Sunday, April 14, 2013

የሀገር ፍቅርና ተቃውሞ‐ አዬ ኢትዮዽያ


ኢትዮዽያዬ ይሄውልሽ ተሳዳቢና አዋራጅ ካልሆናችሁ የሀገር ፍቅር የማይገባችሁ ሆዳሞች ሌቦች ናችሁ እየተባልንልሽ ነው

ሀገር ለመውደድ ወይ ወያኔ ይጥፋ እያልን መለፈፍ አለብን ወይም ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀን አሜሪካ ገብተን ኢህአዴግ ሲወድቅ የመሪነቱን ሚና የሚቀበል መንግስት ማቋቋም አለብን

አለሜ ይሄውለሽ ያንቺ ልጆች ሀገር ወዳድ ለመባል ያለን እጣፈንታ ገ¸ውን ፓርቲ ኢህአዴግን መቃወም ብቻ ሆኖ አረፈልን

በቃ አንቺን ለመውደድ ያንቺኑ ፍጡራን ካልጠላን የአብራኮችሽን ክፋዮች ካልተጠየፍን የማይሆን ስለመሆኑ ወዳጆቻችን ሌት ተቀን ይሰብኩናል

እማማ እውን መውደድ መጥላትን የግድ ይላል? እውን ያንቺን ችግሮች ለመፍታት መታገል እነሱ የምንላቸውን የኛን የሀገር ልጆች ውድቀት ማፋጠን የግድ የሚል ነው?

እማማዬ በይዘት መወዳደር በአማራጭ መሸናነፍ አንሶ ነው ፖለቲካችን እንዲህ በጥላቻ በታወረ ትንታኔና ልማድ የተወጠረው?

ደግሞኮ የዲሞክራሲን አስፈላጊነትና የነጻ ሃሳብን ጠቀሜታ የሚሰብኩን ናቸው ይበጃል የምንለውን ሀሳብ ስላራመድን ሌቦች ሆዳሞች ባንዳዎች የሚሉን

እውን አለሜ በገዛ ነጻነታችን የፈለግነውንና ያዋጣናል ያልነውን አቋም ልናራምድ የማያስችለን ከሀዲነት ምን ይሆን? አገርስ መውደድ በአንድ ከረጢት ተቋጥሮ ለአንድ ጎራ የተቃውሞ ወይም የድጋፍ ቡድን የሚሰጥ ነው?

አፍ ካለሽ ተናገሪ አንቺ አገር እየጠየኩሽ ነው? አሁን ማን ይሙት ሀገር ጥላቻ ማገርና ቋሚ ሆኖ ይገነባዋል? አሁን ማን ይሙት ሀገሬ ልጆችሽ በሚያምኑበት ይዘት ትንታኔና ብስለት መሸናነፍ ተስኗቸው ነው አንዳች የጥላቻ ዛር ሲተፉ የሚውሉት?

እውን አንቺስ አገር በዚህ መሰሉ የጥላቻ ዝማሬያችን ያገኘሽው ጥንካሬ አለያም የኳልንሽ ውበት አለ  ይሆን? ነተረኩሽ አደል ግዴለም ልጠይቅሽ ግድየለም ልጨቅጭቅሽ

አለሜ አንዳንዴ ግርም ይለኛል! ምን መሰለሽ ልጆችሽ ዴሞክራሲን ከሚያጣጥሙትም ሀገር ለረጅምም አመት ተቀምጠው ሰከን ብሎ ተከባብሮ መነጋገር ይሳናቸዋል እንዲያው ምን ይሆን ምክንያቱ ባክሽ?

እማማዬ አዋራጅ የንግግር እና የውይይት አማራጭ ተጠቅመው ሲናገሩ እያየናቸው የሚኖሩባት አሜሪካና የሚኖሩበት አውሮፓ ዲሞክራሲያዊ ልምድ ያልገባቸው መሆኑን እንዲህ ያለው ተግባራቸው እያሳበቀባቸው ምንም ባለማፈር እናት አገር አዋረድናቸው ብለው ዝና ሊሸምቱ ሲሞክሩ እንታዘባለን 

እማምዬ መጽሀፍ ክብራቸው በነውራቸው ነው የሚለው ለኛ ይሆን እንዴአንቺ አገር እውን የኛ በዚህ ደረጃ ለመነጋገር አለመፈለግ የዚህን ያክል የተንፈራቀቀ አቋም መያዝ የኛ የዚህን ያክል መዘላለፍ ጌጥ ይሆንሽ ይሆን? እውን የጎደለው ጓዳሽ እውን የገረጣው ፊትሽ ይህን በመሰለው ልማዳችን ያምርበት ይሆን?

