Thursday, April 25, 2013

አንድ ብቁ አማራጭ ብቻ የነበረበት ምርጫ


የባለፈው ምርጫ ብዙዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎቻችን በርግጥም በአማራጭነት የቀረቡ የፖለቲካ አቅሞች ሳይሆኑ የፖለቲካውን መድረክ ቅንጥብጣቢ ጥቅማጥቅም መሰብሰብያ ያደረጉት መሆኑን ያሳያል$

በአንድ በኩል ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት ፓርቲዎች የተጠናና ጠንካራ የፖሊሲ አማራጮች አቅርበው ለምርጫው ይህ ነው የሚባል መነቃቃት ያላበረከቱበት$ በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዴግን ደከመ ብለው ለተቹበት ጉዳይ የሚያቀርቡት አማራጭ ደግሞ "ፈሪሀ እግዚአብሄር ያለን ፓርቲ ነን" ከሚል ግርድፍ ቃልኪዳን ማለፍ የተሳነው መሆኑን ታዝበናል$

ወደ ምርጫው ያለገቡት ፓርቲዎች ደግሞ በኔ እይታ በምርጫው ባለመሳተፍ አማራጭ የለለው ምርጫ ተከናወነ የሚል ቅኝት ሊያስደምጡን መቋመጣቸውን ታዝቤያለሁላለመወዳደር ምክንያት የሆናቸውን ጉዳይ ባብራሩባቸው መድረኮች የምርጫ አጀንዳቸውን ማራመድ አይችሉም ነበር የሚል ግምገማ የለኝም$

ለ33 ፓርቲዎች ሁነኛ አጀንዳቸው ላናሸንፍ ኢህአዴግን ከምናጅበው ያንንም ይሄንንም ጠቅሰን አንሳተፍም ተሳትፏችንን እንሰርዝ$ ምርጫው ሲከናወን ደግሞ አማራጭ የሌለው ምርጫ ስለመሆኑ እንስበክ በሚል ያከናወኑት የተዋጣለት የማጣጣል ድራማ ነበር$

በሌላ በኩል ደግሞ ይሄ ድራማ የገባው ኢህአዴግ በምርጫው የሚይሳተፉ ተቃዋሚዎች ኖሩም አልኖሩም ህዝቡ የመምረጥ መብቱን የሚጠቀምበት እና በምርጫው ለውድድር ከቀረቡት እጅጉኑ የሚሻል በተግባር የተፈተነ ፖሊሲና አፈጻጸም ያለኝ መሆኑን የማሳይበት ህዝቡም በነቂስ ወጥቶ ይሄንኑ ፖሊሲና አፈጻጸም እውቅና እንዲሰጠው ለማድረግ እተጋለው በሚል መንፈስ ሰርቷል$

በርግጥም ይሄ እቅዱ ኢህአዴግ የሰመረለት ይመስላል$ በአዲስ አበባ እንኳ ከተመዘገበው መራጭ 65 በመቶው መርጧል$ መጀመሪያውንም መምረጥ ከሚችለው ከዚሁ ቁጥር የሚልቀው ተመዝግቧል$ በየትኛውም በዴሞክራሲ የላቀ ልምድ አለው በሚባል አገር ምርጫ ጋር ሲነጻጸር የተመዘገበውም የመረጠውም ህዝብ ብዛት ከፍተኛ ነው$

በኔ ትዝብት ኢህአዴግ አባላቱን እና ደጋፊዎቹን በየቤቱ እየሄዱ ነዋሪው በምርጫ እንዲሳተፍ የመቀስቀስ ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ ችሏል$ ይሄ ልምድ ፓርቲው በሚያጋጥሙት የወደፊት ምርጫዎች በቅስቀሳ ዙርያ አባላቱ ሰፊ ልምድ እንዲቀስሙ ያስቻለ ነው$ ኢህአዴግ ወጣም ወረደም ተቃዋሚዎች ተሳተፉም አልተሳተፉም በያንዳንዱ ምርጫ የአባላቱን ምርጫ የማቀድ የመምራት የመቀስቀስ ነዋሪዎችን በየቤታቸው ሄዶ በማወያየትና እንዲመርጡት በመቀስቀስ ረገድ ሰፊ ልምድ እና ክህሎት እንዲቀስሙ በማድረግ ረገድ የተሳካ ስራ እየሰራ ነው$

በየሰው ቤቱ ሄዶ መቀስቀስ ከባድ ስራ ነው$ ያስፈራል ያሳፍራል ልምድ የሌለን ከመሆኑ የተነሳ$ ይሄን ሰብረው እንዲሰሩ ማድረግ መቻሉ ኢህአዴግ ቀላል ግምት የሚሰጠው አደለም$ ሌላው ደግሞ ይህንን በመሰለው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የሚያሳትፈው ከፍተኛ አመራሩንና መካከለኛ አመራሩን ሁሉ በማሳተፍ ጭምር መሆኑ በዚህ ረገድ ሰፊ ልምድ መቅሰም የቻለበት እንደሆነ ይታመናል$

