ስለቀደሙ ነገስታቶቻችን አውርተው የማይጠግቡ ወዳጆቻችን ስለመለስ ማውረቱ ቢቀርባቸው አንኳ ስለሱ በሚወዱት ግለሰቦችና በፓርቲ ጓዶቹ መዘከሩ ለምን ያንገበግባቸዋል
አሁን መለስ የቀረው ይቅር እንደው
ለነገስታቱ የሚከትቡትን ያክል የሚከትቡለት ስኬቶች ብልህነቶች ድሎች አተውለት ነው ወይስ በሱ አመራር ወቅት የተከሰቱ ድክመቶች ነገስታቱ
ከሰሯቸው ስህተቶች ገዝፈው ነው ወዲያ መንደር ያሉ ወዳጆቻችን በዘከርነው ቁጥር ምርር ብለው የሚያለቅሱት
እነሱም አልነበሩ የትኛውም ንጉስና
መሪ ከነችግሩ ሊያስመሰግነው በሚገባው ሊታወስ ሊደነቅ ይገባዋል እያሉ ሲሰብኩን የነበሩት
ዘክሩ ብለን አላስገደድን በገዛ
የመዘከር መብታችን ለምን ይነተርኩናል
በርግጥ የኛ መንደር ዝክር ወቀሳና
ትችት ተጠምቆ የሚጠጣበት አደለም እኛ ሰፈር ዝክር ዛፍ ተከላ የፖሊሲ ክርክር የልማት ቃልኪዳን ማደስ የአመራር እና የፖሊሲ ስልጠና
ነው እኮ ለምን ብለን ጣላቶቹን እንውቀስ እኮ ለምን በሌሎች ላይ ጣት እንቀስር ዘመን የሚሻገሩ ችግር በሂደት የሚያረግፉ የፖሊሲና
የተግባር ውይይቶች እያሉን እኮ ለምን ድዳችንን ውሀ በማይቋጥር ጉዳይ እናልፋ
በርግጥ ሰውየው በአመዛኙ አማራና
ትግሬ ሲነዳው የነበረውን የዚህን አገር ስልጣንና የፖለቲካ መድረክ በየብሄሩ አስደፍሮታል
በርግጥ ሰውየው የሰሜኖቹን በመላው
ሀገሪቱ የነበረ የማስተዳደር ስራ የየአካባቢው ሰው ራሱን ለማስተዳደር አያንስም በሚል ህገመንግስታዊ ድንጋጌና ፈሊጥ የየብሄሩን
ተፈጥሮ የሚያከብር አሰራር ደንግጎ በስንቱ ተሿሚና ተጠቃሚ ጉሮሮ ላይ ቆሟል
በርግጥ ሰውየው አንድ የፖለቲካና
ኢኮኖሚ ማህበረሰብ የሚፈጥር ህገመንግስትና ፖሊሲ በአግባቡ ይሰናዳ እንጂ ህዝብ በየቋንቋውና ባህሉ መሰረት ሊፈጽመው ይችላል በሚል
ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ነባሩን የአማራኛን ሚና የሚቀይር አሰራር ዘርግቷል የሚገርመው ክሽን ባለ አማርኛ ሀገር መምራቱን አለመዘንጋቱ
ነው
በርግጥ ሰውየው የተሻልን ነን የላቅን
ነን የሚለውን የአንዳንድ የመሳፍንትና የነገስታት ዘር ቆጣሪዎችን እኩል ነን በሚል ታርጋ ማውደሙ ሲታይ ክብራቸውን ዘር እየጠቀሱ
ለሚቀዱ ሰዎች ሬት መሆኑ አጠያያቂ አደለም
በርግጥ ሰውየው ኪራይ ሰብሳቢ ነፍጠኛ
ጠባብ ትምክህተኛ አሸባሪ ጎጠኛ ጥገኛ የሚባሉትን ልምዶችና ጥቅሞች ለማፍረስ የተፋለመ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ ብዙዎቹን ማስኮረፉ
አልቀረም
በርግጥ ሰውየው የስንቱን ቤትና
አጥር የእርሻ መሬት ወዘተ መንገድ ሲገነባ ኤሌክትሪክ ሲያመነጭ ዉሀ ሲቆፍር ትምህርት ቤት ሲገነባ ጤና ጣብያ ሲያንጽ ያወደመ በመሆኑ
ይታወሳል ቅሉ ካሳ ቢከፍልስ ማን ይህን ለመሰለ ተግባሩ ይዘነጋዋል እንጂ
በርግጥ ሰውየው በግርግር ወደስልጣን