እኮ ማነው የሀገር ፍቅርን በየጎራው እየለየ እቺ የተቃዋሚ እቺ ደግሞ የደጋፊ ናት እያለ የሸነሸናት? እኮ ማነው ሀገሬ እንዴት ላፈቅርሽ እንደሚገባና እንደማይገባ ፍቃድ የሚሰጠኝ?
እኮ ማነው ያንተ ፍቅር ጎዶሎ ነው ብሎ ካበቀለኝ ምድር የሚነቅለኝ? እኮ ማን የማይናወጥ የመፍረድ ስልጣን ቸሮት ነው እኔ እንጂ አንተን ብሎ ባላገር ፍቅር የሚለኝ?

አንቺ የፈለግሺው አፈርሺን የሚያበቅሉባት አራሹን ገበሬ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ደሀ አሰራሩን የሚያሻሽሉለት ላቡን ሳይጠየፉ አመለካከቱን ሳያጣጥሉ የቀረውን የሚሞሉ ጎበዞች ነው? ወይስ የወሬ አርበኞች እኮ አፈርሽ በስድብ ፈብራኪዎች ሊታረስ ነው?

ወይስ ስራ አጡ ወጣት በአፍ እላፊ የፈጠራ ብቃቱ ሊሻሻል ነው ይሄ የፖለቲካ ምህዳር እንዲህ በጥላቻ ስድብ እና አሉባልታ የሚናጠው? እናት አለም እዚህ አገር ትልቁ ቁምነገር መጠላላት እና መወራረድ ሆነ እውን ጌጤነው በርቱልኝ ፍቅራችሁን በዚህ ግለጡልኝ ብለሽን ነው?

እኔ ሲገባኝ አንቺ የሚያምርብሽ በርግጥም ረሀብሽን የሚያስታግስ እርሻ አዎን የወጣቶችሽን ሀብት የመፍጠር አቅም የሚያጎለብት ብቃት የባለሀብቶችሽን ቢዝነስ የሚያፈረጥም ምቹ ሀኔታ የተማሪዎችሽን ብቃት የሚያንጽ ጥራት ያለው ትምህርት ተግባር እንጂ እውን አሁን ያንቺን ድህነት ተረብና ዱላቀረሽ መወራረድ ሊፍቀው ነው?

አንቺ አገር ምነው አፍ አውጥተሽ ሀገር በበሰለ ፕሮግራም ሀገር በጠንካራ ዲሲፕሊን እንጂ በጥላቻ በታጨቀ ተረብ እንደማይታነጽ ብትናገሪ?

እማማዬ ምንም ይሁን ምን ያው ልጆችሽ ስለሆን በዚያም በኩል ያለውን ወንድሜን እኔም በዚህ በኩል ሆኜ እማወራውንም ልጅሽን ለመማር አንቺን በተግባር በሚረባው አስተዋጾ እንድንወድሽ እድሉን አትንፈጊን!

የለም የለም አገር መውደድ መቃወም አገር መውደድ መደገፍ አደለም$
አገርማ መውደድ አለሜ የሚጠቅመውን የሚበጀውን አስተዋጾ ማበርከት ነው$ አገሩን የሚወዳት አስተዋጸው ይመስክርለት አገሩን የሚወዳት በሚወደድ ተግባር ያንጻት$

2 comments:

  1. well said,
    good politics is not emotion, it needs substance argument. How would it be possible to convince someone (who is short of basic human needs -food, education and health) play a decent politics,

    Look the young beautiful girls fleeing to the Arab world to cheaply sell their labour. How can one convince them not to be in either side of the corner game? If opportunity allows one, isn't either of the corner stand better paying than washing the Arab floors? Let's really think it in terms of the economic payoffs...after all politics may not be emotion but economics.

    ReplyDelete