Thursday, February 28, 2013

የግብጾቹ ቁማርተኛ ጣቶች!!!



                                                                                         ዘርይሁን ካሳ

የሳውዲው ልኡል በአረብ ህዝብ ጥቅም ላይ ያነጣጠሩ ለራሳቸው የረባ ጥቅም የማይገነቡ ይሆነኝ ብለው የአረቡን አለም ለመጉዳት የሚያሴሩ ኢትዮዽያዊ ጣቶች እንዳሉ ነግረውናል:: ልኡሉ እሳቸው ደጃፍ በአረቡ ህዝብ ስም የሚቦካው ለአረቡ አለም ህዝብ ፋይዳ የሌለው ያረጀ ጎረቤትን በማደህየት የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚጥር ፖለቲካዊ አተያይ  የማይገባን መስሎአቸው ከሆነ ስተዋል::

ኢትዮዽያንና የአፍሪካን ቀንድ የሚያምሰው የነማን ረጅም እጅ እንደሆነ እንረዳለን:: ይህ ረጅም እጅ መደፈቅ ያለበት ያረጀ የግብጽ ፖለቲከኞች ቁማር ነው:: ሁሌም የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ ጎረቤት በማተራመስና በማዳከም የሚያምን ደሀ አመለካከት:: እንዲህ ያለው አመለካከት ነው አስቦና ተጠቦ ሞቶ ከሰማንያ በመቶ በላዩን ዉሀ የምታበረክተውን አገር አንዳች ጠብታ ውሀ የማትጠቀምበትን ስምምነት ያሰረው::

ይሄ ያረጀው የግብጽ ፖለቲከኞች ቁማር በውጤታማ ዲፕሎማሲ ሲረታና ውሀው ፍትሀዊ ክፍፍል ሊደረግበት ጫፍ ሲደርስ የማይቀረውን ለማስቀረት ባለበሌለ ሀይሉ እየተፍጨረጨረ ነው:: የግብጽ ህዝብ ኢትዮዽያ እየተራበች እኛ እንብላ የሚል ኢፍትሀዊ አቋም አለው የሚል እምነት የለኝም::

የሳውዲው ልኡል ሲሆን ሲሆን ወደ በራችን ያመጡትን ጣት በአግባቡ ቢጠቀሙበት ጥሩ ነበር:: ጣታቸውን በወሳኝ ብሄራዊ ጉዳያችን ውስጥ ሰንቅረው ሲያበቁ እንዲህ ለነተበ የማጋጨትና የማተራመስ አጀንዳ የተጠቀሙት መሆኑ ሀሳባቸውን ያኮስሰዋል ያረክሰዋልም::

በርግጥ ራሳችንን እንዴት መከላከልና ጥቅማችንን እንዴት ማስከበር እንዳለብን የምናውቅ በመሆኑ የልኡሉ አይነት የተረገሙ አስተያየቶች አያሰጉንም:: ያም ሆኖ በቀጠናችን ያረጁ የፖለቲካ ጓዳዎች የሚቦካውን እና እንደሚቦካ የምንጠረጥረውን የመከላከያ ባለስልጣኑ ስላበሰሩን እናመሰግናቸዋለን:: የሱዳኑ የዜና ምንጭ በትክክል እንደጠቆመው ይሄ ንግግር ከጀርባው ሌላ ጉዳይ እንዳለው ተረድተናልም::

በቅርቡ ሙስሊሙ ያነሳውን የውሰጥ ጉዳይ አስታከው ሀገር ወዳዱን ሙስሊም ይሸውዱት ይመስል ከጥያቄው ጀርባ ምን ሊሰሩ ይተጉ እንደነበር ተደርሶበታል:: አሁን ልኡሉ እንደነገሩን አጀንዳው ኢትዮዽያ ስታድግ ያመናል የኢትዮዽያ ማደግ ግብጽን ይጎዳል በሚል የሚቀነቀን እና በፍትሀዊው አገር ወዳድ ሙስሊም የውስጥ ጉዳይ በመግባት ኢትዮዽያ የማያባራ ቀውስ ውስጥ እንድትገባ  በመመኘት እየሰሩት እንደሆነ እናውቃለን::

ያ መረብ ነው የተበጠሰው መረቡ ከኢጋድ ቀጠናዊ መዋቅር ጀምሮ በሌሎች አካላት እይታ ውስጥ መውደቁን ሲያውቁ ከዋሽንግተን እስከ ካይሮ ከካይሮ እስከ ሪያድ ያሉ የዚሁ ሴራ መረቦች ሁነኛ መልካቸውን እና አጀንዳቸውን ፍንትው አድርገው ይነግሩን ጀምረዋል:: የግብጻዊው ሰባኪ የጂሀድ አዋጅ በሀገር ወዳዱ ሙስሊም ስም ነው ፊልም የተሰራበት:: ኢትዮዽያዊው ጁሀርም ሀይማኖት ተንተርሶ የመጣው ሴራ አላማ የኢትዮዽያን መንግሰታዊ መዋቅሮች ማውደም እንደነበር በተባ ምላሱ ነግሮናል:: የሳውዲው ልኡል በዚሁ ማእቀፍ የሚታይ ነው::

