ዘርይሁን ካሳ
ሀገራችን ክፉኛ የፖለቲካ ምህዳር
የመጥበብ ችግር አጋጥሟታል ይላል።
የከፋ የኑሮ ውድነት እንዳለም ማኒፌስቶው
ያትታል።
የጤና አጠባበቁም ሰፊ ችግሮች ያሉበት
እንደሆነ ይጠቅሳል።
የእርሻ ስራውም አደጋ እንደተደቀነበት
ያመላክታል።
ሙስና አደገኛ በሆነ ሁኔታ እየተንሰራፋ
እንደሆነ ለዚህም መፍትሄ እንደሚሻ ያሳያል።
ብሄረሰቦች መብቶቻቸው እንዳልተከበሩላቸው
ያትታል።
የትምህርት ስርአቱ ሰፊ ችግር እንደተጋረጠበት
የጥራት ችገሩም የከፋ መሆኑን ይገልጻል።
በሀገሪቱ የመሬት ወረራ እየተንሰራፋ
እንደሆና ነጻ በሚባል ዋጋ ለውጭ ባለሀብቶች እየተሰጠ ስለመሆኑ ያመላክታል።
ፍትህ የማጣት ችግር እንዳለና ህገወጥነት
እየተንሰራፋ እንደሆነ ይናገራል ማኒፌስቶው።
በዚህ ሁሉ ህዝቡ እንደተማረረና
መፍትሄ እንደሚፈልግ በአጽንኦት ይጠቅሳል።
የጓጓሁት ለነዚህ ሀገራዊ ችግሮች
የተበጁትን መፍትሄዎችና መድረክ ያ እንዲፈጸም ለማድረግ ያዘጋጀውን ስትራቴጂ ማየት ነበር።
ነገሩ ግን ፍየል ወዲህ ቁዝምዝም
ወዲያ ሆነና መፍትሄው ብሄራዊ የሽግግር መንግስት ማቋቋም ሆነ።
የኑሮ ውድነትንና የትምህርት ጥራትን የመሳሰሉ ችግሮችን የሚቀይረው ማጂክ ተጨማሪ ሚንስተሮች እንደኬንያ አባዝቶ ቪላና ቪ8 ማደል ሆኖ አረፈው።
ተቃዋሚነት አማራጭ ፓርቲነት አማራጭ
የኢኮኖሚና የፖለቲካ መፍትሄ የማቅረብና የማስፈጸም እንጂ የችግር ጋጋታ ጠቅሶ ስልጣን ካጋራችሁን ጫጫታው ይታገስ ነበር ማለት አደለም።
እቺ ከኬንያ ኮራፕት ፖለቲክስ የተማሯት
ፖለቲካል ኦፖርቹኒዝም ትመስላለች።
እኔ እስከሚገባኝ ተጨማሪ ሚንስቴሪያል
ቦታዎች መፈጠራቸው ችግሮቹን አይፈቷቸውም። መፍትሄ በምንሻበት ችግር አጋጣሚውን ተጠቅሞ ስልጣን ለመያዝ መሯሯጥ በየትኛውም ሚዛን
ትክክል አደለም።
ይቆየን!
No comments:
Post a Comment