Thursday, February 21, 2013

ክብርህን ከነሱ አትፈልግ በጉያህ ሳለልህ

Zeryihun Kassa


ለአንድ አህጉራዊ ስብሰባ በሄድኩበት ምሳ እየበላን አንድ እዚያው የተዋወኩት ሰው 

ዜድ የኛ አገር ሰዎች አለማቀፍ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋሞች ውስጥ የሚሰሩትን ጨምሮ ለፈረንጅ እና ለሀበሻ የሚሰጡት ክብር ይለያያል 

በዚህም የተነሳ የሀገር ውስጥ አለማቀፍ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን መጠቀም መተው እየተገደድን ነው አለኝ

ለምሳሌ የአየር መንገድ ሆስቴሶች ፈረንጅን የሚያዩበት አይን ተወው ለኛ ግን.... እናም ለበረራ የውጭ አየር መንገዶችን የሚጠቀሙ አሉ... ይህ አተያይ አስጠልቷቸው አለኝ

በኔ እይታ የከበርን መሆናችንን ለማወቅ ራሳችንን ቀና አድርገን ለመሄድ የነማንም የመስተንግዶ መልክና አመለካከት የሚያስፈልገን አይመስለኝም

ክብርህን በሌሎች አመለካከት እና ባህርይ ውስጥ አትፈልገው

አብሮህ የተፈጠረ በሰውነትህ ውስጥ የሚንተገተግ ባንተው እይታ መፋፋትና መጠውለግ ልክ የሚከስም ወይም ወደ ላቀ ደረጃ የሚደርስ እንጂ በነማንም የአገልግሎት አሰጣጥ ቁመና ውስጥ የሚታጨቅ አደለም

እነ እገሌ የሚገባንን ክብር ስላላሳዩን አንዋረድም አገራዊ ተቋሞቻችንን መጠቀምም አናቆምም

አንድ ነገር ግን እናውቃለን የሰው ክብር ከምን እንደሚመነጭ የማናቅ ክብርን በቆዳ ቀለም የምንመዝን መብሰል የሚቀረን አገልጋዮች መኖራችንን

ይህም መሆኑ እንዲያ ያየነውን ሰው ክብር አያሳንስም የዚህ አመለካከት ተግባሪ የሆነውን ሰዎች አመለካከት አለመብሰልን ነው የሚያሳየው

ክቡርነትህን ከነከሌ ኪስ እና አገልግሎት የምትሻው ከሆነ እንደ ተቃጠልቅ ትዘልቃለህ

ክቡር ሰው መሆንህን ማወቅ ባከበሩህም በናቁህም ሰዎች ፊት አንገትህን ቀና አድርገህ መሄድ ያንተ ፈንታ ነው

በማንነትህ ውስጥ የታተመውን ክቡርነት ከነሱ አተያይ እና አገልገሎት አትሻው!!!

እመለስበታለሁ!!!!

No comments:

Post a Comment