Tuesday, December 18, 2012

አሸናፊ አባባሎች



በፉከራ በቀረርቶ ወይም በስራ አልባ ህልም ተፈጥሮ አትረታም::
የታለመ ተግባር ግን የማይቁዋረጥ ስራ ግን ያንበረክካታል::
አሸናፊ መሆን የሚሹ ኢላማቸውን ይሰሩታል ይኖሩታል!!

በማንኛዉም አንድ ጉዳይ ላይ ከሁሉም ጋር ለመግባባት የሚሹ ሰዎች
እብዶች ናቸው
በሁሉም ነገር ከሁሉም የሚለይ እና በሁሉም ነገር ከሌሎች ጋር የሚመስል
ሲጀመር እብድ ነውና
ብልሆች ህጋዊ በሆነና ባመኑበት ጉዳይ ይሰሩበታል
የሚስማሙትንም የማይስማሙትንም አክብረው!!!

መሆን የምትፈልገውን አትቅጠር ዛሬ ላይ ሁነው አድርገው
አለም ለይሉኝታህ ግድ የላትም
ተግባርህን ግን ትከፍለዋለች
ቁምነገሩ ክፍያህ ትልቅና በጎ እንዲሆን በአግባቡ መተለም 
ብቻ ነው!!!

ዛሬን እንዳመነው እንኑረው ደስታ የወደዱትን መኖር መቻል ነውና
ወሬውን ለባዮቹ ተወው ወሬያቸው እምነታቸው እንጂ እምነትህ አደለምና
ያንተ የሆነው እምነትህና ያንኑ የምትኖርበት ግዜ ዛሬ እና አሁን ብቻ
ናቸው!!! በቃ ኑረው ሁነው!!

አገርም ዛሬ በታመነው ዛሬ የሚሰራባት የኛ ስብስብ እንጂ
የንትርክ ቅርጫ የጭቅጭቅ መድረክ አደለችም
ዛሬ ስንሰራ የምታድግ
ስንነታረክ ደግሞ
እምትማስን ናት 
የሚወዱዋት ዛሬን ይኖሩታል!!!

No comments:

Post a Comment