ሲጀመር
በግሌ የትኛውም ሚድያ ከፖለቲካ አቋምና ከትላልቅ ቢዝነሶች ተጽእኖ ውጭ ይሆናል የሚል ቅqት የለኝም$ ሆኖም
አያውቅም$ ዛሬም
በአለም ላይ ያሉ ሚዲያዎች ከዚህ መሰሉ ተጽእኖ ውጭ አደሉም ለመቼውም እሚሆኑ አይመስለኝም$
በገዛ
ፈቃዱ ራሱን ነፃ እያለ የሚጠራው አብዛኛው የግል ፕሬስ ለምንወዳት ሀገራችን ኢትዮዽያ ራሱን የለየለት ተቆርቋሪ አድርጎ ይቀርጻል$ ለሀገሩ
በርግጥም ተቆርቋሪ ሆኖ ከሆነ ደስ ይላል$ እውን በቁምነገሩ ለሀገሩ ተቆርቋሪ
ነው ወይ?
ሁሉም
የግል ፕሬስ በዚህ የሚተች ባይሆንም በርግጥ የሚለፍፉትን ያክል እነዚህ የግል ፕሬሶች የሀሳብ እና የአቋም ነጻነት አላቸው ወይ
በሎ መጠየቅ ይገባል$ ስንኳንስ የተለያዩ ፓርቲዎች የሚያቀነቅኑትን
አቋም ገለልተኛ ሆነው ሊያቀርቡ ይቅርና ከተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ልቀው የተቃውሞ ፖለቲካው አብይ አቀንቃኝ ናቸው$
የለየላቸው
የተቋውሞው ፖለቲካ አካል ሆነው ሲያበቁ እዚያው ሳሉ እነሱው ተመልሰው የነጻ ፕሬስ ተቋርቋሪ ነን ያለኛ ነጻነት የገባው ማን አለ
በሚል ስብከት ያደነቁሩናል$ እኔ እስኪገባኝ ድረስ አንድ ፕሬስ
የገ¸ው ፓርቲ
ሁነኛ ተቃዋሚም ነጻ ሚዲያም የመሆን ቁመና ፈጽሞ ሊኖረው አይችልም$
አንዳንዴ
እገሌ የጋዜጠኝነት ምልክት ነው ብለው የሚነግሩን ግለሰብ ያሻውን ሀሳብ የመግለፅ መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የጋዜጠኝነት ቀንዲል ነው
ከሚሉን የተቃውሞው ጎራ አፈቀላጤ ወይም ህዝብ ግንኙነት ነው ቢሉት ይሻላል$
እንዳለመታደል
ሆኖ ኢቲቪን በመንግስት ቃላቀባይነቱ የሚያብጠለጥለው ነጻ ሀሳቢና ጸሀፊ ሁሉ የተቃውሚው ማውዝ ፒስ የሆኑትን የግል ፕሬሶች ጎበዝ
መረጃ ሳታዛቡ አቅርቡልን አይላቸውም$ በኔ እምነት እንዲህ አይነቱ የግል
ፕሬስ ኢቲቪን ለመሰል ድርጊቱ ሊተቸው የሚችልበት የሞራል የበላይነት የለውም$ የራሱን
የቤት ስራ ስላሰራ$
ከመጀመርያ
እስከ መጨረሻ ገጻቸው ገ¸ውን ፓርቲ በሚያብጠለጥል ጽሁፍ የተሞሉት የተቃዋሚው
ጎራ አፈቀላጤ ጋዜጦች ደርሰው በዚያው ቁመናቸው ኢቲቪን በመንግስት አፈቀላጤነት ይወቅሱታል ኢቲቪ መንግስት ስለሚያስተዳድረው አፈቀላጤ
ሆነ እንደሚነግሩን ነጻ ከሆኑ ምን ይዟቸው ነው ወዲህም መንግስትና ኢህአዴግን ወዲያም ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በተመሳሳይ ትጋት የማያብጠለጥሉት
እውን ማብጠልጠል የላቀው የጋዜጠኝነት ሚና ከሆነ$
ነጻ ናቸው
