Friday, April 19, 2013

̋ወያኔ ኢህአዴግ ካልጠፋ መከራችን አያበቃም̋ ̋




የወያኔዎቹ ፓርቲ ኢህአዴግ ካልጠፋ በቀር አገራችን ኢትዮዽያ መከራዋ የሚያበቃላት አይሆንም። የኛ የተቃዋሚዎች ዋናኛው ስራችን ችግሩን የሚፈቱ አማራጭ መፍትሄዎች ማጠናቀር ሳይሆን ኢህአዴግን መጣል መሆን ይኖርበታል።
 
በርግጥ ችግር የሚፈቱ መፍትሄዎች በማቅረብ ረገድ የረባ አማራጭ ማቅረብ የተሳነንም ቢሆን ተቃዋሚዎች ተረባርበን ኢህአዴግን መጣል ዋናው ስራችን ዋናው ግባችንም መሆን አለበት።

ይገባኛል እንዲህ ያለውን ኢህአዴግን የመጣል አጀንዳችንን ፍጻሜው የማይታወቀው ስርአት ወይም ለበለጠ አመጽ የሚያነሳሳ ሁኔታ መጀመርያ አድርጋችሁ እንደምትቆጥሩት እረዳለሁ። ለዚሁ ማረጋገጫ አድርጋችሁ የምታቀርቡት ደግሞ በተቃወሚ ፓርቲዎች መካከል ያሉትን የማይታረቁ ልዮነቶች ነው። አንዳዶቹ እንዳውም የኛን የተቃዋሚዎችን ህብረትና ስብስብ መቼም መጣጣም እንደማይችል የእንቧይ ካብ እንደሚያዩት አውቃለሁ።

የሆነ ሆኖ የተቃዋሚዎቹ ውል አልባ ጋብቻ ምንም ሆነ ምን በነዚህ ፓርቲዎች ምክንያት የሚፈጠረው ጣጣ ምንም ይሆን ምን የኢህአዴግን ግብአተ መሬት በተቻለን መንገድ ሁሉ ማፋጠን አለብን። ይህን አፋኝ ፓርቲ ይሄን ገዳይ ፓርቲ ይሄን የሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት ጨፍላቂ ፓርቲ ማስወገድ ዋናው ስራችን ሊሆን ይገባል።

ይህን ማድረግ የቻልን እንደሆነ ነው የዚህ አገር መጻኢ እጣ ፈንታ አንጸባራቂ ተስፋዎች የሚኖሩት። ሀገር እንዴት ይመራል ፓሊሲያችን ምን ይሆናል ብሄር ተኮርና ሌሎች ፓርቲዎች ምን አስታራቂ መስመር ይኖረናል የሚለው ዝብርቅርቅ ስንደርሰ የምንጣድበት እንጂ ዛሬ የሚያሳስበን አይሆንም።

ዋናው ችግር አሁን ከኢህአዴግ የተሻለ ወይም ባይሻልም በአግባቡ የተደራጀ አማራጭ አለመኖሩ አደለም። ይልቅ አደጋው ኢህአዴግ ነው። አፋኝ፣ አገር ገንጣይ፣ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ ሙሰኛ፣ ገዳይ፣ አሳሪ እና ሌላም የሆነውን ድርጅት ማውገዝና መጣል ነው ቁምነገሩ።


ድህነት እንዴት በተጨባጭ ይወገዳል? የአገልጋይነት መንፈስ እንዴት ይዳብራል? ኢኮኖሚው እንዴት የላቀ አፈጻጸም ይኖረዋል? ዜጎች እንዴት ልማታዊ እሴቶች ይኖሯቸዋል? የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለመመለስ ትልቅ ጉዳይ አደለም። አማራጭ በመሆን አለመሆናችን ላይ ችግር ቢኖረውም ለዛሬ መላ አቅማችን ማተኮር ያለበት ኢህአዴግን ሊያጣጥሉ በሚችሉ ወቀሳዎች እንጂ ለተጨባጭ ችግሮቻችን መፍትሄ በማፈላለጉ ላይ መሆን የለበትም።

ወያኔ ቤተመንግስት እያለ አማራጭ ቢኖረን እንኳ ተቃዋሚዎች ያንን አማራጭ ማቅረብ የምንችልበት ሚድያ የለም። ቢኖርም ህዝቡ ሊመርጠን ቢፈልግ እንኳ ወያኔ በተለመደ አፈናው የህዝቡን ምርጫ ከማምታታት ወደ ኋላ እንደማይል ይገባኛል።

ስማንጂ የተቃዋሚ ፓርቲ ውበትና ጥንካሬ እንዲህ አይነቱን ደንቃራ ሁሉ አልፎ በአማራጭ ፓሊሲም በዲሲፕሊንም ልቆ በህጋዊ አመራጭ ማሸነፍ አደለም ወይ? የሚል ጥያቄ እንደሚነሳ እረዳለሁ። ሀሳቡ የሚካድ ባይሆንም በዚህ አማራጭ መሄድ በርካታ አስርት አመታት ግማሽ ክፍለ ዘመን አለያም አንድ ክፍለ ዘመን ሊወስድ ስለሚችልና ኢህአዴግ ይህን ያክል ግዜ በስልጣን አንዲቆይ ስለማንፈቅድ በማንኛውም አማራጭ ወያኔን በአጭር ግዜ መጣል  አለብን በሚል ጥድፊያ ተወጥረናል።