ልኡሉ እቺ አገር የማይጠቅም ግድብ እየሰራች ያለችው ይሆነኝ ብላ የሱዳንን እና የግብጽን ጥቅም ለመጉዳት ነው የሚል ተረታቸውን ነው የነገሩን:: ልኡል ሆይ 6000 ሜጋ ዋት ሀይል ለርስዎ ፋይዳ ቢስ ከሆነ ከጪሳሙ ነዳጅ ኤሌክትሪክ እንደሚያገኙ በመተማመኖ ሊሆን ይችላል:: ለኛ 6000 ሜጋ ዋት ማለት እስካሁን የምናመርተውን ኤሌክትሪክ አቅም በሶስት እጥፍ የሚያሳድገው መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን:: የማይጠቅም ግድብ የሚሆነው በርሶ የተቃወሰ ምዘና ካልሆነ በቀር ይህን የመሰለ ጥቅም የለም:: የማይጠቅመውስ የርሶ የርጎ ዝንብነት የርሶ ጣት የማይመለከታትን መጠንቆሏ ነው:: ሌላው የማብራሪያዎ ዉበት ግድቡ ከፈረሰ ካርቱምን ይጠራርጋታል አስዋን ግድብንም ያሰጋዋል የሚለው ቅኝትዎ ነው::

ልኡል ሆይ አስዋን ቢፈርስስ ካይሮ አትጥለቀለቅም እንዴ? ከሆነ ደግሞ መሰራት አልነበረበትም ማለት ነው እንደርስዎ ገለጻ:: የሆነ ሆኖ ሞት ተፈርቶ መተኛት ስለማይቀር ተሰራ:: የኛ ሲሆን ካርቱምን ስለሚያጥለቀልቅ አይሰራም የግብጾቹ ሲሆን ለህዝብ ጥቅም ሲባል ነው አደል?! ልኡልነትዎ አይዞት ቢፈርስ እንኳ ከአስዋን ቀድሞ አይፈርስም:: ከፈረሰም አስዋን ከሚያስከትለው የበለጠም የተለየም ጉዳት አያደርስም:: እናም በርስዎም እርባናቢስ መከራከሪያ ቢሆን ግድባችን ፍትሀዊ ነው::

ልኡል ሆይ ሲፈርስ የሚከሰተው ያሳስቦታል? ባለመገንባቱ ኢትዮዽያና ቀጠናው የሚያጡት 6000 ሜጋ ዋት ሀይል አያስጨንቆትም? ይልቅ ልኡልነትዎ የሚሻለው ግድቡ እንዳይፈርስ የምእራቡን አለም ባንክ ያጣበበውን ገንዘባችሁን ብታበድሩን ኖሮ ግድቡን ይበልጥ ጠንካራ አድርገን እንገነባው ነበረ:: ለነገሩ ከናንተ የጀርባ ውጋትነትም ጋር ቢሆን አስተማማኝ እና ጠንካራ ግድብ ነው እየሰራን ያለነው:: ሲፈርስ ካርቱም ስለምትጠፋ ብቻ ሳይሆን ከግድቡ የሚገኘውን ሀይል ዘላቂ ማድረግ ስለምንፈልግ:: ከደቃቃው አቅማችን የተሰበሰበውን ሀብት ማባከን ስለማንፈልግ እንዲያውም በመገንባቱ የሚጎዱ ያስመሱሏቸውን ግብጽንና ሱዳንን ስለሚጠቅምም ጭምር::

ልኡልሆይ አስዋንን እና የኛን ግድብ ምን ይለየዋል? የኛም ግድብ ለመብራት ሀይልና ለአሳ ምርት ቢያገለግል ነው ልክ አስዋን ለግብጾቹ እንደሚያደርገው:: ወይስ ኢትዮዽያ ውስጥ ናይል ሲገደብ ለአሸባሪ ፈንጂና ቦንብ የምናመርትበት አስመሰሉት:: የኔ ጌታ እኛም ጋ ዉሀ ሲገደብ ሀይል አሳ እና በተወሰነ ደረጃ መስኖ ሊሆን ቢችል ነው:: በባህሪው የአባይ አቀማመጥ ኢትዮዽያ ውስጥ ለመስኖ የመዋል እድሉ ጠባብ ቢሆንም::

በርግጥ ጉዳዩን ለማብራራት ቀናነት ብቻ ሳይሆን እውቀትም ይፈልጋል:: ቀናነቱ እንደጎደሎት አስተያየትዎ ያመለክታል የእውቀትም ችግር ያለብዎት መሆኑን ግን የሚያቀርቡት መከራከሪያ ደካማነት ያመለክታል:: ኢትዮዽያውያን ትሁት ነን ከተነካን ግን ያውቁታል:: እርሶ የማንበብ እድሉ ካለነበረዎት ሌሎችን ይጠይቁ:: ዛሬም ያ አቅማችን አብሮን አለ እንዲያውም ዘምኖና ተሻሽሎ ጭምር:: ሁሌም ለሰላማዊ እና ዲፕሎማሲያዊ አማራጭ ቅድሚያ የምንሰጥ ቢሆንም::