በሚል የዋህነት አደለም ጥያቄውን እያነሳው ያለሁት$ ነን
ስለሚሉን መሆናቸውን በስራቸው ያስረዱን ዘንድ ብቻ ነው$ እኔ
ነጻ ነኝ የሚባል ቅራቅንቦ አይገባኝም ሁላችንም አቋም አለን$ አቋም
አለመያዝም አቋም ነውና$
በቀላል
አገላለጽ እኚህ ጋዜጦች የሚሉንን ያክል ነጻ ቢሆኑ ኢህአዴግን ይህን ያክል ለመተቸት ባልፈራው ድፍረታቸው ተቃዋሚዎችን በተከታታይ
በተቹ ነበር$ የሆነ
ሆኖ ካፈጣጠራቸው የተቃዋሚው ህዝብ ግንኙነት በመሆናቸው ይህንን ሊያደርጉት
አይችሉም$
እውን
ለሀገሩ የሚቆረቆር ሚድያ በወጉ በመከባበር መንፈስ እንኳ ውስጠ ፓርቲ ስብሰባዎችን መምራት የተሳናቸውን ፓርቲዎች እንኳንስ ሀገር
ልትመሩ ይቅርና በአንድ ፓርቲ ዙርያ የተሰባሰባችሁት አመራሮችም ተግባብታችሁ መስራት አልቻላችሁም ሊላቸው ይገባል
እውን
ሚድያው ለሀገሩ የሚቆረቆር ቢሆን ምንም የማይመሳሰል ፖለቲካዊ አቋም ሳይኖራቸው በምርጫ ሰሞን የሚሰባሰቡ የፓርቲ እድሮችን ጎበዝ
ራሳችሁን ቆም ብላችሁ እዩ ምርጫውን ብታሸንፉ በማን የፖሊሲ እምነት ሊሰራ ነው የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ደካማ ውል የምታስሩት
ብሎ ሊወቅሳቸው ይገባል
እንደሚያደነቁረን
አብዛኛው የግል ሚድያ የተቃውሞው ፖለቲካ አብይ አካል ካልሆነ የፓርቲያቸውን ውስጣዊ ስብሰባ ሚስጢራዊነት እንኳ የማይጠብቁ አመራሮች
ዲስፕሊን አልባነት ለምንድነው የማይኮንነው? እኮ
በዚህ ቁመና ነው በከፍተኛ ምስጢር መጠበቅ ያለባቸው ብሄራዊ ጉዳዮች ያሉበትን ሀገር የመምራት ስራ ይህን ለመሰሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና
አመራሮች የምንሰጠው? እኮ
ለነጻ ሀሳብ የቆመው ሚድያ የት ጠፍቶ ነው ይህን የመሰለውን የሰለለ ቁመና ገላልጦ የማይጽፈው?
ሌላ ምንም
ምክንያት የለውም$ በአንድ በኩል የተቃውሞው ጎራ ሁነኛ መሳርያ
ስለሆነ$ ይህን ሀቅ ምንም ያክል መሀላና መገዘት ሀሰት አያደርገውም$ በሌላ
መልኩ ይሄ ነጻ መረጃ የማቅረብ ቁርባን ቀምሻለው የሚለው ሚድያ ገበያውን ለማጧጧፍ በሬ ወለደ ዜናና ግነት ይጠብሳል$ ይሄን
ቁመናውን ይረሳና በሀገር ፍቅርና በነጻ ነኝ መሀላው ሊያደነቁረን ይሞክራል$
የሚሻለው
በስፋት በአሜሪካ ሚድያ እንደተለመደው እኔ የዚህ የፖለቲካ ቡድን እና ፓርቲ አቀንቃኝ ነኝ ብሎ በዚያው ፍልስፍና ዙርያ የበሰሉ
ጽሁፎች ማውጣት እንጂ ባንድ በኩል ገ¸ውን ፓርቲ በሚገባም በማይገባም ምክንያት ማጣጣል
በሌላ ገጹ ደግሞ መረጃ ለማድረስ ብለን ነው እንጂ እኛ ነጻ ነን ማለት ተረት ሊሆን ቢችል እንጂ እውነታውን የናንተም ህሊና የኛም