በርግጥ ይሄ ኢዴሞክራሲያዊነት አደለም ወይ? የዲሞክራሲ ሙርከኞች ከሆናችሁ የወሰደውንም ግዜ ቢወስድ ለምንድነው በህጋዊ መንገድ በጠንካራ አማራጭ የመርታት አማራጭ የማትወስዱት የሚል ተገቢ ክርክር እንደምታነሳ አልስትም። ለግዜው ያንን ህሊናዊ የስነምግባር ጥያቄ ትተን በእኔ እምነት ወያኔ ኢህአዴግን በማንኛውም አማራጭ በፍጥነት ልናስወግደው ይገባል የሚል እምነት አለኝ።

አንተ ሁሌም ታጋይ እኮ በትግሉ ሂደት ባጋጠሙት መሰናክሎች አቅሙ ይበልጥ እየጎለበተ አማራጭ ፖሊሲዎቹ ይበልጥ እየዳበሩ በብስለታቸው መጠን ተቀባይነት እያገኙ በዚያው ሂደት በጠንካራ ስነምግባር የሚመራ የፖለቲካ ድርጅት እና አመራሮች እየፈሩ ይሄዳሉ የሚል ቅኝት አለህ። 

በዚህ መልኩ የማይመራ የፓርቲ ፖለቲካ ስልጣን በማንኛውም አማራጭ በአፋጣኝ ለመያዝ የሚጣደፍ የተቃውሞ ፖለቲካ በመሆኑ በሳል መድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በመፍጠር ረገድ የሚኖረውን ሁነኛ ሚና ያመክናል የሚል እምነት እንዳለህ እረዳለሁ። ኢህአዴግን ከዚህ በላይ ልንታገሰው ስለማንችል ለግዜው ይህን አማራጭ መከተል አለብን ብዬ አላምንም።

እርግጥ ነው በዚህ መልኩ መሄዳችን በጠቀስከው መልኩ ታግለን ቢሆን ኖሮ ዴሞክራሲያዊ ስርአቱ ሊጎናጸፍ የሚችለው ብስለት እና ለውጥ የጎላ አንደሚሆን ይታመናል። የሆነ ሆኖ ዴሞክራሲያችን በተፈጥሮ ባህሪው እንዲያድግ ስንሰራ እና በዚያ መልኩ ሁኔታዎች የምንመኛቸውን እስኪሆኑ ድረስ ኢህአዴግ ወንበሩን ለተጨማሪ አመታት እንዲያመቻች ማድረግ በመሆኑ ለግዜው ብንተወው የሚሻል ይመስለኛል። ኢህአዴግ በየቀኑ የሚያገኘው የመሪነት እድል ያንገበግበኛል እንደሚፈጽማቸው ከማውቃቸው ግፎች አንጻር።

ይሄን የሚያጫውተኝ የማከብረው የሚያከብረኝ በፖለቲካ እምነቱ ግን የማይመስለኝ የኢህአዴግ ተቃዋሚ የሆነ ወዳጄ ነው። ሀሳቡን አከብራለሁ። ሀሳቦቹና አቋሞቹ የሚያሳብቁትን የተዛነፉ መርሆች ግን አምርሬ እቃወማለሁ።

ይህን አስተሳሰብ ከዴሞክራሲያዊ እሴቶች አንጻር እንድትመዝኑት ለናተ ፍርዱን ልተው።

Wednesday, April 17, 2013

Why not us? Why always the unable government?

Why are we reluctant to exhaustively use our constitutional rights? why do we always expect government to do all for us while we know it just can't?

Why don't our opposition parties, despite whatsoever, become competent enough winning every crippling mechanism through legal means and be reliable alternative in the country's weak multi party system?

Why is the opposition weak enough even to write a credible and authentic policy documents though opportunities to air it out is limited? why do the opposition engage themselves in the limited airtime insulting EPRDF than showing their alternative policy and discipline?

Are CSO organizations meeting their objectives? Or are they becoming charities for those running them than for whom they are intended to?

Does the west send us charities for they are worried about the democracy we are in or are they using them as a tool to weaken governments when they go against the choice of the west?

Who say charities are angel like institutions? isn't fair to doubt them like we doubt even state apparatus?

Why are we, all of us, afraid to speak frankly, responsibly and respectfully like we demand from ETV?

IS not ETV a reflection of who we are than not?

Should an Ethiopian work to change ETV or hate it? Why do we fail to read and listen our opponents?

I believe it is a sickness we all share than the government alone. Is there a better way, alternative way to speak frankly and responsibly?

If not let's engage ourselves in ways this country we love expects us to. Whether it is good or bad it is Ethiopian government. What matters is not to hate; what counts is to work to better it through every constitutional way.

Sunday, April 14, 2013

የሀገር ፍቅርና ተቃውሞ‐ አዬ ኢትዮዽያ


ኢትዮዽያዬ ይሄውልሽ ተሳዳቢና አዋራጅ ካልሆናችሁ የሀገር ፍቅር የማይገባችሁ ሆዳሞች ሌቦች ናችሁ እየተባልንልሽ ነው

ሀገር ለመውደድ ወይ ወያኔ ይጥፋ እያልን መለፈፍ አለብን ወይም ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀን አሜሪካ ገብተን ኢህአዴግ ሲወድቅ የመሪነቱን ሚና የሚቀበል መንግስት ማቋቋም አለብን

አለሜ ይሄውለሽ ያንቺ ልጆች ሀገር ወዳድ ለመባል ያለን እጣፈንታ ገ¸ውን ፓርቲ ኢህአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖ አረፈልን

በቃ አንቺን ለመውደድ ያንቺኑ ፍጡራን ካልጠላን የአብራኮችሽን ክፋዮች ካልተጠየፍን የማይሆን ስለመሆኑ ወዳጆቻችን ሌት ተቀን ይሰብኩናል

እማማ እውን መውደድ መጥላትን የግድ ይላል? እውን ያንቺን ችግሮች ለመፍታት መታገል እነሱ የምንላቸውን የኛን የሀገር ልጆች ውድቀት ማፋጠን የግድ የሚል ነው?

