ይሄ የሱሪ የአጭር አላባሽና የሴቶቻችንን
ግንኙነት አለመጣጣም የሚያሳብቅ የለትተለት ትእይንት ነው$ ሱሪው እስከ ወገብ አላባሹ ከዚያ ትንሽ ከፍ ብሎ የሚቀር አይን አፋር
ነገር እንዲያውም አጋላጭ ሊባል ይችላል$ ሴቶቻችን ደግሞ ወደውትና መርጠውት አድርገው ሲያበቁ አለባበሳቸው የሚያምርም የሚያስጠላውንም
መቀመጫቸውን ማጋለጡ ያሳፍራቸዋል$
ደስ የሚል አይነት ሀፍረት$ እነርሱም አጋላጭነቱ ደርሶ ያኔ ትዝ ብሏቸው የማይሸፍነውን አላባሽ ካልሸፈንክ ብለው ሲጎትቱ ሲጓተቱ ያ አጭር ማላበሻቸው መሸፈን ሲሳነው እንታዘባለን$
ደስ የሚል አይነት ሀፍረት$ እነርሱም አጋላጭነቱ ደርሶ ያኔ ትዝ ብሏቸው የማይሸፍነውን አላባሽ ካልሸፈንክ ብለው ሲጎትቱ ሲጓተቱ ያ አጭር ማላበሻቸው መሸፈን ሲሳነው እንታዘባለን$
አዬ ዳሌና መቀመጫ አጋልጠው ይሸፍኑሻል
ሸፍነው ያጋልጡሻል% ተውበውብሽ ያፍሩብሻል
አፍረው ደግሞ ይዋቡብሻል$
እውነት
እኮ ነው መሀል
ላይ ያለ ነገር
ሲሸፈንም ያምራል ሲጋለጥም
ያፍራል!
አፍረው ቢሆን ኖሮ ወደው አይለብሱትም$ ወደው ካማሩበት ደግሞ ተመልካችን
ለመመለስ መታገላቸው ተገቢ አይመስልም$ ዘፋኙ ደስ በሚል ስቃይ እንዳለው የሚያሳፍር ውበት ነው$ በተፈጥሮ ግን ደስ የሚል አያሳፍርም
የሚያሳፍር ደግሞ ደስ አያሰኝም$
አጋልጠው ለተመልካች አስጥተው ሲያበቁ
በል መለስ በል ክንብንብ በል ሲሉት አይመጣ$ እኛም አይናችን አያርፍ እንዳይታይባቸው የሚሸፋፍኑትን ግን የማይሸፈነውን የተጋለጠ
ገላቸውን ለማየት እንደተሽቀዳደምን ይሄው በየታክሲው በየካፌው ሲቀመጠኑና ሲነሱ የነሱም መቀመጫቸው ተጋልጦ የኛም አይናችን ማግጦ
ሌባና ፖሊስ እየተጫወትን$
እነሱ ያቺ ቆንጆ ዳሌና ባታቸውን
እንቁልልጭ እንዳሉ እኛም ሌባና ፖሊስ አይነት ነገር አየሁሽ አየሁሽ እንዳልን አለን$ አጋልጠው የሚሸፍኑሽ ተጋልጠሽ የተሸፈንሽ
ሊያሳዩሽ አዋጅ አዋጅ የሚሉሽ ዉበታቸው ደሞ እፍር ብለው ክንብንብ ሊያደርጉ የሚደክሙብሽ ሀፍረታቸው$ አዬ ዳሌና መቀመጫ እንዲህ
ታደክሙን$ እኛ በማየት ሽቅድምድም እነሱ በማጋለጥና በሀፍረት$
አዬ ዳሌና መቀመጫ አጋልጠው ይሸፍኑሻል
ሸፍነው ያጋልጡሻል አለ!?
በየአጋጣሚው ዝቅ ማለት የሚያስገድድ
ሁኔታ ሲያጋጥማቸው አንድ እጃቸው ከሚወዷት ለአለም ካጋለጡዋት ዳሌና መቀመጫቸው ተመልሳ ለመሸፈን ስትታገል አንድ እጃቸው የተላከችበትን
መልእክት ለብቻዋ መፈጸም ሲሳናት እንታዘባለን$ ብቸኛው ግራ እጅ ሸፍን የተባለውን
ሳይሸፍን ቀኙም የተሰማራበትን ተግባር ለብቻው መፈጸም ተስኖት ሲታገል ለታዘበ ትእይንቱ ሳቢ ነው$
እኛ ወንዶቹ ፈጣጣዎቹ ደግሞ ወይ
ያፈረችበትን መቀመጫዋን ባለማየት አንተባበር ወይ እጁዋ ሊያደረግ የሚፈልገውን አገዝ በማድረግ አንፈጽም እነሱ በሚያፍሩበት እኛ
በምንማረክበት መቀመጫቸው እንቁልልጭ ስንሽቀዳደም እንዳፈጠጥን ሌላ የትእይንቱ አክተሮች ሆነን እናርፋለን$
እውን ባጠረ ሱሪና በአጭሩ አላባሽ
የተነሳ እነሱም ስራ ማብዛት እኛም ባይናችን እንደቀላወጥን መቀጠል አለብን?! በኔ እምነት ወይ አዲሱ መቀመጫና
ዳሌ የማያጋልጠውን ገላግሌ ሱሪ ይልበሱልን ወይ ደግሞ እኛ ቀላዋጭ አይናችንን እናሳርፍ$
አጋልጠው ይሸፍኑሻል ሸፍነው ያጋልጡሻል% ተውበውብሽ ያፍሩብሻል አፍረው
ደግሞ ይዋቡብሻል$ አዬ ዳሌና መቀመጫ$
እውነት እኮ ነው መሀል ላይ ያለ
ነገር ሲሸፈንም ያምራል ሲጋለጥም ያፍራል!
No comments:
Post a Comment