Wednesday, April 3, 2013

እነ ስድብ ጌጡ


አንዳንድ ተቃዋሚዎች የሚቃወሙትን ነገር ድክመት ማሳየት ሲገባቸው
የሚደግፉትንና የሚያቀርቡትን አማራጭ በማብራራት ለማሳመን መጣር ሲገባቸው
ልዩነታቸውን በስርአት እንኳ ማቅረብ ሳይችሉ

ይሄ አገር ዲሞክራሲ ስለመራቡ የዛሬዎቹ መሪዎች ሌቦች ስለመሆናቸው እና
ይህን መንግስት በልማታዊ እና ፖለቲካዊ ጥረቶቹ የደገፈውን ሁሉ ለሆዱ ያደረ ሌባ
ስለመሆኑ ይነግሩናል።

እውን በምን መስፈርት ነው ተሳዳቢ ለህዝብና ለፍትህ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት
ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው።

የምታየውን ወንድምህን ሳታከብርና በስርአት ሳታናግር ጥቅል አገርህን በአግባቡ
ስለመምራትህ ያን የማድረግ ስነምግባሩ ያለህ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለንም።

በቀላሉ ስድብ ተሳዳቢን ያቀላል እንጂ ተሰዳቢን አያሳንስም። ስድብን ትጥቅ ያደረገው
ወገን ነው የሚቀለው እንጂ ስድቡ የተነጣጠረበት ተወቃሽ አይደለም ተዋራጁ።

ወራዳ ብሎ ተሳድቦ ከመዋረድ የተሻለ አማራጭ ይኑረን!

Ethiopia is talk of the World for its impressive growth


I understand there are foreigners working to insight violence in Ethiopia to turn its faces from its economic development. This is Ethiopia and a foreigner has no place to do so with or without Ethiopian name on facebook.

Ethiopia is the talk of the world because it is making massive transformation. Go Ethiopia do your job, make the economic strides despite whatsoever.

The Horn of Africa is enjoying a wind of promising change. After the surgical military intervention of Ethiopia in Somalia to crack Al Shabaab, IGAD and AU are doing their best to keep it free of terror groups and lasting bloodshed.

Ethiopia is making diplomatic gains to make the sub region strong and go economically growing.

At a time the image of the country and the sub-region is getting changed don't spread sorry stories that don't fit to the context of this day.

we don't have to necessarily talk about bloodshed and sorry stories to become competent opponent.

we have a number of issues to sort out and show our political prowess to the people of Ethiopia.

I understand when we lack competence to do what matters most, we take the low way to speak bad.

Let's take time for deep sole searching to see if we are on the right truck.

So long.

መድረኮች በቅርቡ ያወጡት ማኒፌስቶ


                                                        ዘርይሁን ካሳ

ሀገራችን ክፉኛ የፖለቲካ ምህዳር የመጥበብ ችግር አጋጥሟታል ይላል።
የከፋ የኑሮ ውድነት እንዳለም ማኒፌስቶው ያትታል።
የጤና አጠባበቁም ሰፊ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ ይጠቅሳል።
የእርሻ ስራውም አደጋ እንደተደቀነበት ያመላክታል።
ሙስና አደገኛ በሆነ ሁኔታ እየተንሰራፋ እንደሆነ ለዚህም መፍትሄ እንደሚሻ ያሳያል።
ብሄረሰቦች መብቶቻቸው እንዳልተከበሩላቸው ያትታል።
የትምህርት ስርአቱ ሰፊ ችግር እንደተጋረጠበት የጥራት ችገሩም የከፋ መሆኑን ይገልጻል።
በሀገሪቱ የመሬት ወረራ እየተንሰራፋ እንደሆና ነጻ በሚባል ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ ስለመሆኑ ያመላክታል።
ፍትህ የማጣት ችግር እንዳለና ህገወጥነት እየተንሰራፋ እንደሆነ ይናገራል ማኒፌስቶው።
በዚህ ሁሉ ህዝቡ እንደተማረረና መፍትሄ እንደሚፈልግ በአጽንኦት ይጠቅሳል።