ለነገሩ አለቆችዎ ልኡል አፋቸውን አድጧቸው ነው ብለዋል:: የሆነ ሆኖ እሚከካ እሚቦካውን መጠርጠራችን ከዚያም አልፎ እንዲህ በአደባባይ ቀረርቶ ማረጋገጣችን ደስ አስኝቶናል:: የምር እንኳን አፎን አዳጦት አጀንዳ ፈጥሮልናልና:: ሁሌም ስለአረብ ሲነሳ ስለ ኢትዮዽያ ሙስሊም የተነሳ የሚመስላቸው ደምና ሀገርን ከሀይማኖታዊ መመሳሰል ጋር የሚያስተሳስሩ ደካሞች አሉ:: አዎን ሙስሊሞች ኢትዮዽያ ውስጥ አሉ ግን ኢትዮዽያዊ ሙስሊሞች ናቸው:: ሳዉዲአረብያዊ ወይም ግብጻዊ አደሉም:: ሀይማኖታቸውን በሀገራቸው ይኖሩታል ሀገራቸውን ለሀይማኖታቸውም ጭምር ሲሉ ይጠብቁታል::

ለአብነት የቅርቡን ግዜ ሰላማዊውን የሙስሊሙን የውስጥ ጉዳይ እኚሁ የውጭ ሀይሎች ለአሸባሪነት አጀንዳቸው እንዴት ይፈትሉት እንደነበር እናስታውሳለን:: በአንድ በኩል ለሙስሊሙ ከራሱ በላይ ያውቅለት ይመስል መንግስት በጉዳይህ እየገባ እየፈተፈተ ነው የሚል ፕሮፖጋንዳ ይነዛሉ:: በሌላ ገጽታው ደግሞ ከሀገር ወዳዱ ሙስሊም ጀርባ ከቅጥረኞቻቸው ጋር በመተባበር አሸባሪ ድርጊታቸውን ለመፈጸም ሳያሰልሱ ይሰራሉ:: ያም ሆኖ የከፋ ችግር ሳይፈጠር ሁኔታው መልክ እየያዘ ነው:: የሚቀሩትም ነገሮች በሂደት ኢትዮዽያዊው ሙስሊም በራሱ መንገድ የሚፈታቸው ይሆናሉ::

ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሰላማዊ ጥያቄውን በራሱ መንገድ መፍታቱን አያቆምም:: ያ አንድ ነገር ሆኖ ሲያበቃ በሌላም በኩል ልኡል ሆይ እርስዎን እና ግብጻዊውን ሼክ የመሳሰሉ ሰባኪዎችንም ከመሰረታቸው መንጥሮ ከቅጥሩ ያወጣል:: ይቅርታ ያድርጉልን ጌታዬ ኢትዮዽያዊው ሙስሊም ዜግኑትን ወዶ የሚኖር እንጂ የተጋተው አደለም:: አገሩን በፖሊስ ያስጠብቃል የመስጊዱን ሰላም በፖሊስ ያስጠብቃል እንጂ ማንነቱ ተጠርጥሮ ፖሊስ በገባበትና በወጣበት የሚጠብቀውም አይደለም::

ልኡሉና መሰሎቻቸው ኢትዮዽያዊው ሙስሊም አባይን ብርና እውቀቱን ሰውቶ እየገነባው እንደሆነና በቀጣይም በማያሰልስ ትጋቱ እንደሚገነባው የገባቸው አልመሰለኝም:: ይሄ ኢትዮዽያዊ ሙስሊም ሀገራዊ ፍቅሩ ደሙ ጋር የተሰናሰለ መሆኑን አያውቁትም:: ሀይማኖታዊ ተመሳስሎው እና አምልኮቱን በየዋህነት ለአሸባሪና አውዳሚ እቅዳቸው የሚያውለው ይመስላቸዋል::

አይ አለማወቅ ኢትዮዽያዊ መልኩን ነብር ዥንጉርጉርነቱን እንደማይቀይር ቢያውቁ በበጃቸው ነበር!!! እነዚህ ተከታታይ ድርጊቶች በእምነቱ ቅጥር ስር ሊሰሩ መሞከራቸውን የተረዳው ሙስሊም ኢትዮዽያዊ ነብር ሆኗል:: አይነካም አይደፈርም:: ብሄራዊ ጥቅሙን አሳልፎ አይሰጥም:: በተለይ በመስገጃና በአምልኮ ቦታው ሰላሙን የሚነሳው የውጭ ሀይል አይፈነጭበትም የቀረውን በተግባር ትማራላችሁ::

መጋረጃው ተቀደደ መልካችሁንም አወቅነው ግብጻዊው ሼክም ሳውዲው ልኡልም ሌሎች ግብጻዊ የጥፋት ሰረገላዎችም ቀላሉን አማራጭ መተባበርን መወያየትን ምረጡ:: ለነገሩ በመረጣችሁት መንገድም ቢሆን ተጋግጣችሁ ጭምር አዋጩ መተባበር መሆኑን ትማራላችሁ::
ይቆየን!!!

