Monday, August 19, 2013

ለምን አይታወስ አጽሙን ለዘመናት እንዘክረዋለን


ስለቀደሙ ነገስታቶቻችን አውርተው የማይጠግቡ ወዳጆቻችን ስለመለስ ማውረቱ ቢቀርባቸው አንኳ ስለሱ በሚወዱት ግለሰቦችና በፓርቲ ጓዶቹ መዘከሩ ለምን ያንገበግባቸዋል
 
አሁን መለስ የቀረው ይቅር እንደው ለነገስታቱ የሚከትቡትን ያክል የሚከትቡለት ስኬቶች ብልህነቶች ድሎች አተውለት ነው ወይስ በሱ አመራር ወቅት የተከሰቱ ድክመቶች ነገስታቱ ከሰሯቸው ስህተቶች ገዝፈው ነው ወዲያ መንደር ያሉ ወዳጆቻችን በዘከርነው ቁጥር ምርር ብለው የሚያለቅሱት

እነሱም አልነበሩ የትኛውም ንጉስና መሪ ከነችግሩ ሊያስመሰግነው በሚገባው ሊታወስ ሊደነቅ ይገባዋል እያሉ ሲሰብኩን የነበሩት
ዘክሩ ብለን አላስገደድን በገዛ የመዘከር መብታችን ለምን ይነተርኩናል

በርግጥ የኛ መንደር ዝክር ወቀሳና ትችት ተጠምቆ የሚጠጣበት አደለም እኛ ሰፈር ዝክር ዛፍ ተከላ የፖሊሲ ክርክር የልማት ቃልኪዳን ማደስ የአመራር እና የፖሊሲ ስልጠና ነው እኮ ለምን ብለን ጣላቶቹን እንውቀስ እኮ ለምን በሌሎች ላይ ጣት እንቀስር ዘመን የሚሻገሩ ችግር በሂደት የሚያረግፉ የፖሊሲና የተግባር ውይይቶች እያሉን እኮ ለምን ድዳችንን ውሀ በማይቋጥር ጉዳይ እናልፋ

በርግጥ ሰውየው በአመዛኙ አማራና ትግሬ ሲነዳው የነበረውን የዚህን አገር ስልጣንና የፖለቲካ መድረክ በየብሄሩ አስደፍሮታል
በርግጥ ሰውየው የሰሜኖቹን በመላው ሀገሪቱ የነበረ የማስተዳደር ስራ የየአካባቢው ሰው ራሱን ለማስተዳደር አያንስም በሚል ህገመንግስታዊ ድንጋጌና ፈሊጥ የየብሄሩን ተፈጥሮ የሚያከብር አሰራር ደንግጎ በስንቱ ተሿሚና ተጠቃሚ ጉሮሮ ላይ ቆሟል

በርግጥ ሰውየው አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ የሚፈጥር ህገመንግስትና ፖሊሲ በአግባቡ ይሰናዳ እንጂ ህዝብ በየቋንቋውና ባህሉ መሰረት ሊፈጽመው ይችላል በሚል ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ነባሩን የአማራኛን ሚና የሚቀይር አሰራር ዘርግቷል የሚገርመው ክሽን ባለ አማርኛ ሀገር መምራቱን አለመዘንጋቱ ነው

በርግጥ ሰውየው የተሻልን ነን የላቅን ነን የሚለውን የአንዳንድ የመሳፍንትና የነገስታት ዘር ቆጣሪዎችን እኩል ነን በሚል ታርጋ ማውደሙ ሲታይ ክብራቸውን ዘር እየጠቀሱ ለሚቀዱ ሰዎች ሬት መሆኑ አጠያያቂ አደለም

በርግጥ ሰውየው ኪራይ ሰብሳቢ ነፍጠኛ ጠባብ ትምክህተኛ አሸባሪ ጎጠኛ ጥገኛ የሚባሉትን ልምዶችና ጥቅሞች ለማፍረስ የተፋለመ ከመሆኑ አንጻር ሲታይ ብዙዎቹን ማስኮረፉ አልቀረም

በርግጥ ሰውየው የስንቱን ቤትና አጥር የእርሻ መሬት ወዘተ መንገድ ሲገነባ ኤሌክትሪክ ሲያመነጭ ዉሀ ሲቆፍር ትምህርት ቤት ሲገነባ ጤና ጣብያ ሲያንጽ ያወደመ በመሆኑ ይታወሳል ቅሉ ካሳ ቢከፍልስ ማን ይህን ለመሰለ ተግባሩ ይዘነጋዋል እንጂ