የጓጓሁት ለነዚህ ሀገራዊ ችግሮች የተበጁትን መፍትሄዎችና መድረክ ያ እንዲፈጸም ለማድረግ ያዘጋጀውን ስትራቴጂ ማየት ነበር።
ነገሩ ግን ፍየል ወዲህ ቁዝምዝም ወዲያ ሆነና መፍትሄው ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ሆነ።

የኑሮ ውድነትንና የትምህርት ጥራትን የመሳሰሉ ችግሮችን የሚቀይረው ማጂክ ተጨማሪ ሚንስተሮች እንደኬንያ አባዝቶ ቪላና ቪ8 ማደል ሆኖ አረፈው።

ተቃዋሚነት አማራጭ ፓርቲነት አማራጭ የኢኮኖሚና የፖለቲካ መፍትሄ የማቅረብና የማስፈጸም እንጂ የችግር ጋጋታ ጠቅሶ ስልጣን ካጋራችሁን ጫጫታው ይታገስ ነበር ማለት አደለም።

እቺ ከኬንያ ኮራፕት ፖለቲክስ የተማሯት ፖለቲካል ኦፖርቹኒዝም ትመስላለች።

እኔ እስከሚገባኝ ተጨማሪ ሚንስቴሪያል ቦታዎች መፈጠራቸው ችግሮቹን አይፈቷቸውም። መፍትሄ በምንሻበት ችግር አጋጣሚውን ተጠቅሞ ስልጣን ለመያዝ መሯሯጥ በየትኛውም ሚዛን ትክክል አደለም።

ይቆየን!

Is it our blood or our faulty political paradigm?


Had peoples in Ethiopia not been allowed to govern themselves, I believe many political parties go tell their ethnic people that they are mishandled and sidelined in the politics of the country for much of the political elite that can dominate the scene is from few ethnic groups. 

Don't deny that Ethiopia is ethnically diverse. To accept it as ethnically diverse country isn't bad. To let those nations and peoples administer themselves is to recognize their natural, birth gift right to lead and manage their issues. 

To become united as Ethiopia, to form economically and politically strong country, should Amharas go to the south and take the leadership mettle? Do you expect the Oromo go to somali and lead them? 

Why are we demanding for people to be unnaturally mixed through our tools while the simple thing is to accept them as they are? 

What makes a nation united is not when we get mixed all across the country or that one ethnic group gets leaders from the others. No such scientific or natural fact is out here to claim so. 

What enables any nation to form one economic and political unity is the cause they are tied with, the benefits they maximize when they stand together and the strength they amass as a singular regional and global power. 

That is why countries all around the world seek alliances and unities. 

The base of any political unity is interest not blood, the base of any political and economic unity is historical and cultural realities not how we are situated in the country. Unity can't be justified, I dare to reckon, when one ethnic group is administered by another ethnic group.

We can't change our blood, but I very much believe we can shape our paradigm to make our relations far better than it is now. When relations are mature and composed it is easy to make significant economic progress.

Let's leave our blood to rest in its natural context; rather it is very nice of us to question our faulty paradigms that send shocks through the political landscape.

So long!

Tuesday, April 2, 2013

አቤት ትችት ጠባሾች መፍትሄ ፈብራኪ ብንሆን ኖሮ!


