Tuesday, December 11, 2012

ትዝብቴ



ሁላችንም ችግር አለ ባዮች ነን።

ታክሲ ችግር፣ ቤት ችግር፣ ራስ መቻል ችግር፣ ስራ ችግር፣ ግንኙነታችን ችግር። ችግር ያልሆነ ነገር ያለ አይመስለኝም።በግልባጩ ደግሞ እነ እገሌ ናቸው የሚል ጣት መጠቆም እንጂ ሃላፊነት የሚወስድ የለም።

እና ግራ የሚገባኝ ችግሩን ማን ፈጠረው ሊባል ነው። ይህ እኔን ይመለከተኛል የሚል ሃላፊነት መውሰድ የሚችል ልምድና ስብእና በሌለበት እውን የችግሮቹን መነሾ ፈትሾ መፍትሄ የሚሰጠው ማን ሊሆን ነው።

እቺ ሸሸት ሸሸት እምታዋጣን አይመስለኝም እንዲያውም በሺዎች ለሚቆጠር ታሪካችን ሁነኛ መለያ ልምዳችን ሀላፊነት መውሰድን መጥላታችን ይመስለኛል። ለድህነታችንም ሁነኛው ምክንያት ይህ ይመስለኛል።

እኔን ይመለከተኛል ያልን እንደሆነ ምን እንዳይሆን ነው። ክደን ኖረን አይተነዋል ከዛሬ ጀምረን የለም አልሸሽም ይህ የኔ ጥፋት ነው ማለት ብንጀምርስ። ባላጠፋ እንኩዋ ይህን እኔ ሀላፊነት ወስጄ ልፍታው ማለት እንልመድ። ማንም በጥፋተኝነት አይረገም ግን እሺ ማን ይፍታልን ችግራችንን? አማልክት?! አይመስለኝም::

አለም የተለወጥችው ሀላፊነት መውሰድ በቻሉ አንዶችና ጥቂቶች እንጂ በችግር አለ ባይ ባዶ ጭሆቶች አደለም። ችግሩን የተረዳው ዳዊት መፍትሄውን ካላመጣ ዳዊት አደለም። 

መፍትሄው ችግሩን መተረክ ሳይሆን ችግሩን ፊትለፊት ባመንበት አማራጭ መጋፈጥ ነው። ስትጋፈጥ አትወደድ ይሆናል መፍትሄ ግን ስለመሆንህ ጥርጥር የለውም።

No comments:

Post a Comment