Tuesday, February 26, 2013

ችግር ካለ እድገት የለም!


ዘርይሁን ካሳ

"በዝናብ እጥረት የተነሳ ዛሬም የምግብ እህል እጥረት የሚያጋጥማቸው ቦታዎች ቀላል አደሉም  ትልቅ ችግር ነው። አገራችን በርካታ መንገድ የሌለው አካባቢ አላት ይህ ችግር ነው። በቅርብ የጤና ጣብያ የሌላቸው በርካታ ቦታዎች አሉ ይሄም ችግር ነው። ቀላል የማይባል የትምህርት ቁሳቁስና የጥራት ችግር አለ። ፍትሀዊ ያልሆኑ ውሳኔዎች በፍርድ ቤትም በሌሎችም መንግስታዊ ተቋማት ይስተዋላሉ የችግሩ ዝርዝር ይቀጥላል።"

"ይሄ ሁሉ ችግር ባለበት ታዲያ እቺ አገር አድጋለች ሲሉ አያፍሩም! ኢቲቪ ነው ደግሞ የባሰበት መንገድ ተሰራ ምርታማነት ጨመረ ጤና ጣቢያ ተመረቀ እያለ ሌላ አገር ያለን ይመስል የሚዋሸን።እንደ ኢቲቪ ዘገባ ቢሆን ይሄ አገር የት በደረሰ!"

ይሄ አስተሳሰብ እድገት አለ የሚባለው ሁሉም መንገድ ተሰርቶ ሲያልቅ ምንም የምግብ እህል እጥረት ያልተከሰተ ማንኛውም የጤና እክል የተፈታ እንደሆነ ያመላክታል። በየትኛውም አለም ክፍል እያደጉ ያሉ አገሮች ወይም የበለጸጉ የሚባሉ አገሮች ችግሮቻቸውን ፈተው የጨረሱ አደሉም።ሊሆኑም አይችሉም!

ይልቅም ለምተዋል የሚባሉት አገሮች ትልቁ ልማት ችግር መፍታት የሚያስችል ግለሰባዊ እና ተቋማዊ ብቃት መፍጠራቸው ነው።

እንዲህ ያለውን ችግር የመፍታት አቅም በተከታታይ ሳይንሳዊ ምርምርና በማያቋርጥ ቀጣይነት እያላቁት መሄዳቸው ነው።ይህን የመሰለውን ችግር የመፍታት አቅማቸውን ደረጃ በደረጃ ችግሮቻቸውን እየፈቱበት የሚሄዱ በመሆኑ በርካታ የስራ እድል መፍጠር ስኬታማ ተቋሞችና ምርቶች የሚፈልቁበት አዙሪት መፍጠር ችለዋል።

በማንኛውም አገር ትልቁ ቁምነገር ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ፈጠራዎች በማያባራ አዙሪት በላቁ ህሊናዎች እና የተቡ ግለሰቦች ተቋማዊ ቅርጽ ይዘው እየተመረቱ መሄዳቸው ነው። ሌላው ጉዳይ ችግር በመፍታት ሂደት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቁሳቆሶች ወይም ቱልስ ዲዛይን ማድረግና ማምረት መቻል በዚህ የችግር አፈታት ሂደትና እድገት ውስጥ ቋሚ ገጽታዎች እና ልማታዊ አቅሞች እየሆኑ ይሄዳሉ ማለት ነው።

አደግን ለማለት ችግር ጠፋ መባልን የምንመኝ ሰዎች እንዲህ አይነቱን ሁኔታ በወዲያኛው አለም ካልሆነ እዚህ አናገኘውም። ሆኖም አያውቅ ወደፊትም አይሆንም። ችግር ሲጠፋ ስራ ይጠፋል። በቀላሉ ችግር በሌለበት አገር መንግስት አያስፈልግም።

ኢቲቪ አልዋሸም አገራችን እያደገች ነው@ እዚህ አገር ችግሮች አሉ የሚሉ ሰዎችም አልዋሹም አዎ በርካታ ችግሮች አሉ@ ይሄ ማለት ግን ችግሮች እየተፈቱ አደለም ማለት አይሆንም። ችግሮች እየተፈቱ ከሆነ ደግሞ በተፈቱበት ልክ እድገት አለ ማለት ነው።

መንገድ እየተሰራ ነው ማለት ሁሉም ቦታ መንገድ አለ ማለት አደለም@ ጤና ጣብያ ተገነባ ማለት የጤና እክሎች የሉም ማለት አደለም@ የትምህርት ሽፍናንና መሰረተ ልማት ተሳስፋቷል ማለት የጥራት ችግር የለም በሽፋንም ረገድ ቢሆን ገና የሚሰራበት ነገር የለም ማለት አደለም@ የእህል እጥረት አለ ማለት ምርታማነት የጨመረባቸው አካባቢዎች የሉም ማለት አደለም።

ሲደመደም አድገናል ለማለት ምንም ችግር የለም መባል የለበትም! አለማደጋችንንም ለማሳየት ችግር መጠቆምም በቂ አደለም!