                                                                                                        ዘርይሁን ካሳ
አለምን ሁነኛ በሆነ መልኩ የለወጧት ሀያስያን እና የትችት ጥማት ያለባቸው ቃላት ጠባሾች አደሉም$
አለምን እና ለምተው የምናያቸውን ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ የቀየሯቸው ችግር ስለመኖሩ የተረኩ ሳይሆኑ ችግሮች መኖራቸውን ተገንዝበው የችግሮቹን መሰረታዊ መነሻ ለይተው ተመጣጣኝ መፍትሄ ማበጀት የቻሉ ሰራተኞች ናቸው$ ትጉሀን ናቸው$

በርግጥ ይህን የመሰለ የፖለቲካና የቢዝነስ ስራ ማሳመን ይጠይቃልና ምላሳቸውን ሰዎችን ለማነሳሳት እና መፍትሄ ለማስገኘት ለሚያከናውኑት ስራ አጋር ለማሰባሰብ በታቀደና ሳቢ በሆነ መልኩ ተጠቅመውበታል$ ትችት ለመጥበስ ግን አደለም መፍትሄ እየጋገሩ ስለሆነ ትችት ለማሰናዳት ግዜ የላቸውም$

የተቸገረ ሁሉ መቸገሩንና ችግር መኖሩንማ ያውቃል$ ቁምነገሩ ችግር አለ ማለትና ችግሩ የነከሌ ነው የሚለው የማጥቆር ስራ አደለም$

ቁምነገሩ ችግሩን በቅጡ ለይቶ ለችግሩ መፍትሄ ማበጀት በመፍትሄው ዙርያ የሚመለከተውን የህብረተሰብ ክፍል ማሳመን ማግባባት ለችግሩ መፈታት ለሚከናወነው ስራ የሚያስፈልግ ቁሳቁስና ገንዘብ ማሰባሰብ እና ያንኑ እቅድ በመተግበር መፍትሄውን ማስገኘት መቻል ነው$

የማያምር ፖለቲካ ካለ የሚያምረውን ፖለቲካ አምጣው$ ችግር የማይፈታ ፖለቲከኛ ከበዛ ችግር ፈቺው ፖለቲከኛ ሁን$ ዋሾ ከበዛ ሀቀኛው አንተ ሁን$ ሌባ በበዛበት አንተ ታማኝ ሆነህ ተገኝ$

ወዳጄ ይሄን ሀገር መላእክት አይሰሩልንም$ ይሄን አገር ሌሎች ሰዎች እንዲሰሩልንም አንማጸንም$ ይሄ አገር እንዲያምር መኮን ያለበትን እኔና አንተም መሆን አለብን$

ቢሰራ ጥሩ እንደሆነ የሚታየንን ሌሎች እንዲሰሩት መጠበቅ ሳይሆን እውነቱ የምንጠብቀውን ሆነን መገኘት ነው$ ጠያቂ ከመሆን ከምንጠይቀው ውስጥ የጎደለውን አንዱን ሆነን ተገኝተን ያንን ያክል ጉድለት መሙላት ብንችል በዚህ እንከብርበታለን$

የአርሶ አደሩ ልጅ የገጠሩ ልጅ ያለተማረው ፎርድ ሞተርና መኪና መስራት ከቻለ ጆሮው በአግባቡ የማይሰማለት ያልተማረው እና መምህሩ ደደብ ብሎ የሸኘው ቶማስ ኤዲሰን ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ፈጠራዎች ባለቤት ከሆነ

አንደበተ ጎልዳፋው ቸርቺል ያንን ችግሩን ተወጥቶ አገሩ እንግሊዝን ከጀርመኖቹ ወረራ በጠንካራ መሪነት መታደግ ከቻለ

ለአስርት አመታት በተደጋጋሚ ፖለቲካዊ ጥረቶቹ የወደቁበት ኤብርሀም ሊንከን አሜሪካን በፕሬዝደንትነት ከመምራትም በላይ የጥቁሮችን እኩልነት ማስከበር ከቻለ

ጸሀይ የማይጠልቅባትን ታላቅ ነኝ የምትለውን ብሪታንያን ሳይፈራ ጋንድሂ ታግሎ አገሩን ነጻ ማውጣት ከቻለ ማንዴላ የ28 አመታት እስር ሽባ ሳያደርገው ትግሉን ቀጥሎ ጥቁሮች ላይ የደረሰው በደል ልቡናውን ሳያቆሽሸው በይቅር ባይነት አዲስ አገር ደቡብ አፍሪካን ለመምራት ከበቃ

እኛም አገር ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው ጫካ ገብተው በአመታት ጥረት አደገኛ የነበረውን ስርአት ከቀየሩት

እኔና አንተ ዛሬ የምናያቸውን እጥረቶች ለዚያውም ደም የማይጠይቁ ለውጦች ለማከናወን እውን ምን ይሳነናል?

