Monday, June 17, 2013

ተቃዋሚዎች የግብጽን የቤት ስራ እየሰሩላት ይሆን?-1

አንዳንድ ዜጎቻችን ግብጽ የሰጠችንን የቤት ስራ በአግባቡ እንድንፈጽም ይወተውታሉ$ ለግብጽ እጆቿ ሆነው ተልእኮ ለመፈጸም እያቅማሙ ያሉ እንዳሉ አያለሁ$ በኛ ይሁንባችሁ ግብጽን አንችላትም አርፈን እንቀመጥ ከሚሉን የመክሸፍ ፖለቲከኞች ጀምሮ የኢትዮዽያ ሰራዊት ግብጽን ከግምት ያስገባ ዝግጅት አላደረገም እስከሚሉን ድረስ ተረኩ አንድና ያው ነው$

ኢህአዴግ ለፖለቲካ ትርፍ እንዳይጠቀም ብሎ መፈክር ማስነገሩ እራሱ ለፖለቲካ መጠቀም መሆኑ ገሀድ ሆኖ ሳለ ለግብጽ የረጋ ያልረጋ መግለጫ ያልሰጠውን ኢህአዴግን ባልበሰለ ፖለቲካዊ ቁመናው አንድነት ሊመክረው መከጀሉን ሳይ ሳቅ ቢጤ ከጅሎኝ ነበር$ ምንም ያክል ልዩነት ቢኖር ይሄን አይነቱን የግብጽ ፖለቲከኞች አጉራ ዘለል ባህሪ ለመተቸት በቀጥታ መናገር እንጂ ነጥብ ለማስመዝገብ በማሰብ የአባይንና የግድቡን ጉዳይ በዚያ መልኩ አውገርግሮ ማቅረብ የወረደ የፖለቲካ ቁመና ማሳያ ነው$ ይበስላሉ ተብለው ከሚጠበቁ በወጉ ካልተደራጁ ፓርቲዎች በመስማቴ በርግጥ እምብዛም አልገረመኝም$

ያለበቂ ዲፕሎማሲና ውይይት ያልተጀመረ ግድብ?

አዬ አንድነት መግለጫ አውጥቶ ሞቶ ለዘመናት በህዝብ ህሊና ሲመላለስ የኖረውን የአባይን ጉዳይ ያልተወያየንበት ሲል አላፈረም$ የዚህ አይነቱ ንግግሩ የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለማያውቀው ነው በርግጥ$ ይሄ ያልተመከረበት የግድብ ጉዳይ ሀገራችን በደቡብ አፍሪካው እግር ኳስ ቡድን ላይ ድል ስትቀዳች በአጋጣሚ አደለም በደጋፊው ደም ውስጥ የተዘዋወረው$ ጭፈራው አባይ ይገደባል ነበር$ ያልተመከረበትስ የአንድነቱ ፕሮፓጋንዳ ነው የአባዩን ግድብ ለፖለቲካ የማዋል ትልም$

አንድነቶች በዚህ አላበቁም ሌላ ሌላውን ትተነው ኢህአዴግ የሚመራው መንግስት ባለፉት አስራሁለት አመታት ያደረገው የአባይ ተፋሰስ ዲፕሎማሲ ስራና የተፋሰሱ ሀገሮች ስምምነት የት ገብቶ ነው በዲፕሎማሲው መስክ ሳይሰራበት የሚል ተልካሻ መከራከርያ ያቀረበው$ ኢህአዴግ በተቡ እጆቹ የቀረጻቸውን ስኬቶች እናቆሽሽ በሚል የሚነዳው አንድነት ያለበቂ ዲፕሎማሲያዊ ስራ የተገባበት የህዝብን ተቃውሞ አቅጣጫ የማስቀየር ፕሮጀክት ሲል የገለጸው ምናልባት አተርፍ ብሎ ነበር$ አጎደለ እንጂ በአባይ ላይ ድርድር ከማያውቀው ህዝብ የበለጠ ተነጠለ እንጂ$

ለመሆኑ የትኛው ተቃውሞ ነው አቅጣጫው የሚቀይረው$ እዚ ግባ የሚባል በህዝብ ጉዳዩች ላይ የማይሰራ ቅንጥብጣቢ ፍለጋ የተሰባሰበ ተቃዋሚ ነው ህዝብ አደራጅቶ ጠንካራ ተቃውሞ የሚፈጥረው$ ልብ እንቅርት ይመኛል አሉ እማማ ኩሉ$ ሲባል ተሰምቷል$ ኢህአዴግ ከወትሮው በጠነከረ ህዝባዊ ድጋፍ የልማት ውጥኖቹን በላቀ ትጋት እየፈጸመ ያለበት ግዜ ነው$ ተቃውሞ እንኳ ቢኖርበት ኢህአዴግ ተቃውሞ ለማብረድ ህዝብን የበለጠ አያስጨንቅም$ ገንዘብ አዋጡ የአካባቢያችሁ ልማት ላይ 20 በመቶ ሸፍኑ ቁጠባ ቆጥቡ ለቤት ስራ ሌላ ቁጠባ ግቡ ማለትና ተቃውሞን ለማስቀየስ አደናባሪ ስራ መስራት የተለያዩ ናቸው$

