Monday, August 19, 2013

በርግጥም ስለበላን ነው ለኢህአዴግ የምንጮህለት

አርሰን ያለማንም ተማኝነት መሸጥ በገቢው መጠቀም ስለቻልን
ባለብር በመሬት ይሸጣል ይለወጣል ስም መሬት እየጠቀለለ የባለ እኩል ተካፋይ ስላልሆና በመደለያ እየተታለልን ለልመና እና ለሌላ ጪሰኝነት ስላልተዳረግን

በርግጥም ስለበላን ነው የምንጨኸው ስላበላንም ነው ኮሮጆውን በድምጻችን የሞላነው

የምንማርበት ትምህርት ቤት የምንታከምበት ጤና ጣብያ ስለተሰጠን
በሽታን የሚከላከሉ ጠበቆች አዋላጆች ስለተላኩልን ጥቅማችን ያናግረናል

አዎን ስለበላን ድርቅ ሁሉ ርሀብ እማይሆንበት በእርዳታም ቢሆን ከሞት የምናመልጥበት መንገድ ስለተበጀ እንጮሀለን
አዎን የወጣቶች ፓኬጅ የሴቶች ፓኬጅ የሚባል ጥቅም ስላገኘን ስለተለወጥን ድምጻችንን ከፍ አድርገን የፖሊሲውን አዋጭነት የኢህአዴግን ህዝባዊ ውግንና የመለስን ትጉህ መሪነት እንመሰክራለን


ልክ ተብሏል ነግደን እስካሻን የሀብት መጠን መያዝ ስለቻልን ባሻን የንግድ ዘርፍ መሰማራት ስለቻልን ጥቅም ያስጮኸናል


ድሮስ ፖለቲካን የጽድቅ ጉዳይ ማን አደረገው ፖለቲካ የጥቅሞች ትግል የሚካሄድበት ነው ጥቅሞችን በፍትሀዊነት እያጣጠመ የሚመራ እንደ ኢህአዴግ ያለ ፓርቲ ደግሞ በአሸናፊነቱ ይዘልቃል


መንገዱን ዉሀውን ኤሌክትሪኩን ስልኩን ኢንተርኔቱን ዩኒቨርስቲውን ጤና ጣብያውን አስኳላውን በየመንደሩ ስላመጣልን ድምጻችንንም ምስክርነታችንንም ለኢህአዴግ ሰጠን


አዎ በበላንበት አዎ ለጠቀመን ጮህን
እናንተም የምትጮሁት ለጽድቅ አደለም ተገቢ ለሆኑና ላልሆኑ ጥቅሞቻችሁ ብቻ ነው


ለሰማያዊው መንግስት ከሆነ ትግላችሁ ሞያና ቦታ ቀይሩ ይሄ ምድራዊ ጥቅሞች የሚጣጣሉበት ሰፈር ነው


ሆዳም ካድሬ በማለት  የምታወናብዱበት ግዜ አበቃኮ

አዎን የተሻለ ጥቅሞቻችንን እያስከበረ ላለ ብቁ ፓርቲ ለኢህአዴግ እንጮሀለን ድምጻችንን እንሰጣለን

No comments:

Post a Comment