እማማዬ በይዘት መወዳደር በአማራጭ መሸናነፍ አንሶ ነው ፖለቲካችን እንዲህ በጥላቻ በታወረ ትንታኔና ልማድ የተወጠረው?

ደግሞኮ የዲሞክራሲን አስፈላጊነትና የነጻ ሃሳብን ጠቀሜታ የሚሰብኩን ናቸው ይበጃል የምንለውን ሀሳብ ስላራመድን ሌቦች ሆዳሞች ባንዳዎች የሚሉን

እውን አለሜ በገዛ ነጻነታችን የፈለግነውንና ያዋጣናል ያልነውን አቋም ልናራምድ የማያስችለን ከሀዲነት ምን ይሆን? አገርስ መውደድ በአንድ ከረጢት ተቋጥሮ ለአንድ ጎራ የተቃውሞ ወይም የድጋፍ ቡድን የሚሰጥ ነው?

አፍ ካለሽ ተናገሪ አንቺ አገር እየጠየኩሽ ነው? አሁን ማን ይሙት ሀገር ጥላቻ ማገርና ቋሚ ሆኖ ይገነባዋል? አሁን ማን ይሙት ሀገሬ ልጆችሽ በሚያምኑበት ይዘት ትንታኔና ብስለት መሸናነፍ ተስኗቸው ነው አንዳች የጥላቻ ዛር ሲተፉ የሚውሉት?

እውን አንቺስ አገር በዚህ መሰሉ የጥላቻ ዝማሬያችን ያገኘሽው ጥንካሬ አለያም የኳልንሽ ውበት አለ  ይሆን? ነተረኩሽ አደል ግዴለም ልጠይቅሽ ግድየለም ልጨቅጭቅሽ

አለሜ አንዳንዴ ግርም ይለኛል! ምን መሰለሽ ልጆችሽ ዴሞክራሲን ከሚያጣጥሙትም ሀገር ለረጅምም አመት ተቀምጠው ሰከን ብሎ ተከባብሮ መነጋገር ይሳናቸዋል እንዲያው ምን ይሆን ምክንያቱ ባክሽ?

እማማዬ አዋራጅ የንግግር እና የውይይት አማራጭ ተጠቅመው ሲናገሩ እያየናቸው የሚኖሩባት አሜሪካና የሚኖሩበት አውሮፓ ዲሞክራሲያዊ ልምድ ያልገባቸው መሆኑን እንዲህ ያለው ተግባራቸው እያሳበቀባቸው ምንም ባለማፈር እናት አገር አዋረድናቸው ብለው ዝና ሊሸምቱ ሲሞክሩ እንታዘባለን 

እማምዬ መጽሀፍ ክብራቸው በነውራቸው ነው የሚለው ለኛ ይሆን እንዴ? አንቺ አገር እውን የኛ በዚህ ደረጃ ለመነጋገር አለመፈለግ የዚህን ያክል የተንፈራቀቀ አቋም መያዝ የኛ የዚህን ያክል መዘላለፍ ጌጥ ይሆንሽ ይሆን? እውን የጎደለው ጓዳሽ እውን የገረጣው ፊትሽ ይህን በመሰለው ልማዳችን ያምርበት ይሆን?

እኮ ማነው የሀገር ፍቅርን በየጎራው እየለየ እቺ የተቃዋሚ እቺ ደግሞ የደጋፊ ናት እያለ የሸነሸናት? እኮ ማነው ሀገሬ እንዴት ላፈቅርሽ እንደሚገባና እንደማይገባ ፍቃድ የሚሰጠኝ?
እኮ ማነው ያንተ ፍቅር ጎዶሎ ነው ብሎ ካበቀለኝ ምድር የሚነቅለኝ? እኮ ማን የማይናወጥ የመፍረድ ስልጣን ቸሮት ነው እኔ እንጂ አንተን ብሎ ባላገር ፍቅር የሚለኝ?

አንቺ የፈለግሺው አፈርሺን የሚያበቅሉባት አራሹን ገበሬ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ደሀ አሰራሩን የሚያሻሽሉለት ላቡን ሳይጠየፉ አመለካከቱን ሳያጣጥሉ የቀረውን የሚሞሉ ጎበዞች ነው? ወይስ የወሬ አርበኞች እኮ አፈርሽ በስድብ ፈብራኪዎች ሊታረስ ነው?

ወይስ ስራ አጡ ወጣት በአፍ እላፊ የፈጠራ ብቃቱ ሊሻሻል ነው ይሄ የፖለቲካ ምህዳር እንዲህ በጥላቻ ስድብ እና አሉባልታ የሚናጠው? እናት አለም እዚህ አገር ትልቁ ቁምነገር መጠላላት እና መወራረድ ሆነ እውን ጌጤነው በርቱልኝ ፍቅራችሁን በዚህ ግለጡልኝ ብለሽን ነው?

