Tuesday, January 1, 2013

አንድም ሲሆን አምባገነን ቡድንም ሲሆን ስልጣን ቅርጫ ነው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዘናዊ  የቆዩበትን 20 የሚሆኑ የአመራር አመታት ክፉኛ ሲያጣጥሉ የነበሩ ተቺዎች አንዱ የሚነቅፉት ነገር ሰውየው ለወዳጆቻቸው እንኩዋ ስልጣን የማጋራት ዝንባሌ ያልነበራቸው ብቻቸውን ልቀውና ጠንክረው ወጥተው ሀገሪቱን እንዳሻቸው የሚያሾሩ ናቸው የሚል ነበር

ዛሬ ደግሞ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በቡድን የመስራት መንፈስ እናጎለብታለን በሚል መነሻ የጋራ አመራር ሲከተሉና ቀድሞ ያልነበሩ ሁለት ማስተባበሪያዎች በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት ማእረግ ሲያቁሙ ስልጣን ቅርጫ ሆነ እቺ ድሀ አገር ለዚ ሁሉ ተሹዋሚ መክፈል አለባት ወይ ሀይለማርያም ደካማ ስለሆነ መለስ ብቻውን የሰራውን መስራት ተሳነው ከህግና ከህገመንግስት አግባብ ውጪ ሹመት ተፈጸመ የሚል አቤቱታ እዚህም እዚያም ሲነሳ ይሰማል

በቡድን መስራት ደካማነት በግል መስራት ደግሞ አምባገነንነት ከሆነ የቀረው አማራጭ የቱ ነው?

ይሄ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረ አቁዋም እንዴት መስመር እንደሚይዝ ማሰብ ጥሩ ይመስለኛል።

ዶቹን አቅም በሚታይ የስልጣን ክፍፍል ጠሚ ሀይለማርያም ማረጋገጡን ማድነቅ ሲገባ  ደካማነትና ሹመት የማከፋፈል አድርገን የምናይ ከሆነ አስቸጋሪ ነው።

የቀ.ጠ.ሚ. መለስም ቢሆን በኔ እምነት ከፓርቲው ጋር እየተመካከረ እንደሚሰራ ነው የማውቀው ያም ሆኖ ትላልቅና የሚታዩ ስኬቶች እያሉት ስናጣጥለው ኖርን አምባገነን ነው እያልን ሚዛኑን የሳተ የትችት ጋጋታ አወረድንበት  ስንቱ አፍሪካዊ መሪ ሲዝናና እና ቤተሰቡን ባለሀብት እያደረገ በሚገኝበት አህጉር እረፍት ላልሻተበት ትጋቱ ክፍያችን ሚዛን የሳተ ትችት ነበር- ተገቢ ትችቶችን አልነቅፍም

አሁን ደግሞ ይህንን ጥርጣሬ በሚያጠፋ ተግባራዊ የሀላፊነት አመዳደብ ትላልቅ ስራዎችንም መምራት እንዲቻል እያደገች ያለችውንና በዚሁ እመርታ የምትቀጥለውን አገር በተባበረ አመራር ዳር ለማድረስ ተፍ ተፍ የሚሉ መሪዎችም ሲተኩ ማጠልሺያው ተገልብጦ የሚቀጥል ከሆነ ችግሩ ወዲያ ሳይሆን ከተቺው መነጽር ላይ ስለመሆኑ መጠርጠር ተገቢ ነው።

ብዙ ስራ አለብን ረጅም ርቀት እንጉዋዛለንና አትነዝንዙን!!! ያለው ማን ነበር?!
 

No comments:

Post a Comment