Monday, February 11, 2013

ሀይማኖት አሸባሪነትና ኢትዮጵያ



ቁምነገር 1
የትኛውም አገር አሸባሪነት ያሰጋኛል በመሆኑም ሀይማኖትን ተንተርሶም ይምጣ የፖለቲካ ቅራኔዎችን መነሻ አድርጎ አሸባሪነትን ነቅቶ መጠበቅ ብልህነት ነው የሚል አቋም ቢይዝ ምንም የሚገርም ነገር የለውም::

በተለይ በኛ ሁኔታ ደግሞ አልሸባብ እና የኤርትራ መንግስት የሚያሰማ[ቸው አሸባሪዎች በተለያየ ወቅት የሚደቅኑት ስጋት ከሞኖሩ አንጻር ነቅቶ መጠበቅ በአዲስ አበባ ከዚህ በፊት የተፈጸሙት ጥቃቶች ዳግም እንዳይከሰቱ ከማድረግም በላይ ህዝብ የተለያዩ ልማታዊ እንቅስቃሴዎቹን በዚህ የተነሳ እንዳያቋርጥ ማስቻልም ነው::

ህዝቤ ብዬ ለመጥራት የማላፍርበት ህዝብ ሀይማኖተኛ ነው:: ቅጥረኛ አሸባሪዎችን የማይሸከምና ሀገሩን የሚወድ መሆኑንም መሳት የዋህነት ነው:: ሀይማኖቱን የሚወድ ህዝብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሀይማኖቱን ተገን አድርገው የሚመጡበትን ከሀዲዎች አይምራቸውም:: እምነቱን የሚኖረው ሀገሩ ስትኖር ስለመሆኑ አይስትም::

ቁምነገር 2
ሀይማኖት የግለሰብ ምርጫ ነው:: አንድ ማንኛውም ዜጋ ያመነበትን ሀይማኖት የመከተል ነጻነት አለው::
ከዚህ አልፎም ሀይማኖቱን በጸሎት በስግደት በምስጋና በቅዳሴ በበአላት ማክበር መተግበር የሚችልበት የተሟላ ነጻነቱን እየኖረው ያለ ህዝብ ነው::
በአምልኮ ቦታ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በሀይማኖቱ ተከታዮች ያለማንም ጣልቃ ገብነት መፈታት አለበት ብሎ የሚያምን በዚሁ መልኩ ሀይማኖቱን በአግባቡ እንዳይፈጽም በተከለከለበት ግዜም ሳይቀር ተቻችሎ የኖረ ህዝብ::

ዛሬ ዛሬ የዚህን ለአለም አብነት የሆነ ህዝብ ባህል የሚበረዙ አዝማሚያዎች እናስተውላለን:: አብሮ መጠጣት መብላቱን ነውር ለማስመሰል የሚጥሩ ደራሽ አዋቂዎች& የመቻቻሉን ብስለት የፍርሀት የሚያደርጉበት ደራሽ ጀግኖች& ልዩነቶቹን ተወያይቶ በሽማግሌ የመፍታት ልምዱን የመሀይምናን ገባኤ ጉዳይ የሚያስመስሉ ሳይደቁኑ የሚÆስሱ አሜኬላዎች::

ሳይገባቸወም ሳይገባቸውም (ይጠብቃል) የስብከቱን ሜዳ የረገጡ የነገሩንን አሜኬላ ቸል ብለን ዝም ስላልን የሚነግሩን መለኝነት የጎደለው ሀሳብ ሄዶ ሄዶ ምን እንደሚያስከትል መገመት የሚሳነን የሚመስላቸው አውቀውትም ሳያውቁም የዚህች አገር መለወጥ ለማይዋጥላቸው ጠላቶቻችን ቅጥረኛ እየሆኑ ያሉ ሀይማኖተኛ ስም ያላቸው አሜኬላዎች አሉን::

በርካታ ሰባክያን አሏት እቺ አገር በስልምናም በክርስትናም::  ሁሉም ሰባኪ አደለም አብዛኛው ሰባኪ አሸባሪ የሚል ታርጋ አልተለጠፈለትም:: እጅግ በቁጥራቸው የሚያንሱ ህጉ ከሚፈቅድላቸው ቅጥር አልፈዋል በሚል ክስ ታስረው ሊሆን ይችላል::
በርግጥ የተከሰሱበትን ወንጀል ፈጽመዋል አልፈጸሙም ፍርድ ቤት የሚሰጠው ብያኔ ሆኖ አገር የሽብር ጥርጣሬ አስግቷት ያደረገችው ከሆነ ግን ሀይማኖተኞችን እንዴት ያስራል መንግሰት የሚል ጥያቄ መነሳት አለበት ብዬ አላምንም::

በሀይማኖት ሽፋን ስንቱ እንደተቀጨና እስከዛሬም እንደሚቀጭ በየለቱ የምንሰማው ነው:: በሀይማኖት ሽፋን ስንቱ ሀሺሽ እያበቀለ በሀሺሽ ህሊና እያጦዘ ሽብር እንደሚፈጽም በደም የተነከሩ ምስሎችን በየቀኑ እያየን የምናውቀው ነው::