እኔ ሲገባኝ አንቺ የሚያምርብሽ በርግጥም ረሀብሽን የሚያስታግስ እርሻ አዎን የወጣቶችሽን ሀብት የመፍጠር አቅም የሚያጎለብት ብቃት የባለሀብቶችሽን ቢዝነስ የሚያፈረጥም ምቹ ሀኔታ የተማሪዎችሽን ብቃት የሚያንጽ ጥራት ያለው ትምህርት ተግባር እንጂ እውን አሁን ያንቺን ድህነት ተረብና ዱላቀረሽ መወራረድ ሊፍቀው ነው?

አንቺ አገር ምነው አፍ አውጥተሽ ሀገር በበሰለ ፕሮግራም ሀገር በጠንካራ ዲሲፕሊን እንጂ በጥላቻ በታጨቀ ተረብ እንደማይታነጽ ብትናገሪ?

እማማዬ ምንም ይሁን ምን ያው ልጆችሽ ስለሆን በዚያም በኩል ያለውን ወንድሜን እኔም በዚህ በኩል ሆኜ እማወራውንም ልጅሽን ለመማር አንቺን በተግባር በሚረባው አስተዋጾ እንድንወድሽ እድሉን አትንፈጊን!

የለም የለም አገር መውደድ መቃወም አገር መውደድ መደገፍ አደለም$
አገርማ መውደድ አለሜ የሚጠቅመውን የሚበጀውን አስተዋጾ ማበርከት ነው$ አገሩን የሚወዳት አስተዋጸው ይመስክርለት አገሩን የሚወዳት በሚወደድ ተግባር ያንጻት$

የግሉ ፕሬስ ቁማርተኞች


ሲጀመር በግሌ የትኛውም ሚድያ ከፖለቲካ አቋምና ከትላልቅ ቢዝነሶች ተጽእኖ ውጭ ይሆናል የሚል ቅqት የለኝም$ ሆኖም አያውቅም$ ዛሬም በአለም ላይ ያሉ ሚዲያዎች ከዚህ መሰሉ ተጽእኖ ውጭ አደሉም ለመቼውም እሚሆኑ አይመስለኝም$

በገዛ ፈቃዱ ራሱን ነፃ እያለ የሚጠራው አብዛኛው የግል ፕሬስ ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮዽያ ራሱን የለየለት ተቆርቋሪ አድርጎ ይቀርጻል$ ለሀገሩ በርግጥም ተቆርቋሪ ሆኖ ከሆነ ደስ ይላል$ እውን በቁምነገሩ ለሀገሩ ተቆርቋሪ ነው ወይ?

ሁሉም የግል ፕሬስ በዚህ የሚተች ባይሆንም በርግጥ የሚለፍፉትን ያክል እነዚህ የግል ፕሬሶች የሀሳብ እና የአቋም ነጻነት አላቸው ወይ በሎ መጠየቅ ይገባል$ ስንኳንስ የተለያዩ ፓርቲዎች የሚያቀነቅኑትን አቋም ገለልተኛ ሆነው ሊያቀርቡ ይቅርና ከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ልቀው የተቃውሞ ፖለቲካው አብይ አቀንቃኝ ናቸው$

የለየላቸው የተቋውሞው ፖለቲካ አካል ሆነው ሲያበቁ እዚያው ሳሉ እነሱው ተመልሰው የነጻ ፕሬስ ተቋርቋሪ ነን ያለኛ ነጻነት የገባው ማን አለ በሚል ስብከት ያደነቁሩናል$ እኔ እስኪገባኝ ድረስ አንድ ፕሬስ የገ¸ው ፓርቲ ሁነኛ ተቃዋሚም ነጻ ሚዲያም የመሆን ቁመና ፈጽሞ ሊኖረው አይችልም$

አንዳንዴ እገሌ የጋዜጠኝነት ምልክት ነው ብለው የሚነግሩን ግለሰብ ያሻውን ሀሳብ የመግለፅ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የጋዜጠኝነት ቀንዲል ነው ከሚሉን የተቃውሞው ጎራ አፈቀላጤ ወይም ህዝብ ግንኙነት ነው ቢሉት ይሻላል$

እንዳለመታደል ሆኖ ኢቲቪን በመንግስት ቃላቀባይነቱ የሚያብጠለጥለው ነጻ ሀሳቢና ጸሀፊ ሁሉ የተቃውሚው ማውዝ ፒስ የሆኑትን የግል ፕሬሶች ጎበዝ መረጃ ሳታዛቡ አቅርቡልን አይላቸውም$ በኔ እምነት እንዲህ አይነቱ የግል ፕሬስ ኢቲቪን ለመሰል ድርጊቱ ሊተቸው የሚችልበት የሞራል የበላይነት የለውም$ የራሱን የቤት ስራ ስላሰራ$

ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ገጻቸው ገ¸ውን ፓርቲ በሚያብጠለጥል ጽሁፍ የተሞሉት የተቃዋሚው ጎራ አፈቀላጤ ጋዜጦች ደርሰው በዚያው ቁመናቸው ኢቲቪን በመንግስት አፈቀላጤነት ይወቅሱታል ኢቲቪ መንግስት ስለሚያስተዳድረው አፈቀላጤ ሆነ እንደሚነግሩን ነጻ ከሆኑ ምን ይዟቸው ነው ወዲህም መንግስትና ኢህአዴግን ወዲያም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በተመሳሳይ ትጋት የማያብጠለጥሉት እውን ማብጠልጠል የላቀው የጋዜጠኝነት ሚና ከሆነ$