እኔ የበርካታው ተቃዋሚ ምርጫን በማጣጣልና ባለመሳተፍ የሚገለጠው ልምድ ኢህአዴግ ዴሞክራቲክ አለመሆኑን ከማሳየት ይልቅ ሲመረጡም የተመረጡበት ሀላፊነት መውሰድ የማይችሉ በአመዛኙ ደግሞ በምርጫ ከመሳተፍ ይልቅ ምርጫ ባለመሳተፍም ጭምር ኢህአዴግን ማጣጣል የተጸናወታቸው ናቸው ወደሚል ድምዳሜ ቀድሞውኑ ያመራውን አብዛኛውን ህዝብ በተቃዋሚው ጭራሹኑ ተስፋ እንዳይቆርጥ የሚል ስጋት አለኝ$

በኔ እምነት ኢህአዴግን ነጥብ ለማስጣል ምርጫን ባለመሳተፍ ጭምር የሚካሄደው የተቃዋሚ ሀይሎቻችን ትግል ተስፋ የማይደረግባቸው ተወዳዳሪ የፖሊሲ አማራጭ አቅርበው መሸናነፍ የማይችሉና የጋዜጣ ላይ ዘራፍ ባዮች ብቻ እየሆኑ እንዳይሄዱ የሚል ግምት አለኝ$

የሆነ ሆኖ አማራጭ ለኔ የቁጥር ብዛት አደለም$ ሲጀመር ያልተሳተፉት 33 ፓርቲዎች የአቋም የፖለሲ ልዩነት የፈጠራቸው ናቸው ወይስ እንደ እድር የፖለቲካ ፓርቲ በማቋቋም የሚገኝ ሽርፍራፊ ገንዘብ ፍለጋ ነው$ የምር ለሀገራዊ ችግሮቻችን መፍትሄ ተብለው የቀረቡ ሀምሳ እና ስልሳ አማራጮች አሉ ወይስ በጉዳይ ዙርያ ሳይሆን በጥቅም ዙርያ የተሰባሰቡ  የምርጫ ቦርድን በጀት የሚከፋፈሉ ፓርቲዎች ናቸው ያሉን$

እንደኔ አንደኔ ከአብዘኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምሰማው አማራጭ ይልቅ ከፌስቡክ ጓደኞቼ እና ብሎገሮች የማገኘው አማራጭ ይልቃል$ እውነቱን ፍርጥ ካደረግነው አበዛኞቹ ፓለቲካ የማያውቁ ፖለቲከኞች ናቸው ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅማጥቅም ለመቀራመት የተሰባሰቡ ቡድኖች$ ይሄ በርጥም የአገራቸው ጉዳይ አሳስቧቸው የምር አመራጭ ለማቅረብ እየሞከሩ ያሉትን አይመለከትም$

በኔ ግምገማ አማራጭ ያጣነው ተቃዋሚ ፓርቲዎቻችን ህዝባዊ ጥያቄዎችን ሳይሆን በፓርቲ ዙርያ ይገኛሉ ተብለው የሚታሰቡ ጥቅሞችን ለማሰባሰብ የተደራጁና ከዚህም አለፍ ሲል አማራጭ በማቅረብ ሳይሆን ከኢህአዴግ ይልቅ መፍትሄውን ማከናወን የሚችሉ ሀይሎች መሆናቸውን በማሳየት ሳይሆን ኢህአዴግን ራሱን በማጥላላት ለዚሁ የማብጠልጠል ብቃታቸው ሀገር የመምራት ሀላፊነት እንዲቸራቸው የሚፈልጉ ዋታቾች በመሆናቸው ነው$

ትጉህ አጣጣዮች ሆነው ሊሆን ይችላል የችግሩ መፍትሄ መሆናቸውን ግን ዛሬም ማስጨበጥ አልቻሉም$ አማራጭ ፓሊሲም የላቸውም$ በመሆኑም ዛሬም ያለው የተሻለው አማራጭ ኢህአዴግ ብቻ ሆኖ ቀጥሏል$ እኔ እስከሚገባኝ ኢህአዴግ አማራጭ አይፈጥርም ይልቁንም ኢህአዴግ ራሱን የተሻለው አማራጭ አድርጎ ያቀርባል$ ኢህአዴግ እስከሚያመቻችላቸው የሚጠብቁ ፓርቲዎች መቼም አማራጭ የመሆን እድል የላቸውም$

ይቆየን!

Wednesday, April 24, 2013

Election with only one able alternative

First some opposition parties decided not to participate in the elections hoping to criminalize EPRDF.

Then they say because we are out of the elections the public is not going to actively participate in the elections.

Once they know over 30 million voters are registered they say it is because they were obliged to go out for registration.

Once the votes happen and the turn out is big; they claim EPRDF runs alone and wins the election with no apparent alternative.

There is no logic and truth to it that says when opposition A is not in the election, the election has no alternative while opposition C, D and E are part of the election.

The fact of the matter is oppositions like Medrek can't field as many candidates as they claim on weekly papers. They don't even have a registered member let alone candidates that can stand in the elections.

For me the truth is the radical opposition don't like to see how small they are in real value by going for the elections and decline to take part to save their breath may be for 2007 national election.

Time for the opposition to sit back and make thorough assessment of themselves to come ever stronger. Rumor and rants on weekly papers can't and won't create credible and competent opposition.

I believe one able party respects the elections and go for it; dominantly the public commends its effort while it openly tells EPRDF to correct the mistakes discussed in forums across Addis at the least.