Friday, February 22, 2013

ግቡ ነቆራው አደለም ግቡ ችግሩ መፈታቱ ነው



Zeryihun Kassa
በአስተሳሰብ ላይ መተጋገል የሚሳነው ሰው የሚቀለው ታርጌት የቆመን መዘርጠጥ ነው:: በቃ ጀግና ለመባል ያክል::

 

አስተሳሰባችንና በዚያው የተቃኘው ተግባራችን እንዲታረም ራሳችንን የችግሩ አካል አድርገን ስናበቃ የመፍትሄው አካል ሆነን መትጋት እያለብን፣



የሚቀለን ዉሃ ልማት ሆነን ስንት ደንበኛ እያለቀሰ ጥሩ አገልጋይ የሆን ያክል መብራት ሀይል የሚሰራውን የኛን አይነት ሰው እንቦጭቃለን፣



ስንቱን የምናስለቅስ ያለ አግባብ ትርፍ የምናግበሰብስ ነጋዴ ሆነን የታክስ ሰብሳቢውን ተቋም ሰራተኞችና ሀላፊዎች ንዝሀላልነትና ሌብነት እንወቅሳለን::



ሚሊዮኖች እና ቢሊዮኖች የሚሰበስበው ኤንጂኦ ውስጥ እየሰራን እና በደሀ ስም የሚሰበሰብን ብር ያለ አግባብ እየቦጨቅን የመንግስትን ሌቦች ለመተቸት ምላሳችን ይዘረጋል::



ቢያንስ ቢያንስ የማንሰርቅና የማንበድል ጥቂቶች ብንኖር እንኳ በየዘርፉ የሚታየውን ይህን መሰል ችግር ለመፍታት ባለመነሳሳታችን ከንፈር ከመምጠጥ የተሻለ አማራጭ ማሰገኘት ባለመቻላችን ወይም ሌቦቹና ጋጥወጦቹ ስንሰራፋ ባለመታገላችን ያው ከወስላታዎቹ ተለይተን የምንታይ አደለንም!

 

ቢያንስ አፋችንን ስንከፍት ለመተካከም ቢሆን! የችግር ቁስላችን ሲድን አገር ይጠቀማል ስንነቋቆር ቁስላችን የበለጠ ይከፋል!


የቁምነገር ሰው ይበለን!

Thursday, February 21, 2013

ሌላ አገር የለንም ያለንንም አገር ላሸባሪ አንሰጥም

zeryihun kassa
ስለ አሸባሪነት ስናነሳና ስንወያይ እያወራን ያለነው ስለ እስልምና አደለም

እስልምናን ከአሸባሪነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም

ቁምነገሩ አሸባሪዎቹ በስልምና ወይም በሌላ ሀይማኖት ስም የሚነሱና ህዝብ ለሀይማኖቱ ያለውን ፍቅርና ጽናት ስለሚያውቁት በጸያፍ ድርጊታቸው ምክንያት ሲታሰሩ ወይም በህጉ ሲታደኑ

ለሀይማኖቱ ፍቅር ያለውን ህዝብ ሀይማኖተኞች ስለሆንን ታሰርን ለሀይማኖታችን ስለሰራን ታሰርን በሚል የሚታወቅ ግን ቅጥፈት የተሞላ የዘወትር ትርኢታቸው ለማነሳሳት በማሰብ ነው

አሸባሪ የሚገባውን ህጋዊ ቅጣት ያግኝ መንግስትም ይህንን በጥብቅ ይከታተል ስንል እንደ ዜጋ ሙስሊም ስለሆንም ክርስቲያን ስለሆንም የማናምን ለሀይማኖት ግድየለሾች ስለሆንም አደለም

ሰው በመሆናችን መጎዳት በወጣንበት በታክሲ በሆነ ሆቴል ወይም ሀይማኖታዊ ቦታ በፈነዳ ቦንብ ህይወታችን እንዳያልፍ ስለምንሻ ብቻ ነው

ደህንነታችን እንዲጠበቅ ሀይማኖተኛ መሆን የለብንም ይሄ ሰው በመሆናችን የምንጋራው የዜግነት ህጋዊ የመጠበቅ መብታችን ነው

እናም ስለ አሸባሪ ስናወራ ከክቡሩ ሀይማኖተኛ ከአፍቃሪው ከአክባሪው ሀይማኖተኛ እንኩዋንና ሊጎዳ ቀርቶ የተቸገሩ የሚረዳውን ሀይማኖተኛ እየወቀረን አደለም

አሸባሪዎች ስለ እናንተ ሲጻፍ እናንተ ስትወገዙ ክቡሩን ሀይማኖተኛ አወገዙት እያላችሁ አታውጁ ይሄ ህዝብ ስንኳንስና ህጋዊ ጥበቃ የሚያደርግለት ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ባለበት ዛሬ ይቅርና

ለሀይማኖቱ ህጋዊ ጥበቃ በማይደረግበት ግዜም ተከባብሮና ተቻችሎ የኖረ የብስለት ተምሳሌት ነው

እውነቱ ይህ ነው ማንም ይላካችሁ ማን አባይ መገደቡ አይቀርም በተያዘለት ግዜም ያልቃል ከነችግሮቿ አገራችንም ማደጓን ትቀጥላለች በሶማልያም ይሁን በኤርትራ በኩል ሊያሸብሩን የሚሞክሩም ቢኖሩ ከነቅጥረኞቻቸው ይከስራሉ ዳግም ወደኋላ አናይም ሽቅብ ጉዞ ጀምረናል አንመለስም!!!