በኔ እምነት ቁምነገሩ የትችት ናዳ ማውረድ መቻል አደለም$ ቁምነገሩ ዛሬ የተጋፈጥናቸው ፈተናዎች የሚጠይቁትን ብቃትና ክህሎት የሚጠይቁትን ንባብና ትጋት ተላብሰን መፍትሄ አማጭ ሀይሎች የመሆን ያለመሆን ጉዳይ ነው$

አባቶቻችን ላላደረጉት መወቃቀስ ሳይሆን ታሪክ እየጠቀሱ ይህ እንዲህ መሆን አልነበረበትም ማለት ሳይሆን ታሪክ እኛም ትላንት ስንሆን እንዲያው ስለሚመዝነን ዛሬን እንደሚገባን እንኑር$ ዛሬ የሚጠይቀውን የስራና የትጋት ጀግንነት ከፍለን ለተጠራቀሙ ችግሮቻችን መፍትሄ እናብጅ$

የሀገር ፍቅር በትችትና በአቤቱታ ናዳ አይፈታም$ ቁምነገሩ አንተና እኔ የመፍትሄ ሰው መሆን አለመሆናችን ነው$

ትችት ጠባሾችን የመፍትሄ ሰዎች ያድርገን!

ይቆየን!  

ታክሲ ያጣ ተሳፋሪ በተሰለፈባት አዲስ አበባ ስራ ፈቶ የተሰለፈ ታክሲ ማየት ሁለተኛ ክስረት ነው!


                                                                                      ዘርይሁን ካሳ
ዛሬ ጠዋት ወደ ስራ ስገባ ሰርቢሳችንን ስላልተጠቀምኩ ታክሲ መያዝ ነበረብኝ $
ወደ ቦሌ የሚሄድ ታክሲ አጥቼ ከገርጂ የመገናኛ ታክሲ በሽበሽ ስለነበር በዚያ መንገዴን ቀጠልኩ$
መገናኛ ስደርስ ሁለት ረጃጅም የታክሲ ሰልፍ አጋጠመኝና አማራጬን ማሰብ ጀመርኩ$
ከቦሌ በአቋራጭ ካሳንቺስና በሀያሁለት ፒያሳ ነው ባለረጃጅም ሰልፉ$

በመሆኑም የአራት ኪሎ ፒያሳ የብሪታንያ ኤምበሲ መንገድ ሰልፍ ስላልነበረው ያን በአማራጭነት ያዝኩና ወደ አራት ኪሎ አመራሁ$
አራት ኪሎ ደርሼ ከቱሪስት ሆቴል ወደ አምባሳደር ታክሲ ልይዝ ስሄድ የሸወድኩት የመሰለኝ ሰልፍ እዚህ የበለጠ ረዝሞ ጠበቀኝ$

በግምት ስምንት ታክሲ ያክል የሚፈልግ ተሳፋሪ ተሰልፎ እየጠበቀ ነው$ ከ90 እስከ 100 የሚሆን ተሳፋሪዎች ይሆናሉ$ ምንም አማራጭ ስላልነበረኝ በግሬ ከመሄድ ሌላ ቆሞ መጠበቁን ተያያዝኩት$

ምናልባት ወደ 20 ደቂቃ ቆይቼ ተራ ደርሶኝ ተሳፈርኩና ችግሩ በርግጥም እውን የታክሲ ማነስ ነው? እያልኩ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ መንገዴን ቀጠልኩ$

