Sunday, December 23, 2012

እንዲሁ እንዋደድ በምክንያት እንመን!!!

ለመዋደድ እምነትና አቁዋማችን አንድ መሆን አለበት እንዴ
እንዲሁ እንዋደድ በምክንያት እንመን!!!

በተለያዩ ግዜዎች አንዳንድ ወዳጆቻችን ስታስጠላ አታፍርም ደባሪ ምናምን የሚል 
ኮሜንት ፖስት ሲያደርጉ አያለሁ እኔም ያጋጥመኛል

ግን ሲገባኝ ሰው መጠላት እንኩዋ ካለበት ስለ ስነምግባሩ ክፉነት እንጂ አቁዋሙ
የተለየ ስለሆነ አይመስለኝም መሆንም የለበትም

ለመወደድስ ተብሎ ምን አቁዋም ሊያዝ ይችላል እምነትና አቁዋማችን እኮ እንደ መልካችን
የተለያየ ነው

መዋደድ ያለብን እንዲሁ ነው ሰው ስለሆን በቃ
አቁዋምና እምነቶቻችን ግን የየራሳችን ይሆናሉ ቁምነገሩ ሀሳቦቻችን በምክንያት ይብራሩ እንጂ
የተለየ አቁዋም መያዝ ተፈጥሮአዊ መብትና ሰብአዊ ክስተት ነው

እንዲሁ እንዋደድ በምክንያት እንመን!!!

No comments:

Post a Comment