Friday, June 7, 2013

የአባይን ግድብ በግብጸቹ አይን 1

ግብጽና ናይል ናይልና ግብጽ አንድና ያው ናቸው እየተባለ ያደገ ህዝብ$ በዚህ ረገድ አደጋ የምትሆን ታሪካዊ ጠላት ኢትዮዽያ እንጂ ሌላ ማንም አደለም እየተባለ የኖረ ህዝብ ለማመን ቢያመነታ አይገርምም$ በውል መወያየት ጉዳዩን በወጉ ማሳየት ያለባቸውና እውነቱን የሚያውቁት የግብጽ ፖለቲከኞችና ሚዲያው ሲቆምር ግን ይደብራል$

እያወራን ያለነው ግብጽ ቅኝ ገዢዋን እና ጎረቤቷን ሱዳንን በማስማማት ለሀገራችን አንድ ጣሳ ውሀ ያስፈልጋታል ሳትል በስግብግብነት ስለፈጸመችው የዛገ ውልና ይህንኑ አሳፋሪ ስምምነት ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መብቴ እያሉ ስለሚደሰኩሩት ለዚህ ዘመን ስለማይመጥኑ ፖለቲከኞች ነው$

60 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር ዉሀ የምታበረክተው ምድር ህዝብ ጥምና ርሀብ ይፍጅህ ተብሎ 56 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር የሚጠጋውን ውሀ ያለማቅማማት የኔ መብት ነው ስትል ለሱዳን ደግሞ ከ20 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር በላይ ውሀ ትታላታለች$ ለኢትዮዽያዬ የቀራት ግን ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጠላት የሚል ቅጥያ ነው$

ግብጽ ውሀ አጠር አካባቢ ከመሆኗ አንጻር ከሁሉም አገሮች የተለየ ውሀው እንደሚያስፈልጋት እናምናለን ይሄ ማለት ግን እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚል የቀረርቶ ፍቃድ ይኖራታል ማለት አደለም$ ሀገሬ ግብጾቹ ሲያሻቸው በሱማሌ በኩል ሲያሻቸው በኤርትራ በኩል በሚያደርጉት የማመስ ስትራቴጂ ዋጋ ስትከፍል መኖሯ የአደባባይ ሚስጥር ነው$

ሰሞኑን ያን የጎን ውጋትነታቸውን ለማቀጣጠል ሶማሊያ ጎራ ማለት መጀመራቸውንም እናውቃለን ለዘመናት አብረን የኖርነው ሀቅ በመሆኑ እምብዛም አይገርመንም$ ከውስጥ ካልተሰነጠቅን በቀር ማንም ከውጭ ሊሰብረን እንደማይችል ጠንቅቀን ስለምንረዳ$ አንድ ሀሳበ ሰባራ ኬንያዊ በዴይሊ ኔሽን ጋዜጣቸው እንደተመኘልን ግብጾቹና እኛ መራኮታችን እግሯ ለሰለለባት ሀገሩ ኬንያ ጥሩ ዜና መሆኑን ነግሮናል$ በመድከማችን ሊጠነክር መሆኑ ነው$ የዚህ ሰንካላ አስተሳሰብ ፍልስፍና የምትሮጥን ኢትዮዽያን መብለጥ ሳይሆን ከደቀቀች ሀገር የተሻለ ሆኖ መታየት መፈለግ ነው$

ይሄው ኬንያዊ ግብጽን ሲመክር ኢትዮዽያን ለማተራመስ ቀላሉ መንገድ ከአዲስ አበባ ጋር አይንና ናጫ የሆነውን አልሼባብን ማጠናከር ሲቀጥል ደግሞ የኦጋዴኑን ነጻ አውጪ በማስታጠቅ ኢትዮዽያን መበጣጠስ ነው$ በርግጥ ሀገሩ ኬንያም ያን የአሸባሪዎች የሶማሌ ጋጋታ አይታ እንዳላየች ስታልፈው ኖራ ዋጋ አስፍሏት ነው የሶማሊያውን የኢጋድ ስምሪት ያገዘችው$ የሆነ ሆኑ ጠጥም ፈስ ሆኖ በስተመጨረሻ መጥታ ስታበቃ አልሼባብን ሰባበርኩት ለማለት ዳድቷት እንደነበር ይታወሳል$

ኢትዩዽያዬ ስትታመስ ጥሩ እንቅልፋቸውን ሊተኙ የሚመኙ ሰዎች እንዳይኖሩ በርግጥ አንመኝም እዚሁ አገራችንም ሆነው ወያኔን ግብጾቹ ባንበረከኩልን የሚሉ ሀገርና የፓርቲ ልዩነት የማይገባቸው የይስሙላ የዴሞክራሲ ታጋዩች አሉንና$ ሰብአዊ መብት በታፈነበት ግድብ ተገደበ ቀረ የወያኔ ወሬ ነው የሚሉን ቅጣንባሩ የጠፋቸው እዚሁ ሞልተው ስለተረፉን የኬንያዊው ክፉ ምኞት አያበሳጨንም$

ግብጻዊ ብሆን በ2050 150 ሚሊየን ስለሚሆን የህዝብ ብዛታችን ተጨማሪ እስከ 21 ቢሊየን ኪውቢክ ሜትር ውሃ ያስፈልገናል ብዬ አስባለሁ ኢትዮዽያም በተመሳሳይ ግዜ ከግብጽ የሚበልጥ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደሚኖራት ግን መዘንጋት የለብኝም$ ግብጻዊው ምግብ ውሀ ኤሌክትሪክ እንደሚፈልገው ሁሉ ኢትዮዽያዊውም ያ እንደሚያስፈልገው አይጠፋኝም$

እኔ ብቻ ማለት ግን አይገባኝም እኔ ያልኩት ካልሆነ ሳተራምሽ እኖራለሁ ስፈልግም አደባይሻለሁ የሚል ፉከራ አይገባኝም አንድም የሚፎከርባት ሀገር ኢትዮዽያዬ ስለሆነች በሌላም በኩል ግብጾቹ እንዲህ እንዲባጥጡ ተፈጥሮም ይሁን የቅኝግዛት የተንሻፈፈ ስምምነት መብቱን ስለማያጎናጽፋቸው$


የጨለማው ዘመንም ቅኝ ግዛትም አላንበረከከን ስንኳንስና ሊያተራምሱን በደቡብና በሰሜን ሲማስኑ የኖሩ የግብጽ ፖለቲከኞች$ ቀጣዩ ክፍል ይከተላል$

No comments:

Post a Comment