖርኩት ነው፡፡


ለመታገል የግድ አደንቋሪና ባዶ ተቃዋሚ መሆን አያስፈልግም፡፡

ይቆየን ንትርካችን ይቀጥላል፡፡

No comments:

Post a Comment