ርካብ ለመንጠላጠል ለሚመኙ ሰዎች የማይመቹ ህጎችና ዴሞክራሲያዊ አሰራሮች እንዲቀመሩ አመራር የሰጠ በመሆኑና ያን በማስተግበሩ ይኮነናል
በተለይ ይሄ የአሸባሪ ህጉ በአመጻ መንጠላጠል ለሚፈልጉ የፈጠረው ደንቃራነት የዋዛ አደለም
በርግጥም ሰውየው መራራ ትግል በሚጠይቀው
የታሪካችን ወሳኝ ወቅት በቅቶ በመገኘት ለስሙና ለዝናው ሳይሆን ለሀገር ይበልጥ ለሚጠቅመው ልማትና ዘመን ተሻጋሪ ዴሞክራሲያዊ ትግል
ከመራራ አስተሳሰቦችና አሮጌ ልምዶች ጋር የተፋለመ ነው
አዎን ቁልቁል እየተፈጠፈጠች የነበረችን
አገር ሽቅብ ለማንደርደር የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ ኢኮኖሚያዊም ፖለቲካዊም ትንሳኤዋን የጠነሰሰ በመሆኑ በርካቶችን የድህነት ውስጥ
ከበርቴዎችና ተጠቃሚዎች ማስቀየሙ አይቀሬ ነው
ፍንትው ብሎ እንደሚታየው ግዙፍ
አድናቂዎች ጥርት ብሎም እንደሚታየው መራራ ጠላቶችና ወቃሾችም አሉት
መልአክ አልነበረም መልአክ ነኝም
አላለም ግን የሰው ልጅ እቺን አገር ሊሰራትና ሊመራት በሚችለው ሚዛን ሲሰላ ለዘመናት የማንዘነጋቸው በመቶ አመታት ታሪኮቻችን ያልተሳኩ ጉዳዮችን በሁለት
አስርት አመታት ብቻ በተዋበ የፖለቲካ ፍልስፍናና በሚቆጠሩ ኢኮኖሚያና ፖለቲካዊ ስኬቶች ያንቆጠቆጠ ጀግና ነው
ለምን አይታወስ አጽሙን ለዘመናት
እንዘክረዋለን
ደግሞስ ይሄ ሁሉ ወቀሳ በስሙ ዛፍ
በተከልን ነው በስሙ የፖሊሲ ክርክር ስላደረግን ነው በስሙ የአረንጓዴ ልማትና የልማታዊ መንግስትን ፍልስፍናዎች ይበልጥ ስለተነተንን
ነው በስሙ የአገር ልማትና እድገት ግስጋሴያችንን ለማስቀጠል ቃል ኪዳን ስላሰርንና ስላደስን ነው
ለምን አይታወስ አጽሙን ለዘናት
እንዘክረዋለን!
ቁምነገሩና ልዩነቱ ያለው የኛ ዝክር
ወቀሳ መጥመቂያና የትችት ናዳ ማጉረፊያ አለመሆኑ ላይ ነው
ኢትዮዽያዬ በቁሙም በሞቱም ዛፍ
የሚያስተክልና የልማት ግስጋሴሽ ማነሳሻ ቀንዲል የሚሆን መሪ ደጋግሞ ይስጥሽ ለፓርቲውና ለህዝቡ ውስኪ መራጨትንና ድግስን ሳይሆን
ትጋትንና የሚንተገተግ የልማት ተነሳሽነትን አውርሶ የሄደ መሪ
ድህነት ያለእረፍት የሚገላትንና
የሚያማትን ሀገር ቀን ከሌት ያለእረፍት ከ20 አመት ለሚልቅ ግዜ ያገለገለ ሰው መለስ ዜናዊ!
ማረፍ እፈልጋለሁ እረፍትን ማየት
እፈልጋለሁ እያለ ለሚያማትና በየለቱ ለምትሞት ሀገሩ እረፍት ሲሰራ ያረፈን መሪ ካልዘከርን እኮ ማንን ልንዘክር!
እናስ ለዘመናት ዜና ሆኖ ቢኖር
ለወጣቶች አብነቱ ቢተርፍ እንጂ ምኑ ላይ ነው ጉዳቱ
በርግጥ ለትችት ጠማቂዎቹ ዝምታው
ንግግሩ ሳሉ ፖሊሲው ፍልስፍናው ልማቱ ህመሙ ሞቱ ቀብሩ ሚስቱ ልጆቹ ትውስታው መዘከሩ ሁሉ ህመማቸው ስለሆነ ዛሬም ያንኑ ዘፈን
በአዲስ ገንቦ ጠምቀው ቢያሽጎደጉዱት አይገርመንም
እነሱም ይጮሀሉ እኛም ትዝታውና
ዝክሩ ዛፍ እያስተከለን የሀገራችንን ህዳሴ በአረንጓዴ ልማት እንድናጅበው ስንቅ እየሆነን ይዘልቃል!
No comments:
Post a Comment