ነጻ ናቸው በሚል የዋህነት አደለም ጥያቄውን እያነሳው ያለሁት$ ነን ስለሚሉን መሆናቸውን በስራቸው ያስረዱን ዘንድ ብቻ ነው$ እኔ ነጻ ነኝ የሚባል ቅራቅንቦ አይገባኝም ሁላችንም አቋም አለን$ አቋም አለመያዝም አቋም ነውና$

በቀላል አገላለጽ እኚህ ጋዜጦች የሚሉንን ያክል ነጻ ቢሆኑ ኢህአዴግን ይህን ያክል ለመተቸት ባልፈራው ድፍረታቸው ተቃዋሚዎችን በተከታታይ በተቹ ነበር$ የሆነ ሆኖ ካፈጣጠራቸው የተቃዋሚው ህዝብ ግንኙነት በመሆናቸው ይህንን ሊያደርጉት አይችሉም$

እውን ለሀገሩ የሚቆረቆር ሚድያ በወጉ በመከባበር መንፈስ እንኳ ውስጠ ፓርቲ ስብሰባዎችን መምራት የተሳናቸውን ፓርቲዎች እንኳንስ ሀገር ልትመሩ ይቅርና በአንድ ፓርቲ ዙርያ የተሰባሰባችሁት አመራሮችም ተግባብታችሁ መስራት አልቻላችሁም ሊላቸው ይገባል

እውን ሚድያው ለሀገሩ የሚቆረቆር ቢሆን ምንም የማይመሳሰል ፖለቲካዊ አቋም ሳይኖራቸው በምርጫ ሰሞን የሚሰባሰቡ የፓርቲ እድሮችን ጎበዝ ራሳችሁን ቆም ብላችሁ እዩ ምርጫውን ብታሸንፉ በማን የፖሊሲ እምነት ሊሰራ ነው የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ደካማ ውል የምታስሩት ብሎ ሊወቅሳቸው ይገባል

እንደሚያደነቁረን አብዛኛው የግል ሚድያ የተቃውሞው ፖለቲካ አብይ አካል ካልሆነ የፓርቲያቸውን ውስጣዊ ስብሰባ ሚስጢራዊነት እንኳ የማይጠብቁ አመራሮች ዲስፕሊን አልባነት ለምንድነው የማይኮንነው? እኮ በዚህ ቁመና ነው በከፍተኛ ምስጢር መጠበቅ ያለባቸው ብሄራዊ ጉዳዮች ያሉበትን ሀገር የመምራት ስራ ይህን ለመሰሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮች የምንሰጠው? እኮ ለነጻ ሀሳብ የቆመው ሚድያ የት ጠፍቶ ነው ይህን የመሰለውን የሰለለ ቁመና ገላልጦ የማይጽፈው?

ሌላ ምንም ምክንያት የለውም$ በአንድ በኩል የተቃውሞው ጎራ ሁነኛ መሳርያ ስለሆነ$  ይህን ሀቅ ምንም ያክል መሀላና መገዘት ሀሰት አያደርገውም$ በሌላ መልኩ ይሄ ነጻ መረጃ የማቅረብ ቁርባን ቀምሻለው የሚለው ሚድያ ገበያውን ለማጧጧፍ በሬ ወለደ ዜናና ግነት ይጠብሳል$ ይሄን ቁመናውን ይረሳና በሀገር ፍቅርና በነጻ ነኝ መሀላው ሊያደነቁረን ይሞክራል$

የሚሻለው በስፋት በአሜሪካ ሚድያ እንደተለመደው እኔ የዚህ የፖለቲካ ቡድን እና ፓርቲ አቀንቃኝ ነኝ ብሎ በዚያው ፍልስፍና ዙርያ የበሰሉ ጽሁፎች ማውጣት እንጂ ባንድ በኩል ገ¸ውን ፓርቲ በሚገባም በማይገባም ምክንያት ማጣጣል በሌላ ገጹ ደግሞ መረጃ ለማድረስ ብለን ነው እንጂ እኛ ነጻ ነን ማለት ተረት ሊሆን ቢችል እንጂ እውነታውን የናንተም ህሊና የኛም ያውቀዋል$

በመሆኑም እንዲህ ያለው ጋዜጠኛም መባል ያለበት የነጻ ጋዜጣ ምልክት ሳይሆን የሚደግፈው የተቃውሞ ቡድን አስተሳሰብ አቀንቃኝ ብቻ ነው$ ለምሳሌ በአሜሪካ ፎክስ ኒውስ የሪፐብሊካኑን አቋም በአዋጅ በግልጽ ያራምዳል$ MSNBC በበኩሉ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን አቋሞች ያራምዳል ተብሎ ይታመናል$ ሲኤንኤን ደግሞ ሚዛናዊ ዜና ለማቅረብ ይሞክራል ሆኖም በተወሰነ ደረጃ ግራ ዘመም ነው የሚል ወቀሳ ይሰነዘርበታል$

በኔ እምነት አንድም ለይቶልን እንደነዚህ ሚድያዎች የፖለቲካና ኮርፖሬት አጀንዳዎችን ማራመድ አለያም ሲኤንኤን እንደሚያደርገው ጥቂት ሚዲያዎችም በኛ አገር እንደሚያደረጉት መሀሉ ሜዳ ላይ መጫዎት ብንችል ነው እሚሻለው$

