Tuesday, May 14, 2013

አቤት ዘረኝነት

አቤት ዘረኝነት አንድ Dawuro Wisdom የሚባል የፌስ ቡክ ጉዋደኛዬ ራሱን በደበቀባት አካውንቱ ጀርባ ይሄ አገር የዘር ማጥፋት እየተፈጸመበት እንደሆነና ያን ለማስቀረት መፍትሄው ትግሬዎችን ማጥፋት እንደሆነ ነገረኝ፡፡
የለም ይሄ እብደት ነው ዶክተር አማክር ብዬ መከርኩት፡፡

በጣም ተበሳጫና ይሄን ያልከኝ ትግሬ በመሆንህ መሆኑን ፎቶህን ተመልክቼ ደረስኩበት አለኝ፡፡ ቅድም የትግሬዎቹን መገደል አስፈላጊነት አሁን ደግሞ የኔን ትግሬነት ወዲያውና እዛው መሳሳቱና ላርመው ስሞክር መደማመጥ ባለመቻላችን በጨዋ ደንብ ተሰናብቼው ወጣሁ፡፡

ዳውሮ ዊዝደም የሚል ስም የለጠፈው ወዳጄ ግን አሁንም እዚያው ነው የዘር ማጥፋት አማራጩን ዘረኝነትን ከሀገራችን ለማጥፋት እያቀረበልን፡፡ ዘረኛው አፈፍ ብሎ ዘረኛ ሲል የጅራፉን ገርፎ የመጮህ ተረት ያስታውሰኛል፡፡ ለህዝብና ለዴሞክራሲ ያላቸው ቁርጠኝነት ወደ ዘረኝነትና ወደዘር ማጥፋት ከሚወስዳቸው ይሰውረን፡፡

በአደባባይ እንዲህ ልለው ግን መረጥኩ

አሁንም እዛው ነህ ከቻት እኮ ትቼህ የወጣሁት የሀሰት ፈጠራህ ታክቶኝ ነበር፡፡ Dawuro Wisdom እንዳንተ ገለጻ ገዳዩ ትግሬ ነው እኔም ወንጀሉን ወንጀል የሚያሰኘው የገዳዩ ብሄር ሳይሆን የወንጀሉ አስነዋሪነት ነው ማለቴ ትግሬ ስለሆንኩና ምርጥ ዘሬን ለመከላከል በማድላቴ መሆኑን ነቅተህብኛል፡፡

ጌታዬ ለብሄሬ ማንነት ካንተ ማረጋገጫ ስለማያስፈልገኝ ትግሬም አልከኝ ቀይረህ ደግሞ ለትችት ሲያመችህ ኦሮሞ ወይም አማራ ለውጥ የለውም፡፡ በቃ የሆንኩትን ነኝ፡፡ ወንጀልን ወንጀል ለማለት እንዳንተ ዘርን መቁጠር አያስፈልግም፡፡

እባካህ ወዳጄ ምነው ይሄ ዘር መቁጠር ቢለቅህ፡፡ የኔ ጌታ በቻት እንደነገርከኝ ሳይሆን ትግሉ ካስተሳሰብ ጋር እንጂ አንተ እንዳልከው ትግሬን ወይም ሌላን ብሄር ከማጥፋት ካለማጥፋት ጋር አደለም፡፡ ለነገሩ ልትተቹት የምትፈልጉት ሰው ብሄር መቀያየር ልማዳችሁ ነው፡፡

አንተ ትግሬን ለማጥፋት ትጋ እኛ የምናምንበት አስተሳሰብ እንዲመረጥ ህገመንግስቱ የሚፈቅድልንን ያህል በመከራከር ምርጫ እያሸነፍን ለመቀጠል እንሞክራለን፡፡ ወንድሜ ዘር ማጥፋትን እያወገዘ ዘር ለማጥፋት የሚሰራ አንተን አየሁ፡፡ እንዲህ ያለውም የህሊና መዛባት መላ ስለማይጠፋለት እንደመከርኩህ ዶክተር አማክር¡

No comments:

Post a Comment