Monday, April 22, 2013

ሀገሩን የሚጎዳ ሀገር ወዳድ

ሀገሬን እውዳለሁ የሚል አንድ ገጽ ወሬ ገልበጥ ሳይል እንኳ ሀገሩን የሚጎዳ ተግባር ሲፈጽም የምናየው ዜጋ ብዙ ነው።

የሀገር ፍቅር በአፍ አደለም የሀገር ፍቅር በእጅ ነው። ስትጮህ አይሰማኝም በርግጥ ያደነቁራል ስትሰራ ግን አምንሀለው ነው ነገሩ። የሀገር ፍቅር ቀረርቶ አደለም። የሀገር ፍቅር አንዲት ፍሬ ችግር ለህዝብህና ለራስህ መፍታት ከቻልክ በዚያ ይገለጣል።

የእህል እጥረት አለ እውነት ነው። እርይ እርይ የእህል እጥረት አለ ማለት ግን የሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ስንኳንስና የላቀ ሚናው ተራ አጀንዳው አደለም። ሀገር ወዳዱ አንዲት ጋት ይህን የእህል እጥረት መፍታት የሚችል ምርምር ከሰራ ዘመናዊ ማረሻ ካዘጋጀ የተሻሻለ አስተራረስ ለአርሶ አደሩ ማሳየት ከቻለ የምርት አሰባሰብ በዘመናዊ መንገድ እንዲሰራ በማድረግ እስከአንድ ሶስተኛው ምርት የሚባክንበትን ሁኔታ ካስቀረ ወይም ለማስቀረት ላይ ታች ካለ ይሄ በርግጥም ሀገር ወዳድ ነው።

ወይ የእህል እጥረቱን ለማስቀረት የሚያስችሉ ዘይቤዎችን እንዳንሰማ ወይ ደግሞ ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል መፍትሄ እንዳንፈልግ በፋይዳ አልባ ጫጫታቸው የሚረብሹን የዘወትር ከሳሾች መባከናቸው ሳያንስ ሌሎቻችንንም ሊያባክኑን ስለሆነ እንዳይጮሁ ማድረግ ባንችልም ጫጫታቸውን ቸል ብለን በርግጥም የእህል እጥረቱን በሚፈቱ ጉዳዮች ላይ ልናቱኩር ይገባል። እነዚህ ሀገር የሚጎዱ ሀገር ወዳዶች ናቸውና።

ሰው ስራ አይሰራም ሰነፍ ነው ኡኡ ባለስልጣኑ ሌባ ነው ነጋዴውም ሆዳም ነው ጋዜጦቹን እኛ የማንፈልገውን ከተናገሩ አጭበርባሪዎች ናቸው። ጎብዝ ሀገር ሊቀየር ከሆነ ሰልፍ ስንጠራህ ውጣ እነዚህ በወጉም ያልበቁህን ባሶች አቃጥል ስንልህ ያለማቅማማት አውድም እኛ ካልሰተሳተፍን ምርጫ አማራጭ የለውም እኛ ካልተመረጥን ምርጫ ፍትሀዊ አደለም የሚሉህ ተቃዋሚዎች ሀገር የሚጎዱ ሀገር የሚወዱ ልጆችህ ናቸው። እነሱው ጻድቅ እነሱው ፈራጅ እነሱው ጯሂ እነሱው ታማኝ።

ተሸነፍኩ ማለት ሞቱ የሆነበት ተቃዋሚ ዴሞክራሲ ስላልገባው የቤት ስራውን እስኪጨርስ በምርጫው ባይሳተፍ እንደ ምርጫ ማጣት መታየት የለበትም። ሲጀመር በምርጫ አያምንም ሲጀመር ሌላኛው አማራጭ ሊረታኝ ይችላል ብሎ ስለማያምን ተወዳዳሪ ሳይሆን የለየለት ያለኔ ተመራጭ ያለኔ አሸናፊ ያለኔ ምሁር ማነው የሚል የአስተሳሰብ ህመም ያለበት ሀገር የሚጎዳ ሀገር ወዳድ ነው።

ኢህአዴግ የተሸነፈ ለት ነው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የነበረው ኢህአዴግ ሲያሸንፍ የመጭበርበሩ ማሳያ ነው የሚል ሽንፈትን የማያምን ሁነኛ የአስተሳሰብ ስብራቱን መጠገን የተሳነው የተመዘገበ የሚታወቅ አባል ሳይኖረው አቅሜን ፈርታችሁት ነው እያለ በየጋዜጣ የጫጫታ ቁመናው ራሱን በተሳሳተ መስተዋት የሚያይ ከኔ ሌላ አማራጭ የለም የሚል ግን በተመሳሳይ ችግር ሌት ተቀን ኢህአዴግን የሚወቅስ በሚወነጅልበት ጉዳይ እንኳ ሳይቀር የወደቀ ተቃዋሚ መያዝ ሀገር የሚጎዱ ሀገር የሚወዱ ግለሰቦች የመሸከም ማሳያ ነው።

የዚህ ሀገር ፖለቲካዊም ሆኑ ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች በሰሞንኛ የጋዜጣ ጫጫታ የሚቋጩ አደሉም። የጠራ የመታገያ ግብ የጠራ ፖሊሲ በዚያ ዙርያ የተሰለፈ ገና ከጅምሩ በዲሞክራሲያዊ አሰራር ውስጡን ያነጸ ፖለቲካ ይሻል። ለጥቆ በየሞያችን ሳናሰልስ ምርጥ የሚባለውን አስተዋጾ ማበርከት የቻልን እንደሆነ ነው አገር የሚጠቀመው። አገርህን ስትጠቅም ሀገርህን መውደድህን እናውቃለን።