በርግጥ ሰውየው በግርግር ወደስልጣን ርካብ ለመንጠላጠል ለሚመኙ ሰዎች የማይመቹ ህጎችና ዴሞክራሲያዊ አሰራሮች እንዲቀመሩ አመራር የሰጠ በመሆኑና ያን በማስተግበሩ ይኮነናል በተለይ ይሄ የአሸባሪ ህጉ በአመጻ መንጠላጠል ለሚፈልጉ የፈጠረው ደንቃራነት የዋዛ አደለም

በርግጥም ሰውየው መራራ ትግል በሚጠይቀው የታሪካችን ወሳኝ ወቅት በቅቶ በመገኘት ለስሙና ለዝናው ሳይሆን ለሀገር ይበልጥ ለሚጠቅመው ልማትና ዘመን ተሻጋሪ ዴሞክራሲያዊ ትግል ከመራራ አስተሳሰቦችና አሮጌ ልምዶች ጋር የተፋለመ ነው

አዎን ቁልቁል እየተፈጠፈጠች የነበረችን አገር ሽቅብ ለማንደርደር የሚከፈለውን ዋጋ ከፍሎ ኢኮኖሚያዊም ፖለቲካዊም ትንሳኤዋን የጠነሰሰ በመሆኑ በርካቶችን የድህነት ውስጥ ከበርቴዎችና ተጠቃሚዎች ማስቀየሙ አይቀሬ ነው

ፍንትው ብሎ እንደሚታየው ግዙፍ አድናቂዎች ጥርት ብሎም እንደሚታየው መራራ ጠላቶችና ወቃሾችም አሉት

መልአክ አልነበረም መልአክ ነኝም አላለም ግን የሰው ልጅ እቺን አገር ሊሰራትና ሊመራት በሚችለው ሚዛን ሲሰላ  ለዘመናት የማንዘነጋቸው በመቶ አመታት ታሪኮቻችን ያልተሳኩ ጉዳዮችን በሁለት አስርት አመታት ብቻ በተዋበ የፖለቲካ ፍልስፍናና በሚቆጠሩ ኢኮኖሚያና ፖለቲካዊ ስኬቶች ያንቆጠቆጠ ጀግና ነው

ለምን አይታወስ አጽሙን ለዘመናት እንዘክረዋለን
ደግሞስ ይሄ ሁሉ ወቀሳ በስሙ ዛፍ በተከልን ነው በስሙ የፖሊሲ ክርክር ስላደረግን ነው በስሙ የአረንጓዴ ልማትና የልማታዊ መንግስትን ፍልስፍናዎች ይበልጥ ስለተነተንን ነው በስሙ የአገር ልማትና እድገት ግስጋሴያችንን ለማስቀጠል ቃል ኪዳን ስላሰርንና ስላደስን ነው

ለምን አይታወስ አጽሙን ለዘናት እንዘክረዋለን!
ቁምነገሩና ልዩነቱ ያለው የኛ ዝክር ወቀሳ መጥመቂያና የትችት ናዳ ማጉረፊያ አለመሆኑ ላይ ነው

ኢትዮዽያዬ በቁሙም በሞቱም ዛፍ የሚያስተክልና የልማት ግስጋሴሽ ማነሳሻ ቀንዲል የሚሆን መሪ ደጋግሞ ይስጥሽ ለፓርቲውና ለህዝቡ ውስኪ መራጨትንና ድግስን ሳይሆን ትጋትንና የሚንተገተግ የልማት ተነሳሽነትን አውርሶ የሄደ መሪ

ድህነት ያለእረፍት የሚገላትንና የሚያማትን ሀገር ቀን ከሌት ያለእረፍት ከ20 አመት ለሚልቅ ግዜ ያገለገለ ሰው መለስ ዜናዊ!
ማረፍ እፈልጋለሁ እረፍትን ማየት እፈልጋለሁ እያለ ለሚያማትና በየለቱ ለምትሞት ሀገሩ እረፍት ሲሰራ ያረፈን መሪ ካልዘከርን እኮ ማንን ልንዘክር!

እናስ ለዘመናት ዜና ሆኖ ቢኖር ለወጣቶች አብነቱ ቢተርፍ እንጂ ምኑ ላይ ነው ጉዳቱ

በርግጥ ለትችት ጠማቂዎቹ ዝምታው ንግግሩ ሳሉ ፖሊሲው ፍልስፍናው ልማቱ ህመሙ ሞቱ ቀብሩ ሚስቱ ልጆቹ ትውስታው መዘከሩ ሁሉ ህመማቸው ስለሆነ ዛሬም ያንኑ ዘፈን በአዲስ ገንቦ ጠምቀው ቢያሽጎደጉዱት አይገርመንም

እነሱም ይጮሀሉ እኛም ትዝታውና ዝክሩ ዛፍ እያስተከለን የሀገራችንን ህዳሴ በአረንጓዴ ልማት እንድናጅበው ስንቅ እየሆነን ይዘልቃል!

No comments:

Post a Comment