ችግሮች ስለለሉ አደለም የማንመለሰው ችግር የመፍቻውን ቁልፍ ስለታጠቅን ነው የቀረውን ተግባርና ውይይት እየፈቱት በመዳህም በመወላከፍም በመራመድም በመሮጥም እንወጣዋለን

በማሸበርም በሌላም መንገድ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማሳካት የሚራወጡ ውጫዊም ይሁኑ የውስጥ ስሁታንም በተግባር ህዝቡን ያውቁታል!! እዚህ አገር በሀገር አይቀለድም!!!

ኢትዮፕያ ለዘላለም ትኑር!!!  ሀይማኖታዊ መቻቻሉም ለዘላለም ይኖራል!!!

ክብርህን ከነሱ አትፈልግ በጉያህ ሳለልህ

Zeryihun Kassa


ለአንድ አህጉራዊ ስብሰባ በሄድኩበት ምሳ እየበላን አንድ እዚያው የተዋወኩት ሰው 

ዜድ የኛ አገር ሰዎች አለማቀፍ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋሞች ውስጥ የሚሰሩትን ጨምሮ ለፈረንጅ እና ለሀበሻ የሚሰጡት ክብር ይለያያል 

በዚህም የተነሳ የሀገር ውስጥ አለማቀፍ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን መጠቀም መተው እየተገደድን ነው አለኝ

ለምሳሌ የአየር መንገድ ሆስቴሶች ፈረንጅን የሚያዩበት አይን ተወው ለኛ ግን.... እናም ለበረራ የውጭ አየር መንገዶችን የሚጠቀሙ አሉ... ይህ አተያይ አስጠልቷቸው አለኝ

በኔ እይታ የከበርን መሆናችንን ለማወቅ ራሳችንን ቀና አድርገን ለመሄድ የነማንም የመስተንግዶ መልክና አመለካከት የሚያስፈልገን አይመስለኝም

ክብርህን በሌሎች አመለካከት እና ባህርይ ውስጥ አትፈልገው

አብሮህ የተፈጠረ በሰውነትህ ውስጥ የሚንተገተግ ባንተው እይታ መፋፋትና መጠውለግ ልክ የሚከስም ወይም ወደ ላቀ ደረጃ የሚደርስ እንጂ በነማንም የአገልግሎት አሰጣጥ ቁመና ውስጥ የሚታጨቅ አደለም

እነ እገሌ የሚገባንን ክብር ስላላሳዩን አንዋረድም አገራዊ ተቋሞቻችንን መጠቀምም አናቆምም

አንድ ነገር ግን እናውቃለን የሰው ክብር ከምን እንደሚመነጭ የማናቅ ክብርን በቆዳ ቀለም የምንመዝን መብሰል የሚቀረን አገልጋዮች መኖራችንን

ይህም መሆኑ እንዲያ ያየነውን ሰው ክብር አያሳንስም የዚህ አመለካከት ተግባሪ የሆነውን ሰዎች አመለካከት አለመብሰልን ነው የሚያሳየው

ክቡርነትህን ከነከሌ ኪስ እና አገልግሎት የምትሻው ከሆነ እንደ ተቃጠልቅ ትዘልቃለህ

ክቡር ሰው መሆንህን ማወቅ ባከበሩህም በናቁህም ሰዎች ፊት አንገትህን ቀና አድርገህ መሄድ ያንተ ፈንታ ነው

በማንነትህ ውስጥ የታተመውን ክቡርነት ከነሱ አተያይ እና አገልገሎት አትሻው!!!

እመለስበታለሁ!!!!

Monday, February 11, 2013

ሀይማኖት አሸባሪነትና ኢትዮጵያ



ቁምነገር 1
የትኛውም አገር አሸባሪነት ያሰጋኛል በመሆኑም ሀይማኖትን ተንተርሶም ይምጣ የፖለቲካ ቅራኔዎችን መነሻ አድርጎ አሸባሪነትን ነቅቶ መጠበቅ ብልህነት ነው የሚል አቋም ቢይዝ ምንም የሚገርም ነገር የለውም::

በተለይ በኛ ሁኔታ ደግሞ አልሸባብ እና የኤርትራ መንግስት የሚያሰማ[ቸው አሸባሪዎች በተለያየ ወቅት የሚደቅኑት ስጋት ከሞኖሩ አንጻር ነቅቶ መጠበቅ በአዲስ አበባ ከዚህ በፊት የተፈጸሙት ጥቃቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ከማድረግም በላይ ህዝብ የተለያዩ ልማታዊ እንቅስቃሴዎቹን በዚህ የተነሳ እንዳያቋርጥ ማስቻልም ነው::