ሀገራችንን በተግባራችን ስለመውደዳችን እርግጠኛ እንሁን እወዳታለሁ ማለትማ ምላስ ይላል ቁምነገሩ እጅህ የጨበጠው ጠቃሚ መሆን አለመሆኑ ነው።

አድርባይነትና የኢህአዴግ ውስጠ-ፓርቲ ትግል


የውስጠ ፓርቲ ትግል በተለይም የገዢ ፓርቲ የውስጥ ርስበርስ መተጋገል ባህል አመለካከቶችን የመቃኘት አዝማሚያዎችን እና የተሳሳቱ ተግባሮችን የማረም ብልሹ አሰራሮችን የመከላከልና ሲፈጠሩም በፍጥነት የማረም አቅም አለው።

ይሄ የሚሆነው ፓርቲው ውስጣዊ ባህሪው ለትግል የሚመቹ አሰራሮች ያሉት በግቡ ዙርያ መተጋገልን መሰረት ያደረጉና የአስተሳሰብ ፍጭቶችን ማስተናገድ የሚቸሉ እንደሆነ ነው። አባላትም በነዚሁ የመታገያ ግቦች ዙርያ ለመታገል የሚገደዱበት ባህልና አሰራር የተፈጠረ እንደሆነ ነው።

በፓርቲው ውስጥ የሚታዩ ውስጠ ትግልን የሚያሟሙቱ በግብ ዙርያ የሚሰባሰቡ ሳይሆን በአለቆችና አለቆች ሊያስገኙ በሚችሉት የሹመትና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ዙርያ የተሰለፉ ቡድኖች እንዳሉ መታዘብ ይቻላል።

በተለያዩ ግምገማዎች እንደሚስተዋለው አንዲህ አይነቱን ተግባር በግልጽ ለማስኬድ የሚፈራ ቁመና ቢኖራቸውም በግል ጥቅማቸው ዙርያ ተሰባስበው አለቆችን በማሞካሸትና በመከላከል የአለቆች ተቆርቋሪ መስሎ በመቅረብ ፍርፋሪ ሹመትና መሰል ጥቅሞች ለማስጠበቅ የሚሰሩ ቀላል ግምት የማይሰጣቸው አባላት አሉ።

እኚሁ አባሎች በአባልነት ለመቀላቀል የነበራቸውም አነሳሽ ምክንያት ይሄን የጥቅም ርሀባቸውን የገዢው ፓርቲ አባል በመሆን ማሳካት እንደሚችሉ ማለማቸው ነው። የትኛውም የድርጅቱ ግብ መሳካት አለመሳካት ቁብ አይሰጣቸውም። ዋናው አጀንዳቸው ጥቅማቸው ነው። ጥቅማቸው ደግሞ የሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲሳካ የኛም ጥቅም እግረመንገድ የሚጠበቅ ይሆናል በሚል እምነት የሚቀነቀን አደለም።

እንዲያውም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚሰሩት ግቡን በሚደፍቅ ማንኛውም አማራጭ ሁሉ ነው። ግባቸው ጥቅማቸው እንጂ ህዝባዊ ተጠቃሚነት አደለምና። በመሆኑም ፓርቲው በከፍተኛ መጠን እያሰባሰበ ያለውን አባል በአገራዊ ጉዳዮች ዙርያ ማሰለፍ የሚያስችለው ውስጣዊ መዋቅር በየግዜው እየከለሰ አባላቱን እያታገለ ትግሉ ይበልጥ በተግባር እያነጻቸው እንዲሄዱ የሚያሰችል ውስጣዊ ሁኔታ መፍጠር መቻል ይኖርበታል። አንገብጋቢ የወቅቱ ስራም መሆን አለበት የሚል እምነት አለኝ።

ከዚህ አንጻር የኢህአዴግን ውስጣዊ ዲሞክራሲያዊ ትግልና አሰራር እያኮላሸ ያለውን ሰፊ የአድርባይነት ልምድና ተግባር ከበቀለበት መነሻ አስተሳሰብ ጋር ማክሰም የሚያስችል ቅኝት መንደፍ ይህንኑ አተያይ የእለት ተለት ተግባራዊ መመርያ የማድረግ እና በሂደት ከማይናወጥ የፓርቲ መሰረታውያን አንዱ ለማድረግ ትልቅ ስራ ያሻል።

ይህ አይነቱ ልምድ ከፓርቲው አይነኬ ልምዶች መካከል የሚገባው ደግሞ በአተያይ ልቆ በተግባር ደምቆ የአሰራር መሰረቶች ተጥለውለት በማይናወጥ ማህተም ዘላቂነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ ነው።

በአድርባይ አሰራር ተጠቃሚ የነበሩ ቀላል የማይባሉ አባላት በቀጥታ ለአድርባይነት በአደባባይ ባይታገሉም ውስጥ ውስጡን በትግል ላይ የሚመሰረተውን ግብ ፈለቅ አካሄድ የማብጠልጠል ድክመቶችን የማጉላት አዝማምያ ሊከተሉ የሚችሉበት እድል አይኖርም ብሎ ማሰብ የዋህነት ይሆናል። በዚህም በኩል የትግል አብነት መስሎ ለመምጣት የማያቅማሙ በመሆኑ ይሄን በንቃት መከታተል ተገቢ ነው።

