Thursday, February 21, 2013

ሌላ አገር የለንም ያለንንም አገር ላሸባሪ አንሰጥም

zeryihun kassa
ስለ አሸባሪነት ስናነሳና ስንወያይ እያወራን ያለነው ስለ እስልምና አደለም

እስልምናን ከአሸባሪነት ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም

ቁምነገሩ አሸባሪዎቹ በስልምና ወይም በሌላ ሀይማኖት ስም የሚነሱና ህዝብ ለሀይማኖቱ ያለውን ፍቅርና ጽናት ስለሚያውቁት በጸያፍ ድርጊታቸው ምክንያት ሲታሰሩ ወይም በህጉ ሲታደኑ

ለሀይማኖቱ ፍቅር ያለውን ህዝብ ሀይማኖተኞች ስለሆንን ታሰርን ለሀይማኖታችን ስለሰራን ታሰርን በሚል የሚታወቅ ግን ቅጥፈት የተሞላ የዘወትር ትርኢታቸው ለማነሳሳት በማሰብ ነው

አሸባሪ የሚገባውን ህጋዊ ቅጣት ያግኝ መንግስትም ይህንን በጥብቅ ይከታተል ስንል እንደ ዜጋ ሙስሊም ስለሆንም ክርስቲያን ስለሆንም የማናምን ለሀይማኖት ግድየለሾች ስለሆንም አደለም

ሰው በመሆናችን መጎዳት በወጣንበት በታክሲ በሆነ ሆቴል ወይም ሀይማኖታዊ ቦታ በፈነዳ ቦንብ ህይወታችን እንዳያልፍ ስለምንሻ ብቻ ነው

ደህንነታችን እንዲጠበቅ ሀይማኖተኛ መሆን የለብንም ይሄ ሰው በመሆናችን የምንጋራው የዜግነት ህጋዊ የመጠበቅ መብታችን ነው

እናም ስለ አሸባሪ ስናወራ ከክቡሩ ሀይማኖተኛ ከአፍቃሪው ከአክባሪው ሀይማኖተኛ እንኩዋንና ሊጎዳ ቀርቶ የተቸገሩ የሚረዳውን ሀይማኖተኛ እየወቀረን አደለም

አሸባሪዎች ስለ እናንተ ሲጻፍ እናንተ ስትወገዙ ክቡሩን ሀይማኖተኛ አወገዙት እያላችሁ አታውጁ ይሄ ህዝብ ስንኳንስና ህጋዊ ጥበቃ የሚያደርግለት ህገመንግስታዊ ድንጋጌ ባለበት ዛሬ ይቅርና

ለሀይማኖቱ ህጋዊ ጥበቃ በማይደረግበት ግዜም ተከባብሮና ተቻችሎ የኖረ የብስለት ተምሳሌት ነው

እውነቱ ይህ ነው ማንም ይላካችሁ ማን አባይ መገደቡ አይቀርም በተያዘለት ግዜም ያልቃል ከነችግሮቿ አገራችንም ማደጓን ትቀጥላለች በሶማልያም ይሁን በኤርትራ በኩል ሊያሸብሩን የሚሞክሩም ቢኖሩ ከነቅጥረኞቻቸው ይከስራሉ ዳግም ወደኋላ አናይም ሽቅብ ጉዞ ጀምረናል አንመለስም!!!

ችግሮች ስለለሉ አደለም የማንመለሰው ችግር የመፍቻውን ቁልፍ ስለታጠቅን ነው የቀረውን ተግባርና ውይይት እየፈቱት በመዳህም በመወላከፍም በመራመድም በመሮጥም እንወጣዋለን

በማሸበርም በሌላም መንገድ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማሳካት የሚራወጡ ውጫዊም ይሁኑ የውስጥ ስሁታንም በተግባር ህዝቡን ያውቁታል!! እዚህ አገር በሀገር አይቀለድም!!!

ኢትዮፕያ ለዘላለም ትኑር!!!  ሀይማኖታዊ መቻቻሉም ለዘላለም ይኖራል!!!

No comments:

Post a Comment