ይሄ እጥረት ካለ ግን ምነው ብር ያላቸው ሰዎች ታክሲ እየገዙ የማያሰማሩት ወይስ ሹፌሩን ወያላውን ተቆጣጥሮ አትራፊ መሆኑ ከባድ ይሆን? በሚል ራሴን እየሞገትኩ አምባሳደር ስደርስ ከፍልውሀ መታጠፍያ ጀምሮ ታክሲዎች ቆመው አያለሁ$

የመጨረሻው ፌርማ አምባሳደር ደርሼ ስወርድ በርካታ ታክሲዎች አፋቸውን ከፍተው ቆመዋል$
በግርምት ከላይ ከፍልውሃ መታጠፍያ ጀምሮ የቆሙትን ታክሲዎች አምባሳደር መዝናኛ አካባቢ እስካሉት ድረስ ቆጠርኳቸው$

16 ታክሲዎች አፋቸውን ከፍተው አምባሳደር ቆመው ቱሪስት ሆቴል ላይ መቶ የሚሆን ሰው ተሰልፏል$
ሌላው ቢቀር ከፊሎቹ ታክሲዎች ቱሪስት አካባቢ እንዲቆሙ ከፊሎቹ ከአምባሳደር እንዲነሱ በማድረግ ተሳፋሪውም ባለሀብቱም መጠቀም አይችሉም ነበር?

ባለንብረቶቹስ አፋቸውን ከፍተው ታክሲዎቹ ከሚቆሙ በዚህ መልኩ እንዲደራጁ ማድረግ ይሳናቸዋል?
ትራንስፖርት ቢሮና ባለንብረቶቹ አይታያቸው እንበል ሹፌሮቹስ ይህን ማስተዋል ተሰኗቸው ነው?
እሺ ይህም ይቅር ያለምንም በቂ ተግባር በየታክሲ ተራ ተገትረው ብር የሚሰበስቡ ወጣቶች እቺን ታክል እንኳ አስተዋጾ ማበርከት ተስኗቸው ነው?

ይሄ የምር እጅጉን  የወረደ የስራ እና የአገልግሎት ስርአት እንዳለን የሚያመላክት እኮ ነው$ ቢያንስ ያለውን እንኳ ከወዲህም ከወዲያም ከመነሻም ከመድረሻም ማስቆም አይቻልም ማለት ነው?
አዲስ አበባ መስተዳድር የትራንስፖርት ቢሮውን በአግባቡ ሊያየው ይገባል$ ቢያንስ የሚያንሰው እስኪሟላ ባለው የተሳለጠ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ አይቻልም እንዴ?

ሁሌ ላልተሳካ ስራ ሰበብ ከመደርደር እንዲህ ያሉትን የተበላሹ የመነሻና የመድረሻ ቦታ አነሳስ እና አካሄድ መልክ ማስያዝ የሚቻል ይመስለኛል$
ተመሳሳይ ነገር ከካሳንቺስ ቦሌ መድሀኔ አለም እና ቦሌ ድልድይ መንገድ ይሰተዋላል ቦሌ ድልድይ መኪና ይሰለፋል ካሳንቺስ ተሳፋሪ ይሰለፋል$ እውን እቺን ታክል መፍትሄ ማሰብ ከብዶ ነው?ወይስ የግብር ይውጣ ስለሚሰራ?

ተመሳሳዩን ሌሎች ተሳፋሪዎች በየአካባቢያቸው ሊያነሱት እንደሚችሉና እንደሚኖር እርግጠኛ ነኝ $
እባካችሁ ቢያንስ ያሉትን ታክሲዎች በአግባቡ ማሰማራት ቢቻል ባለንብረቶቹም መኪናዎቻችሁ ከሚቆሙ ሊሰሩ የሚችሉበትን የተሻለ አደረጃጀት ብትከተሉ$

ይቆየን!