የአድርባይነቱ መብቀያ
በኔ እይታ ለአድርባይነት ለሙ መሬት መንግስታዊ እና ድርጅታዊ ስራዎች የሚመሩት ሀላፊዎች በሂደት የተጎናጸፉት ያሻቸውን ያለበቂ ምክንያት የመሾምና የማውረድ ስልጣን ነው። ይሄ ረጅም እጅ ነው አድርባይነትን የሚያበረታቱ አስተሳሰቦችን እና ተግባሮችን እያነጸ ያለው።

በተግባር ይሄ አስተሳሰብ ደግፈኝ ትሾማለህ ተቃወመኝ ቆመህ ትቀራለህ የሚል መፈክር ያለው ይመስላል። ይሄው ሁኔታ ለአድርባዮች ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።በመሆኑም ይሄ አሰራር በስፋት እስከቀጠለ ድረስ ይሄ አዝማምያ የመቃናት እድሉ ጠባብ ነው።

ሹመት ተለይቶ የሚታወቅ ግልጽ ዝርዝር አሰራር እንዲኖረው ቢደረግና ከአባላት መሀከል የሚደረግ ሹመት ደግሞ ብቃትን እና የትግል አስተዋጾን መነሻ አድርጎ በአባላት መሀከል በሚደረግ ግልጽ አሰራር በውድድር ወይም በሌላ ግልጽ አሰራር የማይፈጸም ከሆነ ካጫፍ ያለው ሀላፊ እጅ ርዝመትም ከታችና ከመሀል ያለው ሰራተኛና አባልም አጎንባሽነት ማብቂያ የሚገኝለት አይመስለኝም።

ስለሆነም በአስተሳሰብ ረገድ አባላት መተማመን እና ታማኝ መሆን ያለባቸው ለመስመር ለመታገያ ግቦች እንጂ ለወቅታዊ ተሿሚዎች መሆን አይችልም ከተሿሚ ጓዶቻቸው ጋር በመከባበር እና በመተጋገዝ መስራት እንጂ ሌላ ንክኪ ሊኖራቸው አይገባም። 

አባላት ስለ ላቀ ተጠቃሚነትም ያስቡም ከሆነ ጥቅም ማግኘት ያለባቸው ግቡ በአጠቃላይ ከሚፈጥረው ውጤትና በዚያ ሂደት በነበራቸው አስተዋጾ ልክ እንጂ በሌላ መልክ በመሞዳሞድ መሆን እንደሌለበት ማወቅ ይኖርባቸዋል። ይሄ አስተሳሰቡ ነው ይሄን አስተሳሰብ የሚደግፍ ማስፈጸም የሚችል አሰራርና እየተገመገመ የሚቀጥል አፈጻጸም እንዲኖር ማድረግ ይደር ይዋል የሚባል ስራ አይሆንም።

በኢህአዴግ ውስጥ እየተስዋለ ያለው ለግለሰብ ታማኝ በመሆን ጥቅም የማግበስበስ አዝማምያ በቶሎ መልክ ካልያዘ በቀር በሂደት ፓርቲው በሹማምንት ዙርያ በሚፈጠሩ የጥቅም ኪራይ ሰብሳቢ ቡድኖች መናጡ አይቀርም። 

የላቀው ግብ መስመሩ መሆኑ ይቀርና ስሌቱ ሃላፊያችን ምን ያስደሰታቸው ይሆን የሚል ጮሌ ቀመር ይሆናል። የዚ መጨረሻው ሁሉ ነገሩ ሀላፊዎችን ማደለብ ብቻ እንጂ ህዝባችንን እና የምንወዳትን ሀገር መሆን ይሳነዋል።

ለአድርባይነት ያጎነበሰች ህሊናችንን እና የደከመ ምርጫችንን ለመገምገም እና ለማረም ያብቃን። ኢህአዴግም በጉባኤው ቃል እንደገባው ይሄን የመፈጸም እድሉ እንደሚኖረው ተስፋ አደርጋለሁ። የገባኤው ውሳኔ መነሻ እንጂ የችግሩ መፍቻ ቁልፍ እንዳልሆነ ስለሚታወቅ።

በሚቀጥለው ጽሁፌ የአድርባይነትን መነሻዎችና ተጨባጭ መፍትሄዎች ለመጠቆም እሞክራለሁ።

አጋልጠው ይሸፍኑሻል - የሴት ዳሌና መቀመጫ


ይሄ የሱሪ የአጭር አላባሽና የሴቶቻችንን ግንኙነት አለመጣጣም የሚያሳብቅ የለትተለት ትእይንት ነው$ ሱሪው እስከ ወገብ አላባሹ ከዚያ ትንሽ ከፍ ብሎ የሚቀር አይን አፋር ነገር እንዲያውም አጋላጭ ሊባል ይችላል$ ሴቶቻችን ደግሞ ወደውትና መርጠውት አድርገው ሲያበቁ አለባበሳቸው የሚያምርም የሚያስጠላውንም መቀመጫቸውን ማጋለጡ ያሳፍራቸዋል$ 

ደስ የሚል አይነት ሀፍረት$ እነርሱም አጋላጭነቱ ደርሶ ያኔ ትዝ ብሏቸው የማይሸፍነውን አላባሽ ካልሸፈንክ ብለው ሲጎትቱ ሲጓተቱ ያ አጭር ማላበሻቸው መሸፈን ሲሳነው እንታዘባለን$

አዬ ዳሌና መቀመጫ አጋልጠው ይሸፍኑሻል ሸፍነው ያጋልጡሻል% ተውበውብሽ ያፍሩብሻል አፍረው ደግሞ ይዋቡብሻል$  እውነት እኮ ነው መሀል ላይ ያለ ነገር ሲሸፈንም ያምራል ሲጋለጥም ያፍራል!