ልበሙሉ ፓርቲና መንግስት ካልሆነ እንዲህ ያለውን የተለጠጠ ስራና የህዝብ ተሳትፎ ሊጠይቅ አይችልም$ በርግጥ ይሄ የሚባለው የግብጹ አይነት ማእበል መጥቶ ኢህአዴግን በጠራረገው ከሚል ስልጣን የመያዝ ጉጉት መሆኑን እረዳለሁ$ መመኘት አይከለከል እድሉ ቢገኝ የመምራት አቅሙ የለም እንጂ የሀገሬ ሰው ከበሮ በሰው እጅ ያምር የሚለው ለዚህ ለዚህ እኮ ነው$ እውን አንድነት ለአባይ ግድብ ወገንተኝነት ለማሳየትም ኢህአዴግን ካልወረፈ አይሆንለትም ማለት ነው? መለከፍ እኮ መጥፎ ነው$ ወቀሳ ሱስ ሆነባቸው ማለት ነው$ ማንንም ሳያጣጥሉ መልእክት ማስተላለፍ ይቻል ነበር$

ዳሩ ጡት ነካሽ አይጠፋ ለግድቡ ዶላር ዳያስፖራው እንዳያዋጣ ከመወትወት ለመሰብሰብ በሚደረገው ጥረትም ላይ ለማደናቀፍ የሰሩትን የተረገመ ተግባር ስለማልረሳ ግብጽን አበጀሽ ማለታቸው አይደንቅም$ እግረ መንግዳችሁን ኢህአዴግን ብትገላግሉን እና ቦታውን ለኛ ብታመቻችሉን ግድቡን በመተው እንክሳላን እንደሚሉ አይሳትም$ ለዚህ እኮ ነው አስመራና ካይሮን ሳይረግጡ የማይውሉ ለሀገራችን እየታገልን ነው የሚሉ ተቃዋሚዎች ሞልተው የተረፉን$ ለሀገራችን ብለን ሲሉ ሀፍረት እንኳ አይሰማቸውን እኮ ደሞ$ እኮ ለሀገር ግድቡነው ፋይዳ ያለው የግብጽ ሎሌነት?

በርግጥ አንድ የመድረክ አባል ግድቡ በተጀመረ ሰሞን ስለአባይ ተጠይቀው ”የአባይን ልጆች ጠይቂያቸው“ የሚል መራራ መልስ መስጠታቸውን እናስታውሳለን$

እኮ አባይን ለመገደብ ስንት ሺ ዘመን እናስብ? እኮ ግብጽን ለማሳመን ስንት አስርት አመታት እንምከር? እኮ አንድነትና መሰሎቹ ይሄን የመሰለ የሀገር ክህደት እየፈጸሙ ነው አባይን ለፖለቲካ እንዳያውለው ኢህአዴግን የሚያሳስቡት$ ኢህአዴግማ በያንዳንዱ ኢትዮዽያዊ ደምስር የሚላወሰውን አባይን ነፍስ ዘራበት$ የምስራች አባይ ጨለማ ገላለጠ የምስራች አባይ ሚሊዮኖች ዶላር ሆነ የምስራች አባይ እሸት ቦቆሎ ሊያበላን ነው የሚል ተረክና ተግባር እያቀጣጠለ አገርን ከዳር ዳር ለልማት አነቃነቀ$

ለነዚህ አይነት የተግባር ጀግኖች ክብር አለን$ ትላንት ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው ጨቋኙን ስርአት ገላገሉን ዛሬ ደግሞ ግዜው የሚጠይቀውን ዲፕሎማሲና ሀብት አሰባስበው የአፍሪካውን ቁጥር አንድ ባለ 6000 ሜጋ ዋት የመብራት ሀይል የሚያመነጭ ግድብ ሰርተውልናል$


የአካባቢውን የመጠፋፋት ፖለቲካ ተቋቁሞ ከትንሿ ሀብታችን የሚቻለውን ሀብት ሰብስቦ የላቁ የልማት ትልሞቹን የሚተገብር ፓርቲ በመሆኑ ኢህአዴግ ለላቀ አስተዋጾው መበረታታትና መደነቅ አለበት$ ስንኳንስና ኢህአዴግ መድረክስ የተፈረካከሰ ቁመናውን ይዞ ያለኔ አሳር ይለን የለ? ተቃዋሚዎቹ ለግብጾቹ እየሰሩ አለመሆናቸውን እያንዳንዱ ዜጋ የማረጋገጥ ሀላፊነት አለበት በአገር አይቀለድምና$

No comments:

Post a Comment