ጥያቄው ማነው እሱ አደለም መጠየቅ ያለበት ምን አደረገ ምን እየሰራ ነው የሚለው ነው::  ማንነታቸውን ሸፍነው ስንት አስነዋሪ ነገር የፈጸሙና የሚፈጽሙ ስለምናውቅ ማንነታቸው ሊያዘናጋን ይገባል የሚል እምነት የለኝም:: መመልከት ተግባራቸውን መመርመር ድረጊታቸውን ነው ተግባር ዋሽቶ አያውቅምና::


ቁምነገር 3
የሀይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ተብሎ እንዳንናገር አፋችን እንዳንሰራ እጃችን ታስሮ የምንወዳት ሀገራችን ስትታመስ የምንወደው ህዝባችን በወጣበት ሲቀር ማየት አንሻም::

በሀይማኖቱ ጣልቃ አንገባም እንጂ ሀይማኖቱን ከለላ አድርጎ ዉሏችንን እንዲያበላሸው ለማንም አንፈቅድም ሌላ አገር የለንም::
በታመሰ አገር ሀይማኖታችንን አንኖረውም:: በሌሎች አገር የምናየው መተራመስ ፍንዳታ እንዲገርፈን አንፈልግም:: ለችግሩ ድህነታቸን መች አነሰን ሌላ ካንሰር ልንጨምር ይቅርና::
በመሆኑም መንግሰት በሀይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም በሚል መዝሙር  እንዳሻን እንዘውር የሚባልባት አገር መሆን የለባትም::

ሰው መሆን ይቀድማል ሰውነት ደግሞ መንፈስን ብቻ የያዘ አደለም:: አካል ህሊና ማህበራዊነት የመሳሰሉ ሌሎች ተፈጥሯዊ ፍላጎቶችና ተፈጥሮ አለን:: ሁሉን በልኩ በሚዛኑ መያዝ መልመድ መብሰል ነው::
እስከሚገባኝ ድረስ ሀይማኖተኝነት አምቧጓሮ አደለም እንዲያውም ባለመግባባት ውስጥም ተቻችሎ ተዋዶ መኖርን የሚያስችል ቁመና ነው::

የለም የለም ይሄ የሀይማኖት ጉዳይ ነው እንዴት እንናገራለን የሚባል ቀልድ መኖር የለበትም:: ሀይማኖተኛና ሀይማኖት መከበርና ህጋዊ ጥበቃ ማግኘት አለባቸው:: ያም ሆኖ የሚደረግላቸው ጥበቃ ግን ገደብ የለሽና ሌሎቹን እሴቶቻችንን የሚያጎድፉ እንዲሆን ሊፈቀድ አይገባም:: ቁሙ ቅጥሩ እዚህ ድረስ ነው መባል አለባቸው::

ህዝባችን ሀይማኖተኛ ነው ለሀይማኖቱ ተቆርቋሪ ነው በሀይማኖት ስም  አሸባሪነትን የሚጭኑበት ልል ማህበረሰብ ግን አደለም:: ይሄ ህዝብ እንደ ንብ ብሄራዊ ጸጥታውን የሚያደፈርሱበትን ከመመከት ወደኋላ አይልም::

እመለስበታለሁ!!!!



1 comment:

  1. ahebarinetin kehulum askedmo yemikelakel eco islam new komitewechachin aweliya letesebesebew hizb yalutin lastawsih wedaje << egna muslomochi menegest enkon akrarinetin bifeqed ashebarinetin bifeqid egna ( muslimochi betibik enawegzalen miknayatum haymanotachin silemayfeqid,, neger gin ene kante gar yemismamabet hasib linor yichila esum beislam sim yeminqesaqesu ashebariwechi linoru yichilalu yihim new haymanotun yemigodaw neger gin eskahu betarig ketekahedut chifchefawech weyim gidiyawechi yetekenawenut beislam hamanot tekeay sayhon belelochi haymanot sim new lemanignawim hulachinm yehagerachinin selam metebeq gid yilenal muslimu kristiyanu sayil hulum halafinetun mewetatina hagerachinin kedihineta mawtat yinoribetal liyunetochi binoru eckon bemenegager meftat yinoribinal gin komitewechachin beselamaw menged jemerew neber gin selam yemaywedew mengistachin embi bemalet yemeretnachewin yeminiwedachewin lehagerachin edget defa qena bsilu yeneberuna mirit yeethiopia lijochi kaliti eyemaqequ yogegnalu enji bihonim gin yemishalew hulachinim lehagerachin selam halafinet alebin ena ante banesahew hasab mulu bemulu esmamalehu gin komitew tefetew mengistim behaymanot yemayigeba kehon new bihonim gin komitew bastemarunina haymanotachin bemifeqdew meneged hulgize selamin asqedimalehu ashebarinetin gin hulgizem bihon eqawemale !!!!!

    GIN YANESAHEWIN HASAB TEMECHITOGNAL SIMETAWI HOGNE TETSAFKOCHEW SILEHON TIREDAGNALEH BIYE ASIBALEHU

    ReplyDelete