አፍረው ቢሆን ኖሮ ወደው አይለብሱትም$ ወደው ካማሩበት ደግሞ ተመልካችን ለመመለስ መታገላቸው ተገቢ አይመስልም$ ዘፋኙ ደስ በሚል ስቃይ እንዳለው የሚያሳፍር ውበት ነው$ በተፈጥሮ ግን ደስ የሚል አያሳፍርም የሚያሳፍር ደግሞ ደስ አያሰኝም$

አጋልጠው ለተመልካች አስጥተው ሲያበቁ በል መለስ በል ክንብንብ በል ሲሉት አይመጣ$ እኛም አይናችን አያርፍ እንዳይታይባቸው የሚሸፋፍኑትን ግን የማይሸፈነውን የተጋለጠ ገላቸውን ለማየት እንደተሽቀዳደምን ይሄው በየታክሲው በየካፌው ሲቀመጠኑና ሲነሱ የነሱም መቀመጫቸው ተጋልጦ የኛም አይናችን ማግጦ ሌባና ፖሊስ እየተጫወትን$

እነሱ ያቺ ቆንጆ ዳሌና ባታቸውን እንቁልልጭ እንዳሉ እኛም ሌባና ፖሊስ አይነት ነገር አየሁሽ አየሁሽ እንዳልን አለን$ አጋልጠው የሚሸፍኑሽ ተጋልጠሽ የተሸፈንሽ ሊያሳዩሽ አዋጅ አዋጅ የሚሉሽ ዉበታቸው ደሞ እፍር ብለው ክንብንብ ሊያደርጉ የሚደክሙብሽ ሀፍረታቸው$ አዬ ዳሌና መቀመጫ እንዲህ ታደክሙን$ እኛ በማየት ሽቅድምድም እነሱ በማጋለጥና በሀፍረት$

አዬ ዳሌና መቀመጫ አጋልጠው ይሸፍኑሻል ሸፍነው ያጋልጡሻል አለ!?

በየአጋጣሚው ዝቅ ማለት የሚያስገድድ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው አንድ እጃቸው ከሚወዷት ለአለም ካጋለጡዋት ዳሌና መቀመጫቸው ተመልሳ ለመሸፈን ስትታገል አንድ እጃቸው የተላከችበትን መልእክት ለብቻዋ መፈጸም ሲሳናት እንታዘባለን$ ብቸኛው ግራ እጅ ሸፍን የተባለውን ሳይሸፍን ቀኙም የተሰማራበትን ተግባር ለብቻው መፈጸም ተስኖት ሲታገል ለታዘበ ትእይንቱ ሳቢ ነው$

እኛ ወንዶቹ ፈጣጣዎቹ ደግሞ ወይ ያፈረችበትን መቀመጫዋን ባለማየት አንተባበር ወይ እጁዋ ሊያደረግ የሚፈልገውን አገዝ በማድረግ አንፈጽም እነሱ በሚያፍሩበት እኛ በምንማረክበት መቀመጫቸው እንቁልልጭ ስንሽቀዳደም እንዳፈጠጥን ሌላ የትእይንቱ አክተሮች ሆነን እናርፋለን$

እውን ባጠረ ሱሪና በአጭሩ አላባሽ የተነሳ እነሱም ስራ ማብዛት እኛም ባይናችን እንደቀላወጥን መቀጠል አለብን?! በኔ እምነት ወይ አዲሱ መቀመጫና ዳሌ የማያጋልጠውን ገላግሌ ሱሪ ይልበሱልን ወይ ደግሞ እኛ ቀላዋጭ አይናችንን እናሳርፍ$

አጋልጠው ይሸፍኑሻል ሸፍነው ያጋልጡሻል% ተውበውብሽ ያፍሩብሻል አፍረው ደግሞ ይዋቡብሻል$ አዬ ዳሌና መቀመጫ$

እውነት እኮ ነው መሀል ላይ ያለ ነገር ሲሸፈንም ያምራል ሲጋለጥም ያፍራል!

Sunday, April 21, 2013

"ወያኔ ኢህአዴግ ካለጠፋ" ለሚለው መጣጥፍ አንድ አንባቢዬ የላከው ቆንጆ የመልስ ምት


አንባቢዎቼ በወያኔ ኢህአዴግ ካልጣፋ መከራችን አያበቃም በሚለው መጣጥፌ ላይ ሬገን ሶሎሞን የተባለ አንባቢዬና የፌስ ቡክ ጓደኛዬ የሰጠውን አስተያየት እንደሚከተለው ያለምንም መጨመርና መቀነስ አቅርቤዋለሁ$ ቈንጆ ሙግት ነው አንብቡት$