እንደኔ እንደኔ ጭልጥ ያለ የፖለቲካ አጀንዳ እያራመደ ያለ ሚድያ በምንም መስፈርት ለነጻ ሀሳብ ተቆርቋሪ ስለሆንኩ እና የሀገር ፍቅር ስላለኝ ነው ቢለን ሊገባን አይችልም$ የሚሻለው ይህን አቋም የማራምደው የዚህ ፖለቲካ ድርጅት አቋም ለሀገሬ ይበጃታል ብዬ ስለማምን ነው ቢባል ነው$

በአስሩም ጣታቸው የለየለት የተቃዋሚ ጎራ አቋም እያራመዱ (ማራመድ መብታቸው ነው) እኛ ከየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አቋም እጃችንን የታጠብን ነን ማለት ቀልድ ነው$ በአንድ እግር አገር ወዳድ ነጻ ጋዜጠኛ በሌላው ደግሞ የተቃውሞ ፖለቲካው ጠበቃ መሆን አይቻልም$
ጋዜጠኛ የፖለቲካ አቋም ሊኖረው ይችላል$ ያንን የፖለቲካ አቋሙን አራምዶ ሲያበቃ ግን የለም የለም የፖለቲካ አጀንዳ የለኝም እኔ የማንኛውም ሀሳብ በነጻ መነገር ጠበቃ ነኝ ብሎ መቅረቡ የዋህነቱ ነው ሀቁ አደለም$

አንድም ለይቶልን የፖለቲካ አቋማችንን አውጀን እንስራ አለያ በተጨባጭ በተቻለ መጠን ገለልተኛ ሆነን እንቀጥል$ ነጻ ነኝ እያሉ መቆመሩ የትም አያደርስም$

Friday, April 12, 2013

ተቃዋሚን ጀግና ደጋፊን ሆዳም ማን አደረገው?


የኛ አገር ቅጥ አንባሩ የጠፋው የፖለቲካ ምህዳርና ሚድያ ጫፍ የረገጠ ተቃዋሚ ወይም አሜን አሜን ባይ የበዛበት ነው$

በዚ መሀል መንገድ አይታየውም$ መሀለኛውን መንገድ መሀል ላይ ያለውን በርካታ አማራጭ ለመመዘን እና ለማቅረብ ግድ አይለውም$ መራገጥ ብቻ ይመስላል ቁምነገሩ$
ነፃነት ለኛ ሀገሩ ሚድያ መዋሸት መረጃ መፍጠር መሳደብ ያዙኝ ልቀቁኝ እንጂ የበሰለ እና ሀብት መፍጠር የሚችል መረጃ ማቅረብ ይሳነዋል$

ከዚህ የራቀው ሌላኛው አማራጭ ደግሞ አጨብጫቢ አድርባይ የበዛበት ለሰከኑ ውይይቶች እና የሀሳብ ልውውጥ ሳይሆን ለመሞጋገስ የተፈጠረ የሚመስል በአመዛኙ አስመሳዮች ለወቅታዊ ትርፍ የሚሰበሰቡበት ጎራ ነው$

ወዲያ ተሳዳቢ ወዲህ ደግሞ አድናቂ$ ያኛው የፈጠጡ ስኬቶች የማይታዩት ከሀዲ ይሄኛው ደግሞ የዋሉ ያደሩ እጥረቶችንና ችግሮችን የሚክድ ልብ አውልቅ$ ያኛው በስድቡ ጋጋታ ጀግና ሆኖ ለመታየት የሚጥር አድርባይ$ ይሄኛው ደግሞ በማሞካሸት ጥቅም ማግበስበስ የሚሻ አድርባዮች ናቸው$

አንዱ ጀግና መባል ሆዱን ብልት አድርጎት የቆመውን ሁሉ ለመጣል በመሞከርና በማዋረድ ጀግና ሆኖ ለመገኘት የሚጥር ጅብ$ ሀገራዊ ግቦቹን ዳር በማድረስ ሳይሆን የሚቃወማቸውን የመጣል ብቻ ጂኒ ያለበት አተያይ ባለቤት$ ለሱ እሱና እንደሱ ያሉ ተሳዳቢዎች ካልሆኑ በቀር ጀግና የለም$

የሚቃወመውን አካልና ደጋፊዎቹን የመርገምት ጨርቅ ያክል ያረክሳቸዋል$ እሱ የሚቃወመውን የደገፉ ሁሉ እውራን ሆዳሞች ሌቦች ለጥቅም የተረቱ ጅቦች ናቸው$ ላለመሆናቸው ማረጋገጫው እንደሱ መሳደብ ብቻ ነው$

ሌሎች መሳደብም ማስመሰልም ጠልተው የተቀመጡት ደግሞ ፈሪዎች ናቸው በዚህ ሰው የቃላት ማውጫ ዝርዝር መሰረት$ መንገዱ ወይ መሳደብ ወይ መሰደብ ብቻ ነው$ በመሀሉ ምንም የለም$ ልክ እንደ አንድነት ወይም ሞት$ ይሄ እንግዲህ ተሳድቦ አድናቆትን መሸመት የሚፈልገው አድርባይ ነው$

ሌሎቹ አድናቂ አድርባዮች ደግሞ ለቆመና ለተሾመ ሁሉ ማቃጠር የሚወዱ እርሶ እንዳሉት እያሉ ማቆለማመጥ የሚያምርባቸው ቃጭሎች ናቸው$ በነዚህ የአስተሳሰብ አድማስና ቃላት ማውጫ ላይ ስህተት እጥረት ችግር የሚባል ነገር አለቃ ፊት አይነሳም$

