Monday, May 20, 2013

ህዝባዊ ይሁንታ ተቃዋሚዎችና ኢህአዴግ


እነ Abraha Desta and et el ኢህአዴግ ይሁንታ ወይም ሌጂቲሜሲ የሌለው ስለመሆኑና ኢኮኖሚያዊ እድገት የግዴታ መሟላት ያለበት የመግቢያ ነጥብ እንጂ ምርጫ አሸንፎ ለመቀጠል የማያስችል ስለመሆኑ ነግረውናል። ሲጀመር ኢህአዴግ ህዝባዊ ተቀባይነት እንዲኖረው በአብዛኛው ህዝብ መመረጥ እንጂ በተቃዋሚዎች ወይም በተቃዋሚ ደጋፊዎች መመረጥ ወይም ይሁንታ ማግኘት አይገባውም። ይሄ መቼም ሊሆን አይችልም።

ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ ህዝባዊ ይሁንታ የለውም ሲሉን እያሉን ያሉት እኛ መሪ ፓርቲ መሆኑን አልተቀበልንም ከሆነ ትክክል ናቸው። ያ ካልሆነ የህዝቡን ይሁንታማ ህዝቡ በየምርጫው በነቂስ እየወጣ ገለጸኮ። መቼም ህዝብ በነቂስ ወጣም ለማለት እውነቱ ለተቃዋሚዎች ብቻ ሲሆን ነው ካልተባለ።

2ኛው ላነሳው የፈለኩት ቁምነገር ተፎካካሪ ፓርቲዎች ሁነኛ ስራቸው ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገብ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም የሚለውን ነው። ድህነትን መቅረፍና ተጨማሪ ሀብት መፍጠር ሌላ ምንም ፖለቲካዊ ስራ እንኳ ባይሰራበት ዴሞከራታይዝ የማድረግ አቅም አለው። ምክንያቱን እድገት የሚያመጣቸው ቁሳቁሶችና ሪሶርሶች የማህበረሰቡን መብት የማሳወቅ ለመብቱ እንዲከራከር አቅም የመፍጠር ተፈጥሯዊ ባህሪ አላቸውና።

 ያም ሆኖ ግን ኢኮኖሚ ብቻ በቂ አደለም ዴሞክራሲውም አብሮ ማደግ አለበት መባሉ አሳማኝ ነው። ይሄ እንዲሆን ግን የግድ መሪው ፓርቲ ቦታውን መልቀቅ አይጠበቅበትም። ግዜው የሚጠይቀውን አመራር እስከሰጠና የተሻለው ፓርቲ ሆኖ እስከተገኘ በሌሎች ዴሞክራሲያዊ ሀገሮች እንደሆነው ኢህአዴግ ለበርካታ አስርት አመታት መሪ ሆኖ የመቀጠል ዴሞክራሲያዊ መብት አለው። 

መሪ ፓርቲ መቀየር አለበት የሚል ዴሞክራሲያዊ እሴት የለም። ለዚያውም በጉዳዩች ዙርያ በፖሊሲ ዙርያ ሳይሆን መሪ ፓርቲን ከስልጣን ማውረድን አላማቸው አድርገው ዘይትና ውሀ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በህብረት በሚሰሩበት የላሸቀ የተቃውሞ ፖለቲካ ባለበት ሁኔታ ይቅርና።

ምርጫ ዴሞክራሲያዊ የሚሆነው ፓርቲዎች ስለተቀያየሩ ሳይሆን ህዝቡ ይሰራልኛል የሚለውን ፓርቲ በየግዜው ወጥቶ መምረጥ በመቻሉ አለመቻሉ ነው። ህዝቡ እስከመረጠ ድረስ ያኔም አሁንም ኢህአዴግ ማሸነፉ ምርጫውን ስህተት አያደርገውም። የሚያመላክተው የተገላቢጦሽ ለሀላፊነት የሚበቃና እምነት የሚጣልበት ብቁ ተቃዋሚ ፓርቲ አለመኖሩን ነው።

ሌጂቲሜሲ ወይም ይሁንታ የተቃዋሚዎቹ ካድሬዎች እንደሚነግሩን የአሸናፊው ፓርቲ የመቀየያየር አለመቀያየር ወይም የተቃዋሚዎች ኢህአዴግ አገር ለመምራት ብቃት አለው የሚለው ይሁንታ አደለም። ቀላል ነው በቃ የአብዛኛው ህዝብ ለኢህአዴግ ካርድ መስጠት ይሁንታ ነው። ይሄ ያልበሰለና በቅጡ ያልታሰበበት ነጥብ የስልጣን ኮርቻውን ለማግኘት በመቋመጥ የመጣ ሌላ መከራከሪያ ነጥብ መሆኑ ነው። ቀሽም ክርክር ቢጤ ነው ለኔ።

ለመመረጥ ቁምነገሩ ብቁ አማራጭ ፓርቲ ሆኖ መገኘት ነው። ተፎካካሪ ፓርቲን በማጠልሸት ሳይሆን በራስ ፖሊሲና ፕሮግራም ዙርያ መተማመን በመፍጠር ህዝብን አሰባስቦ አሸናፊ መሆን ነው ቁምነገሩ። ሰባራ ሰንካላ ምክንያት እየደረደሩ ይሄን ኢህአዴግ ስለከለከለ ይሄን ሴራ ስላካሄደብን የሚሉ ሰብብተኛ ፓርቲዎች የመሪነቱም ቦታ ቢሰጣቸው ተመሳሳይ ሰበባቸውን እየጠቀሱ በዚህ ምክንያት ሳናድግ ቀረን በዚህ ምክንያት ይሄ የዲፕሎማሲ ስራ ከሸፈብን የሚሉ ሰበብተኛ ከመሆን የሚድኑ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለንም። 

የሰበብ ስብራታችሁን እና ተሸናፊ ስነልቡናችሁን መጠገን። ይህን ድቀት በአደባባይ ሁሌም ኢህአዴግ ስህተቶቹን በአደባባይ እንደሚያምነው ዋጥ አድርጎ በእልክ ህጋዊ አማራጮችን አሟጦ አሸናፊ ሆኖ መገኘት ወይም ደግሞ በዚያው ሂደት የአገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ባህል አሸናፊ እንዲሆን ማስቻል ነው። ይቆየን።

No comments:

Post a Comment