ውድ ዘሪሁን ካሳ
በቅድሚያ በዚህ ወር ሃሳብህን ስላካፈልክባቸው መጣጥፎችህ ምስጋናዬ ይድረስህ $ በሁለቱ ላይ ሀሳብ መስጠት እንዲያስችለኝ ሁለቱንም በጥሞና አንብቤያለሁ$ እናም በመሰረታዊው ሃሳቦችህ ላይ በተለይ ከአንዱ ጋር እስማማለሁ$ ሁለቱ መጣጥፎችህ ወያኔ ኢህአዴግ ካልጠፋ መለስ ተኪ የሌለው መሪ አይደለም የሚሉት ናቸው$ በሚቀጥለው ጊዜ መለስ ተኪ የሌለው መሪ አይደለም ለሚለው መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ$ ከዚህ በታች የተሰጠው አስተያየት ግን ወያኔ ኢህአዴግ ካልጠፋ ለሚለው መጣጥፍህ አንኳር ትችቶችህ የተሰጠ የመልስ ትችት ነው$

በመጀመሪያ በተቋዋሚው /ሰብ እኔን ጨምሮ ወያኔ ኢህአዴግ ካልጠፋ ኢትዮጵያ ሰላም አትሆንም ወይም መከራችን አያበቃም የሚለው ቅዠት መኖሩን አምናለሁ$ ይህ ሀሳብ የሚነሳበት ዳራ ወያኔ ኢህአዴግ የችግሮቻችን ሁሉ መሰረት ነው ብሎ ከሚያስብ ነገር አቅላይ አተያይ ነው$ ቅዠት ነው የሚያስብለኝም ለዚያ ነው$ ነገር ግን ለድርድር የሚያመች ሁኔታ ቢኖርና ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች የሚሳተፉበት ስርዓት መፍጠር ቢቻል በግሌ ደስ ይለኝ ነበር$ ብዙ ተቃዋሚዎችም ይህ እንደሚያስማማቸው አውቃለሁ$ በፕሮግራማቸውም ሳይቀር ይህንን ያወጁ ወይም ያስቀመጡ አሉ$ ያም ሆኖ አንተ የገለጽከውን አይነት ዝንባሌ አለ$ ለዚህ ግን ተጠያቂው ተቃዋሚው ብቻ አይመስለኝም$ የአንተም መጣጥፍ አተያዩን መኮነኑ ደግ ሆኖ ለመቸከላችን ምክኒያቱ ተቋዋሚው ነው ወደሚል ድምዳሜ የሚያንደረድረውን ሃሳብ አልስማምበትም$

ሁለተኛ አማራጭ ፖሊሲና ስትራቴጂ ስንል ደረጃዎችና የሚቀርብበትም ከዚያ የሰፋ ከባቢ አለው$ በኔ አተያይ ከፖሊሲና ስትራቴጂ በፊት ሀገራችንን ወዴትና እንዴት እንደምንወስዳት ባለው ራዕይና ተልኮአችን ላይ የጠራ ስምምነት የለም$ ከዚያ ሲቀጥል ደግሞ እንደ ሀገር ለመቀጠል ስጋትና አደጋ የሚሆኑን ጉዳዮች ተብለው የተቀመጡት አጀንዳዎች አንገብጋቢነታቸው የተመዘነበት ዕይታ ከሀገሪቱ ህልውና ይልቅ የህወሀት ኢህአዴግንና አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚለውን መስመሩን የበላይነት ለማስጠበቅ የተቀረጹ ናቸው$ በዚህ ውስጥ አማራጭ ብሎ ነገር የለም$ አማራጭ የሌለውና ብቸኛ እንዲሆን ተገፍቶ ተገፍቶ እዚህ ደርሷልና$ አማራጭ የሚኖር የነበረው ከመሰረቱ ሁሉንም አካላት ያሳተፈና ተቀባይነት ያለው አስማሚ ባይሆን እንኳ ሁሉን ለማቀፍ ክፍት የሆነ ራዕይና ተልኮ ተቀርጾ ይህን ግብ እዳር ለማድረስ ስጋቶቻችንና አደጋዎቻችን ላይ ከሞላ ጎደል አብዛኛው ሰው የሚስማማበት አካሄድ ቢመረጥ ነበር$ ይህን ሁኔታ ስታስብ ከመጠጋገን ይልቅ አፍርሶ መስራት ትክክል ነው የሚለውን አተያይ ለመኮነን እንዲህ ቀላል አይመስለኝም$

ሌላው አንዳንዱ ነገር ለምሳሌ ሐገር የምትመራበትን መርህ መድብለ ፓርቲ ወይስ የአንድ ፓርቲ የበላይነት መርህ ይሁን የሚለው በኢትዮጵያ ሁኔታ የአማራጭ ጉዳይ አይደለም$ በህገ መንግስቱም የተቀመጠ ነው$ ኢህአዴግ ይህ እንዳይኖር ወይም ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሲብስም የህዝብን የመቃወም መብት በሚጥሱ ህጎችና አስተዳደራዊ እክሎች የበላይነቱን ስለማስጠበቅ ይሰራል$ እየሰራም ነው$ ይህን በአጠቃላይ ፍሬሙ ውስጥ ያላስገባህ እንደሆን አተያይህን ሸውረር ያደርገዋል$