ህዝቤ ብዬ ለመጥራት የማላፍርበት ህዝብ ሀይማኖተኛ ነው:: ቅጥረኛ አሸባሪዎችን የማይሸከምና ሀገሩን የሚወድ መሆኑንም መሳት የዋህነት ነው:: ሀይማኖቱን የሚወድ ህዝብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀይማኖቱን ተገን አድርገው የሚመጡበትን ከሀዲዎች አይምራቸውም:: እምነቱን የሚኖረው ሀገሩ ስትኖር ስለመሆኑ አይስትም::

ቁምነገር 2
ሀይማኖት የግለሰብ ምርጫ ነው:: አንድ ማንኛውም ዜጋ ያመነበትን ሀይማኖት የመከተል ነጻነት አለው::
ከዚህ አልፎም ሀይማኖቱን በጸሎት በስግደት በምስጋና በቅዳሴ በበአላት ማክበር መተግበር የሚችልበት የተሟላ ነጻነቱን እየኖረው ያለ ህዝብ ነው::
በአምልኮ ቦታ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በሀይማኖቱ ተከታዮች ያለማንም ጣልቃ ገብነት መፈታት አለበት ብሎ የሚያምን በዚሁ መልኩ ሀይማኖቱን በአግባቡ እንዳይፈጽም በተከለከለበት ግዜም ሳይቀር ተቻችሎ የኖረ ህዝብ::

ዛሬ ዛሬ የዚህን ለአለም አብነት የሆነ ህዝብ ባህል የሚበረዙ አዝማሚያዎች እናስተውላለን:: አብሮ መጠጣት መብላቱን ነውር ለማስመሰል የሚጥሩ ደራሽ አዋቂዎች& የመቻቻሉን ብስለት የፍርሀት የሚያደርጉበት ደራሽ ጀግኖች& ልዩነቶቹን ተወያይቶ በሽማግሌ የመፍታት ልምዱን የመሀይምናን ገባኤ ጉዳይ የሚያስመስሉ ሳይደቁኑ የሚÆስሱ አሜኬላዎች::

ሳይገባቸወም ሳይገባቸውም (ይጠብቃል) የስብከቱን ሜዳ የረገጡ የነገሩንን አሜኬላ ቸል ብለን ዝም ስላልን የሚነግሩን መለኝነት የጎደለው ሀሳብ ሄዶ ሄዶ ምን እንደሚያስከትል መገመት የሚሳነን የሚመስላቸው አውቀውትም ሳያውቁም የዚህች አገር መለወጥ ለማይዋጥላቸው ጠላቶቻችን ቅጥረኛ እየሆኑ ያሉ ሀይማኖተኛ ስም ያላቸው አሜኬላዎች አሉን::

በርካታ ሰባክያን አሏት እቺ አገር በስልምናም በክርስትናም::  ሁሉም ሰባኪ አደለም አብዛኛው ሰባኪ አሸባሪ የሚል ታርጋ አልተለጠፈለትም:: እጅግ በቁጥራቸው የሚያንሱ ህጉ ከሚፈቅድላቸው ቅጥር አልፈዋል በሚል ክስ ታስረው ሊሆን ይችላል::
በርግጥ የተከሰሱበትን ወንጀል ፈጽመዋል አልፈጸሙም ፍርድ ቤት የሚሰጠው ብያኔ ሆኖ አገር የሽብር ጥርጣሬ አስግቷት ያደረገችው ከሆነ ግን ሀይማኖተኞችን እንዴት ያስራል መንግሰት የሚል ጥያቄ መነሳት አለበት ብዬ አላምንም::

በሀይማኖት ሽፋን ስንቱ እንደተቀጨና እስከዛሬም እንደሚቀጭ በየለቱ የምንሰማው ነው:: በሀይማኖት ሽፋን ስንቱ ሀሺሽ እያበቀለ በሀሺሽ ህሊና እያጦዘ ሽብር እንደሚፈጽም በደም የተነከሩ ምስሎችን በየቀኑ እያየን የምናውቀው ነው::

ጥያቄው ማነው እሱ አደለም መጠየቅ ያለበት ምን አደረገ ምን እየሰራ ነው የሚለው ነው::  ማንነታቸውን ሸፍነው ስንት አስነዋሪ ነገር የፈጸሙና የሚፈጽሙ ስለምናውቅ ማንነታቸው ሊያዘናጋን ይገባል የሚል እምነት የለኝም:: መመልከት ተግባራቸውን መመርመር ድረጊታቸውን ነው ተግባር ዋሽቶ አያውቅምና::


ቁምነገር 3
የሀይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ተብሎ እንዳንናገር አፋችን እንዳንሰራ እጃችን ታስሮ የምንወዳት ሀገራችን ስትታመስ የምንወደው ህዝባችን በወጣበት ሲቀር ማየት አንሻም::