በርሶ አመራር ምን ያልተፈጠረ አለ የሚሉ ዋሾዎች ናቸው$ ራሳቸው ተሿሚዎቹ እስኪታዘቧቸው ድረስ የሆነ ያልሆነውን የሚቀባጥሩ አጀንዳቸው ተሙለጭልጮ ማደግ ብቻ እንጂ አባል የሆኑበት ድርጅት ሀገራዊ ራእይ ማሳካት አለማሳካቱ ወይም የሚሰሩበት ተቋም አላማ መሳካት አለመሳካቱ አደለም$

የተባለ ያልተባለውን ለሀላፊያቸው በማቅረብ ተወዳጅ ለመሆን የሚጥሩ ለዚሁ አስተዋጿቸው ስልጣን ወይም የውጭ ጉዞ ምናምን እንዲቦጨቅላቸው የሚሹ ሰብአዊ ክብራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ያሳነሱ ውራጆች ናቸው$ መርጠው በወረደው መንገድ የሚጓዙ ደካሞች$
ወዳጆቼ በመሀሉ ሌላ መንገድ አለ$ በርካታ መንገድ$ 

ትልቁ ነገር በተሰለፍንበት የስራ መስክ የሚሻለውን አስተዋጾ ለማበርከት መጣር ነው$ ሲቀጥል ከዛም በተጨማሪ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሀላፊነት መሸከም የሚመርጥ ሰው ደግሞ በመረጠው ድርጅት አባል በመሆን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙርያ መሰለፍና የሚያምንበትን ሀገር የሚመጥን ለውጥ ለማበርከት መጣር ይችላል$

ይሄ ጥረት ግን በምንም ሚዛን መሳደብና ማጣጣልን በሁነኛ አማራጭነት እንድንይዝ ወይም ማቆለማመጥና ጥገኝነትንም በመሸከፍ ሆዳችንን የሚበላንን የግል ጥቅም እንድናሯሩጥ አይጋብዘንም$

የተሰራውን አዎ ይሄ ተሳክቷል ብሎ በማመን የቀረውን ደግሞ በኔ አተያይ ይሄ ሊሰራ ሲገባው መፈጸም አልቻለም በሚል መከራከር በይዘት ለመሸናነፍ መሞከር ሲገባ እኔ ካለኩት አማራጭ ውጪ የሆነ አተያይ አፈር ድሜ ይብላ በሚል የሚከናወን እሰጥ አገባና አሜን ባይነት ለዚህ አገርና ለዚህ ደሀ ህዝብ ምኑም አደለም$

እንዲህ ያለውን ከአሮጊቶች ተረት ያነሰ ቁምነገር አልባ ዝባዝንኬ በመስማት ህዝብ ግዜውንም ማባከን የለበትም$

ጀግና ተሳዳቢም ጀግና አሜን ባይም አደለም$ ጀግና ተጫባጩን ችግር በተጨባጭ መፍትሄ የሚረታ ነው$ ጀግና ለፈጠጠው ድህነት መፍትሄ የሚሆኑ አተያዮች እና አሰራሮች የሚቀምር አንዳች ድህነት መቅረፊያ መሳሪያ ማዘጋጀት የሚችል የፈጠራ ሰው ነው$

ጀግና የሚያምንበትን አማራጭ እንዲሰሙት የሚሻውን ያክል አምሮ የሚቃወመውን አማራጭ ለመስማት ዝግጁ የሆነ በዚሁ አማራጭ ቢሸነፍ እንኳ ለመቀበል የማያቅማማ ልበ ሙሉ እንጂ  ኦናው ተሳዳቢም ባዶው አሜን ባይ አድርባዮችም አደሉም$ የነዚህ ሁለት ባዶዎች ልዩነት አንዱ ተቃዋሚዎች አዝለው እንዲያሳድጉት የሚሻ መሆኑ ሌላኛው ባለቀን ተጠግቶ ጥቅም ለማጋበስ መሞከሩ ናቸው$

ጀግና እኔ እንጂ ሌላ ማን አለ አይልም$ ጀግና የኔ አስተዋጾ መቅረት የሚፈጥረው ክፍተት ይኖራል በመሆኑም የሚደክሙ ጓዶችን ላግዝ ትግሉን አንድ ጋት ወደፊት ፈቅ ላድርግ የሚል$ ባያደርግ ትግሉ አንድም ጋት ቢሆን እንዳይጓተት በመስጋት ሲያደርግም ትግሉ አንድም ጋት ወደፊት ሲጓዝ ከሌሎች እንደሱ ተፍ ተፍ ከሚሉ ጓዶቹ ውጤት ጋር ሲደመር ሀገራዊ ፋይዳው የላቀ እንደሚሆን በማመኑ ነው$

ጀግና ዛሬዎቹን የሚረታ እንጂ በዛሬዎቹ ርግማንና ስድብ አለያም የዛሬዎቹን ሹማምንት ሲያደንቅ ግዜውን የሚያባክን አደለም$ ጀግና ዛሬዎቹን ለላቀው ጥቅም የሚያውል አሸናፊ ነው$ የሚረታውም ድህነትን የሚያስገኘውም ሀብት እንጂ ሌላ ሰብአዊ ባላንጣዎች የሉትም$