እንደዚሁም ሁላችንም እንደምናውቀው የኢህአዴግ ሃሳብና ተግባር አማራጭ ሃሳቦችን በእንጭጩ ማጥፋት ነው$ እንዲህ አይነቱ ተግባር ቀድሞ በአስተዳደራዊና በቢሮክራሲ መሰናክሎች ባስ ሲልም በሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ጭምር ሲፈጸም ነበር$ አሁን አሁን ከዚህ ተግባር በተጨማሪ ከህገ መንግስቱ የሚጻረሩ የህግ ማዕቀፎችና ማስፈጸሚያ ህጎችን እንኳ በማውጣት ተቃዋሚዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ ብሎ በሚያስባቸው ክፍተትና ቀዳዳዎች ላይ ሲጥፍ ሲደርት ማየት የተለመደ ነው$ ያንተ ሃሳብ እንደሃሳብ አንዱን ጎን ብቻ መውሰዱና መተቸቱ ኢፍትሃዊ ትችት የሚያደርገው ከዚያም ሲያልፍ ያለውን ሁኔታ የማስቀጠል መከላከል የሚሆነው ለዚህ ነው$

በተጨማሪም ዺሞክራሲ በተፈጥሮ ባህሪው የሚያድገው እንዲሁ እድሜ ጠገብ ስለሆነ ወይም ብዙ አመታት በማስቆጠሩ አይደለምበሂደቱ ውስጥ የሚቀርብለት ግብዓትም ወሳኝ ሥፍራ አለው$ በተለይ ለዲሞክራሲ እድገት ብሎ በቅን ልቦናና ያለራስ ወዳድነት የሚስራ መንግስትን ትጋትና ሁሉንም ያገባኛል የሚል ህብረተሰብን አስተዋጽኦ የሚቀበል ሰፊ ምህዳር በግብዓትነት በቅድሚያና በወሳኝነት ይፈልጋል$ ይህ በኢትዮጵያ የለም ብቻ ሳይሆን ኢህአዴግና መንግስት በዚህ ረገድ ዲሞክራሲ በሁለት እግሩ ይቆም ዘንድ የገንዘብ የዕውቀትና የተግባር አስተዋጽኦ ለማድረግ የሚታትሩትን ግለሰቦችና ድርጅቶች በማደን ተግባር ላይ መሰመራታቸው ዛሬ ዛሬ መላው አለም የሚያውቀው ባህሪይ ሆኗል$ አሁን ባለው የፖለቲካ ምህዳር የሚመጣው ለውጥ በራሱ ተፈጥሮአዊና ነጻ አይደለም$ የህወሀት ኢህአዴግ ጣልቃ ገብነት የሚያሳርፈው ተጽዕኖ እንደ ጄኔቲክ ምህንድስና ዓይነት መጠንና ቅወጣው ከፍ ያለ ቁጥጥር አብይ መገለጫው ነው$ በመሆኑም ሆን ተብሎ ዲሞክራሲን በማጫጨት ለፍሬ የሚበቃበትን ጊዜና ዕድገቱን አዝጋሚ ተደርጓል$ እየተደረገም ነው$ ስለዚህ በዚህ በኩል ያለህ ትችት ትክክለኛ አተያይ አይመስለኝም$ አልስማማበትምም$

ከዚያ በመለስ ግን በሁለት ጉዳዮች የምንስማማ ይመስለኛል$ አንደኛ ተቃዋሚዎች ከወያኔ ኢህዴግ የሚያሳትፍ ፖለቲካ አይከተሉም$ በማናቸውም ሁኔታ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ወድቆ ያሉትን ባለስልጣናት አባሮ በአዲስ መተካት በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረት ምኞት አለ$ ይህ ትክክለኛ ምኞት አይመስለኝም$ የሚሳካም አይደለም$ ምክኒያቱም በዚህ ሥርዓት ጥቅማቸው የተከበረላቸው ወይም የመሰላቸው ከዚህ አይነት ትግል ተቃራኒ መቆማቸው አይቀርም$ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታና በትምህርትና ዕውቀት ሥርጭትም ምክኒያት እነዚህ /ሰብ ክፍሎች ብዙ ናቸው$ ከዚሁ ጋር የዚህ የድጋፍ መሰረቱ ትግራይና ብሔር ብቻ ነው ብሎ መታሰቡም ትክክል አይደለም$ ስለዚህም ወያኔ ኢህአዴግን አጥፍቶ በምትኩ ሌላ የአሸናፊ ፖለቲካ ለማምጣት መታገላቸው በሂደት ዋጋ የሚያስከፍል ነው$ እያስከፈላቸውም ነው ብዬ አምናለሁ$

ሁለተኛው ከጥቂት የድጋፍ መሰረታቸው በጣም ውሱን ከሆኑት የፖለቲካ ተቀናቃኝ ድርጅቶች በቀር በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያሉ ተቃዋሚዎች ወያኔ ኢህአዴግ ስለመውደቁ የመተለማቸውን ያህል ከውድቀቱ ማዶ ሀገሪቱ እንዴትና በምን ሁኔታ እንደምትመራ እንደዚሁም ከመሃከላቸው ምንና ማን አስማሚ ሃይል ሆኖ ሽግግርን እንደሚመራ በግልጽ ያስቀመጡት ወይም ይህን የሚገዛ አጠቃላይ ስምምነት የለም$ ይህ ያሳስበኛል$ ያሰጋኛልም$ ይህም እንደማስበውም ለሚያገኙት ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ አይነተኛ ቦታ አለው$ እኔም በወያኔ ኢህአዴግ ካልጠፋ መጣጥፍህ ላይ ያነሳኋቸውን አንኳር ነጥቦች እዚህ ላይ ቋጨሁ$ በቸር ያቆየን$