በሀይማኖቱ ጣልቃ አንገባም እንጂ ሀይማኖቱን ከለላ አድርጎ ዉሏችንን እንዲያበላሸው ለማንም አንፈቅድም ሌላ አገር የለንም::
በታመሰ አገር ሀይማኖታችንን አንኖረውም:: በሌሎች አገር የምናየው መተራመስ ፍንዳታ እንዲገርፈን አንፈልግም:: ለችግሩ ድህነታቸን መች አነሰን ሌላ ካንሰር ልንጨምር ይቅርና::
በመሆኑም መንግሰት በሀይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም በሚል መዝሙር  እንዳሻን እንዘውር የሚባልባት አገር መሆን የለባትም::

ሰው መሆን ይቀድማል ሰውነት ደግሞ መንፈስን ብቻ የያዘ አደለም:: አካል ህሊና ማህበራዊነት የመሳሰሉ ሌሎች ተፈጥሯዊ ፍላጎቶችና ተፈጥሮ አለን:: ሁሉን በልኩ በሚዛኑ መያዝ መልመድ መብሰል ነው::
እስከሚገባኝ ድረስ ሀይማኖተኝነት አምቧጓሮ አደለም እንዲያውም ባለመግባባት ውስጥም ተቻችሎ ተዋዶ መኖርን የሚያስችል ቁመና ነው::

የለም የለም ይሄ የሀይማኖት ጉዳይ ነው እንዴት እንናገራለን የሚባል ቀልድ መኖር የለበትም:: ሀይማኖተኛና ሀይማኖት መከበርና ህጋዊ ጥበቃ ማግኘት አለባቸው:: ያም ሆኖ የሚደረግላቸው ጥበቃ ግን ገደብ የለሽና ሌሎቹን እሴቶቻችንን የሚያጎድፉ እንዲሆን ሊፈቀድ አይገባም:: ቁሙ ቅጥሩ እዚህ ድረስ ነው መባል አለባቸው::

ህዝባችን ሀይማኖተኛ ነው ለሀይማኖቱ ተቆርቋሪ ነው በሀይማኖት ስም  አሸባሪነትን የሚጭኑበት ልል ማህበረሰብ ግን አደለም:: ይሄ ህዝብ እንደ ንብ ብሄራዊ ጸጥታውን የሚያደፈርሱበትን በራ ከመመከት ወደኋላ አይልም::

እመለስበታለሁ!!!!



Saturday, February 9, 2013

Meles Zenawi didn't live for legacy?!

         
  Zeryihun Kassa


Many think as if the talk about Meles Zenawi's legacy is to paint him a big personality cult. As far as I see it, he lived in how and what he believed in with tangible consequences.


The legacy he left behind is for our lesson if at all we are bright enough to learn from the life of other people especially from such committed figures like Meles Zenawi whether we shared his views or not.


The character he demonstrated over the years, the long hours he worked to get his visions done, his articulation of issues unmatched by his opponents and his tall role as member of EPRDF were things we can learn from.


One may not share his view of the world and his political inclination but everyone can learn from the kind of devotion he put into his work, the ambitions he set, the servant of the people he was.... and a lot more can really help us identify our roles to engage in fruitful purposes that set us free from the age long poverty and backwardness that we have begun to unravel over the last decade or so.


Meles lived his time and he is gone. It doesn't matter what we feel and believe about him. Whether we set up a personality cult around him or not it doesn't at all help him a bit.


After all he lived every bit of his life in good days and bad days; I think he had nothing to blame himself for as he did what he believed in with ways he saw fit for the purpose. Many of the strategies worked as he and his colleagues plot them; few failed them of course.


What matters is he was open to learn from what went right and wrong; he didn't like to gloat over his victories and he also didn't enjoy being unkind of his efforts just for some of his parties efforts went wrong. He took the lessons with his comrades and moved on.


Here I believe those of us who are around have a lot to learn from this big figure whether we are opponents or supporters. The character he illustrated all through the way beginning from his early days are principled and well footed. Above all in every policy and strategy he set, I see proactive moves that essentially sees things from inside out.


For instance, he doesn't pin our hopes of peace with the turmoils in the sub region. He rather rightly relates them with how we govern our own country Ethiopia. So long as I know he did always say this nation can only be developed as much as we the people of Ethiopia are committed to do so.


If anybody is not contented with the pace and quality of development of this great nation, then it is up to him to make his contribution as best as he can. Of course, nobody has the privilege of criticizing others; on the contrary every body has the natural right and national duty to set one's foot's print in the development of this beloved nation we call home.


Meles left his foot print for good. Some believe he did the wrong way. At least the best things for us is not to form one and same view but to engage in constructive services plus actions to help move this nation a step forward.


This kinds of actions counts and matters. Cheap talks are cheap, let us engage in dear investments: choosing to work to serve the best we can to the people we often reiterate that we love.


I believe love is a verb and it is actions that speaks well about love, not weird criticisms. I hope we be light and model not critic and pain in the back of those who try and do something they see important to help this country go forward.