ያውቀዋል$
በመሆኑም
እንዲህ ያለው ጋዜጠኛም መባል ያለበት የነጻ ጋዜጣ ምልክት ሳይሆን የሚደግፈው የተቃውሞ ቡድን አስተሳሰብ አቀንቃኝ ብቻ ነው$ ለምሳሌ
በአሜሪካ ፎክስ ኒውስ የሪፐብሊካኑን አቋም በአዋጅ በግልጽ ያራምዳል$ MSNBC
በበኩሉ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን አቋሞች ያራምዳል ተብሎ ይታመናል$ ሲኤንኤን
ደግሞ ሚዛናዊ ዜና ለማቅረብ ይሞክራል ሆኖም በተወሰነ ደረጃ ግራ ዘመም ነው የሚል ወቀሳ ይሰነዘርበታል$
በኔ እምነት
አንድም ለይቶልን እንደነዚህ ሚድያዎች የፖለቲካና ኮርፖሬት አጀንዳዎችን ማራመድ አለያም ሲኤንኤን እንደሚያደርገው ጥቂት ሚዲያዎችም
በኛ አገር እንደሚያደረጉት መሀሉ ሜዳ ላይ መጫዎት ብንችል ነው እሚሻለው$
እንደኔ
እንደኔ ጭልጥ ያለ የፖለቲካ አጀንዳ እያራመደ ያለ ሚድያ በምንም መስፈርት ለነጻ ሀሳብ ተቆርቋሪ ስለሆንኩ እና የሀገር ፍቅር ስላለኝ
ነው ቢለን ሊገባን አይችልም$ የሚሻለው ይህን አቋም የማራምደው
የዚህ ፖለቲካ ድርጅት አቋም ለሀገሬ ይበጃታል ብዬ ስለማምን ነው ቢባል ነው$
በአስሩም
ጣታቸው የለየለት የተቃዋሚ ጎራ አቋም እያራመዱ (ማራመድ መብታቸው ነው) እኛ
ከየትኛውም ፖለቲካ ድርጅት አቋም እጃችንን የታጠብን ነን ማለት ቀልድ ነው$ በአንድ
እግር አገር ወዳድ ነጻ ጋዜጠኛ በሌላው ደግሞ የተቃውሞ ፖለቲካው ጠበቃ መሆን አይቻልም$
ጋዜጠኛ
የፖለቲካ አቋም ሊኖረው ይችላል$ ያንን የፖለቲካ አቋሙን አራምዶ
ሲያበቃ ግን የለም የለም የፖለቲካ አጀንዳ የለኝም እኔ የማንኛውም ሀሳብ በነጻ መነገር ጠበቃ ነኝ ብሎ መቅረቡ የዋህነቱ ነው ሀቁ
አደለም$
አንድም
ለይቶልን የፖለቲካ አቋማችንን አውጀን እንስራ አለያ በተጨባጭ በተቻለ መጠን ገለልተኛ ሆነን እንቀጥል$ ነጻ
ነኝ እያሉ መቆመሩ የትም አያደርስም$
" አንድም ለይቶልን የፖለቲካ አቋማችንን አውጀን እንስራ አለያ በተጨባጭ በተቻለ መጠን ገለልተኛ ሆነን እንቀጥል. ነጻ ነኝ እያሉ መቆመሩ የትም አያደርስም " ያልከዉ ጥሩ እይታ ነዉ ፨ ምናልባትም የፕሬስ ነፃነት በአግባቡ ሲከበር , የጋዜጠኞች ሙሉ መብት በተግባር ሲዉል, የጋዜጠኞች በሰበብ አስባቡ መታሰር ሲቀር, ... ያኔ ሚድያዎችም ራሳቸዉን ለመግለፅ ድፍረቱን ያገኙ ይሆናል ፨ በነገራችን ላይ የአሜሪካ ገዥ ፓርቲ (ዲሞክራቲክ ፓርቲ) የተቃዋሚዉን ፓርቲ (የሪፐብሊካንን ፓርቲ) ደጋፊ ጋዜጠኞች አያስርም አያንገላታም ፨ ለዚህ ነዉ ጋዜጠኞችም ሚድያዎችም በቀጥታ ራሳቸዉን ለመግለፅ የቻሉት ፨
ReplyDelete