Friday, February 22, 2013

ግቡ ነቆራው አደለም ግቡ ችግሩ መፈታቱ ነው



Zeryihun Kassa
በአስተሳሰብ ላይ መተጋገል የሚሳነው ሰው የሚቀለው ታርጌት የቆመን መዘርጠጥ ነው:: በቃ ጀግና ለመባል ያክል::

 

አስተሳሰባችንና በዚያው የተቃኘው ተግባራችን እንዲታረም ራሳችንን የችግሩ አካል አድርገን ስናበቃ የመፍትሄው አካል ሆነን መትጋት እያለብን፣



የሚቀለን ዉሃ ልማት ሆነን ስንት ደንበኛ እያለቀሰ ጥሩ አገልጋይ የሆን ያክል መብራት ሀይል የሚሰራውን የኛን አይነት ሰው እንቦጭቃለን፣



ስንቱን የምናስለቅስ ያለ አግባብ ትርፍ የምናግበሰብስ ነጋዴ ሆነን የታክስ ሰብሳቢውን ተቋም ሰራተኞችና ሀላፊዎች ንዝሀላልነትና ሌብነት እንወቅሳለን::



ሚሊዮኖች እና ቢሊዮኖች የሚሰበስበው ኤንጂኦ ውስጥ እየሰራን እና በደሀ ስም የሚሰበሰብን ብር ያለ አግባብ እየቦጨቅን የመንግስትን ሌቦች ለመተቸት ምላሳችን ይዘረጋል::



ቢያንስ ቢያንስ የማንሰርቅና የማንበድል ጥቂቶች ብንኖር እንኳ በየዘርፉ የሚታየውን ይህን መሰል ችግር ለመፍታት ባለመነሳሳታችን ከንፈር ከመምጠጥ የተሻለ አማራጭ ማሰገኘት ባለመቻላችን ወይም ሌቦቹና ጋጥወጦቹ ስንሰራፋ ባለመታገላችን ያው ከወስላታዎቹ ተለይተን የምንታይ አደለንም!

 

ቢያንስ አፋችንን ስንከፍት ለመተካከም ቢሆን! የችግር ቁስላችን ሲድን አገር ይጠቀማል ስንነቋቆር ቁስላችን የበለጠ ይከፋል!


የቁምነገር ሰው ይበለን!

No comments:

Post a Comment