አልሞ የሚመታው ጠላት ስንፍና አልሞ የሚገነባው ሀብት ትጋትና የመቻቻል ፖለቲካ እንጂ ማዋረድም በማዳነቅ ለመጠቀም መሞከርም የአላማው ይዘት አደለም$ ግቡ ሀገራዊ ድሉ ህዝባዊ አቅሙ ህሊናዊና ከውስጥ የሚመነጭ ነው$

ወዳጄ ቁምነገሩ ከመቃወምህም ከመደገፍህም አደለም$ አሰላለፍህ በየትም ይሁን በየት አስተዋጾህ ሀገራዊ አጀንዳን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ይሁን$ ይዘቱ ባለፋይዳ ክርክርህ የበሰለና በጉዳዮች ዙርያ የሚያጠነጥን ይሁን$

እውነት እውነት እልሀለው እንደላው መጻፍ የምር ተሳዳቢም አሜን ባይ አድርባዮችም ቢሆኑ ለዚህ አገር እዚህ ግባ የሚባል ፋይዳ አይኖራቸውም$
ሁሌም በመሀሉ መንገድ አለ$

Wednesday, April 10, 2013

Benishangul Gumuz revoked the Eviction of Amharas from the State


I learned Benishangul Gumuz Regional State revoked the decision of the districts that evicted farmers of Amhara region origin.

The Regional State in consultation with Amhara Regional State call up on those who have been evicted to welcome back to where they live with no conditions.

The decision of the officials in the district could be to protect the forests and the land in the region; but it takes, the report I heard say, coordinated effort to effectively resolve those concerns.

It is not about evicting communities; it is about halting the trend of migration looking for farm land with concerted effort, it says.

I am happy the two regional states have come to such consulted solutions to end the misery the communities have gone through since they left their area.

It is to be recalled over 5000 people of Amhara origin left the state. Now all of them are invited to go back and resume their life there.


The report even try to show how the two regions are working in close cooperation. It also says the state doesn't have anything against Amhara people there; that is why it indicates Amharas are serving as senior officials across the state.

I do appreciate those who voice their concern to essentially resolve the plight of those evicted. Yet end to the political opportunism that swirl around this issue.

It is nice to find a sustainable resolution to such matters through the parliament, Federal Affairs Ministry and I learned Benishangul Gumuz regional state revoked the decision of the districts that evicted farmers of Amhara region origin.

The regional state in consultation with Amhara Regional State call up on those who have been evicted to welcome back to where they live with no conditions.

The decision of the officials in the district could be to protect the forests and the land in the region; but it takes, the report I heard say, coordinated effort to resolve those concerns.

It is not about evicting communities it is about halting the trend of migration looking for farm land with concerted effort, it says.

I am happy the two regional states have come to such consulted solutions to end the misery the communities who left from the Benishangul Gumuz have gone through since they left their area.

It is to be recalled over 5000 people of Amhara origin left the state. Now all of them are invited to go back and resume their life there. The report even try to show how the two regions are working in close cooperation by indicating many Amharas are serving as senior officials across the state.

I do appreciate those who voice their concern to essentially resolve the plight of those evicted. Yet end to the political opportunism that swirl around this issue.

It is nice to find a sustainable resolutions to such matters through the parliament, Federation House and Federal Affairs Ministry.

I am happy for them. The regional states also deserve appreciation for their prompt response on the case..


Sunday, April 7, 2013

Meles Zenawi isn't a saint

I don't expect Meles to be saint. I know he is a human being when he makes errors in his undertakings.

We remember Meles for many outstanding operations and apparent results. He lived his time loving Ethiopia in action and turning its bad images with good ones.

You will never have saint leaders with no visible mistakes. You only have leaders with outstanding achievements or with outstanding failures.

Meles is known for his trademark accomplishments. That is why most of us believe he is a noble politician.

Anyone who loves his or her country does as much as he does even if it takes making the same mistakes he does. I am sure such performances will have profound effect on Ethiopia.

No best criticism propels Ethiopian economy by double digit for a decade, no best insult and cynicism take Ethiopian social services like health and education through such impressive progress and no heap of blame builds infrastructure in such a massive scale.

Ethiopia seeks our hands to get dirty with national deeds that matter most. Ethiopia seeks our minds to imagine solutions for our formidable problems. Ethiopia seeks our errs to listen to outstanding ideas that can resolve the development doldrums we face.

This country can't afford a piece of a page for nasty comments and hatred messages; this country can't afford a citizen to engage in smear campaign. This country can't afford to invest brains that imagine how best they can insult their brother on the other side of the isle.

Love your country with your fruitful contributions that can be solutions to any minute problem. Problem solved is promised delivered for a real patriot who loves his/her country.

The very cheap talk that says "There is this and that problem" is a very poor contribution from any one of us, particularly "we the so called educated". The Educated does relevant solutions for real problems amongst the public.

By complaining "these guys are not solving the problems" we are not solving the problems either. Just conquer the problem and get it solved.

I do admire Meles for resolving some of the problems with due diligence. Emulating him for that is the best thing anyone can do be it his opponent or his supporter. No one appreciating Meles for being complete and perfect but many are complementing him for his unmatched patriotic performance.

Yet I believe Ethiopia can have another best leader like him or even better than him. To deny him his deserving admiration shows the wickedness of the person who denies his achievements because he will always be remembered for his best contributions be it with our consent or otherwise.

Nations have never denied their heroes off their deserved status.

Time for action not just for naive criticisms.