አሸናፊት ና ስኬት

አሸናፊነትን ሰበብ አይረታውም

አሸናፊነት ያለሙትን ማሳካት እመረጡበት መድረስ መቻል ነው$ አሸናፊነት እንደ ኳስ ይነጥራል እንጂ እንደ ረጠበ ስፖንጅ እመሬት አይጠፈጠፍም$ አሸናፊ ልምድ በሚወጣም በሚወርድም እርግጫ አይረበሽም$ በቁምነገሩ በራሱ ህይወት ሂደት ሌሎች ያላቸው ፋይዳ ወሳኝ ሚና እንደሌለው ብቻ ሳይሆን ወሳኙን ሚናውን የሚጫወተው ራሱ ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ ያውቃል$

አሸናፊ ልምድ ለውድቀቶቹ ሰበብ አይቆጥርም ራሱ እንጂ ሌሎች ሰበቦች ለውድቀቱ መሰረታዊ ፋይዳ እንደሌላቸው ስለሚረዳ$ ሰው ልምድን እንደሚመስል ጠንቅቆ ያውቃል$ ሁዋኝ እንጂ ተደራጊና ተሰሪም እንዳልሆነ አይስትም$ ይሄን ቢስት እንኳ ሀቁ እንደማይቀየር ያውቀዋል$
ህይወት ምርጫ እንደሆነና ያን ምርጫ የማካሄድ ጉዳይ የራሱ ስለመሆኑ እርግጠኛ ነው$ የተሳሳተ ምርጫ በማካሄድ ወይም የመረጠውን ምርጫ በአግባቡ ባለመተግበሩ የሚመጡበትንም ጣጣዎች በጸጋ ዋጥ ያደርጋል እንጂ እነ እገሌ ይህን አድርገው ባይሆን ኖሮ ይሄ ባልሆነ ነበር የሚል ሰበብ አያውቀውም$ እነ እገሌ የማይገባ ነገር እያደረጉም ቢሆን የራሱን ከባቢና ምርጫ የሚያበላሹበትን ሁኔታዎች መቆጣጠር የሱ እንጂ የማንም ሀላፊነት እንዳልሆነ አሳምሮ ያውቃልና$

ሰው አቅሙ የሚችለውን ሁሉ ከሞከረና አቅሙ አሁን ያልደረሰበትንና ለስራው አስፈላጊ የሆነ ብቃት ያለማቋረጥ እስከገነባ ድረስ ሽንፈትን እንደገዛ ራሱ ሽንፈት ለመቀበል አይቸገርም$ ሽንፈትን መቀበል የሚያስፈልገው ትክክለኛውን የችግሩን ምንጭ ማከም አስፈላጊ በመሆኑ ነው$ ችግሩ እውስጥ ሆኖ ሳለ በተደጋጋሚና በቸልተኝነት ችግሩን ውጫዊ ማድረግ ለተወሰነ ግዜ ጫናውን ለሌሎች ለማጋራትና ራስን ተጠያቂ ላለማድረግ ያንደፋድፍ ካልሆነ በቀር ፋይዳ ቢስ ነው$

ሰላምነኝ እረ አልታመምኩም እያሉን በሽታ ገዘግዞ እንደሚገላቸው ድብብቆሽ ተጫዋቾች የራሳችንን ችግሮች በመካድ ለሌሎች እጥረቶችን እያጋቡ ለመኖር መሞከር አደገኛ ነው$ እንዲህ ያለው ክፉ ባህሪ ሳይደነድን በግዜ ካልታረመ ምነው እናቴ ሳንቲሞቹን ሳነሳ በከለከልሺኝ እንዳለው ሌብነት ሱስ ሆኖ ለውድቀት እንደዳረገው ግለሰብ መሆን ይከተላል$

አሸናፊዎች የተመቸ ሁኔታ ከሌለ ሁኔታውን በማመቻቸት አስፈላጊ ቁሳቁሶች ካልተሟሉ በማሟላት ደንቃራ በየመንገዱ ከተኮለኮለ ያን በማጥራት የሚመኙትን ነገና የሚሹትን ጉዳይ ከማሳካት ወደኋላ አያውቁም$ ይሄ ማለት ሁሉን ጉዳይ እዚያውና ወዲያው ካልፈታሁ ይላሉ ማለት አደለም፡፡ ይልቁንም ከነሱ የሚጠበቀውን እያሟሉ የሚወስደውን ግዜ ወስደው ምርጫቸውን ለማሳካት ሳያሰልሱ ይሰራሉ$

ይሄ ማለት ለጉዳዩች ለግለሰቦችና ማህበረሰቦች የተመረጡ አላማዎች መክሸፍ ከነሱ ውጭ የሆኑ ውጫዊ ምክንያቶች የሉም ማለት አደለም$ አሸናፊ ግለሰቦች አሸናፊ ማህበረሰቦች ያንን የመሳሰሉ እንቅፋቶችን በመለኝነት ተሻግረው ነው ህልማቸውን የሚያሳኩት የሚለውን ተፈጥሯዊ ሀቅ ለማመላከት ነው$

አሸናፊነታቸውን በተሟላ ካፒቴንነት ይመሩታል፡፡ ለእድል የሚተው ነገር የለም፡፡ እድል ካለች የምትቀርጸው እነሱ መገመት ማቀድ ያልቻሉትንና በነሱ ቁጥጥር ስር ያልሆነ ነገር የሆነ እንደሆነ ብቻ ነው$ ሰበብ በአሸናፊ ግለሰቦች ልምድ ቦታ የለውም$ በህሊናቸው ስለማይከሰት አደለም መርጠው ትተውት እንጂ$

ሰበብ ሽንፈትን በጸጋ ማጣጣም የማይችሉ ግለሰቦች ለህሊናቸው ማሞኛነት የሚጠቀሙበት ማደንዘዣ እንጂ ድርጊቶች ላለመሳካታቸው የሚቀርብ አሳማኝ ምክንያት ወይም መነሻ አደለም$ አሸናፊነት እኮ ያው በሰበብነት የቀረበውን አስቸጋሪም ነገር መሻገር መቻልና ያሰቡበት መድረስ እንጂ ሌላ ምንም አደለም$ ይቆየን$

No comments:

Post a Comment