Friday, December 28, 2012

የተቃዋሚው ጎራ የትግል ታርጋ

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ችግሮችንና  መነሻቸውን ተንትነው መፍትሄዎችን ተልመው እንዲነሱ ይጠበቃል  የትግበራ ስትራቴጂያቸውን እና ታክቲኩን ቀይሰው በዚህ አይነቱ የበሰለ ፕሮግራም ለውድድር የሚቀርቡም መሆን ፓርቲ የመሆን ግዴታ ነው ዲስፕሊን ያላቸው ብቁ አባላትና ደጋፊዎችም ማፍራት ለነገ እሚታለፍ ስራ አይሆንምበዚሁ ቁመናቸው ብርታት ምርጫዎችን በስኬት የሚሳተፉ ይሆናሉም ተብሎ ይገመታል

በኛ ሁኔታ ተቃወሚዎች የኔ ቢጤው መንደገኛ የሚያነሳውን የተቆራረጠ እዚህም እዚያም የሚታዩ የዋናውን ችግር ምልክቶች ከመተረክ እና ለሁሉም ችግር ያው የተለመደውን አስፕሪን እና መለጣጠፊያ ከማቅረብ በዘለለ ይህ ነው የሚባል ዘላቂ መፍትሄ ማቅረብ የሚያስችል ብስለትና መለኝነት የማይታይባቸው ናቸው

ለሁሉም ችግር ወደብ ስለለለ ብዝሀነታችን ህገመንግስታዊ እውቅና ስለተሰጠው ኢህአዴግ ስላላሰራን ብዝሀነት አንድነትን ስለሚሸረሽር የሚሉ በርግጥም ጫማችን የትጋ እንደቆረቆን በቅጡ የማያውቅ ተቃዋሚ ነው ያለን

እንዳለመታደል ሆኖ የኛ ተቃዋሚ ጫማችን ስለጠበበን እግራችን ይቆረጥ የሚል ነው:: ህብረበሄራዊ ማንነታችንና ኢትዮያዊው ጠንካራ አንድነት የተሰጠው ብያኔ ስለማይመጥነው በደም ለከበረና በነጻነት ለሚያንጸባርቅ ታሪኩና በመከባበርና በመቻቻል ለዘለቀው ብዝሀነቱ የሚመጥን የማንነት ጫማ ሰፋ እና አመር ብሎ ቢዘጋጅለት ህገመንግስታዊ እውቅና ቢሰጠው የምር እውነቱን ማወቅና ለአኩሪው ማንነቱ የሚመጥን ህገመንግስታዊ እውቅና መስጠት እንጂ ሌላ አለመሆኑን መረዳት በተገባ ነበር

እንዲያውም ህገመንግስታዊ እውቅናው ብዝሀነትን ተረድቶ ተቻችሎ በመኖር ረገድ ከመሪዎቹ ለላቀው ህዝብ ለዘመናት ላቆየው ህብረብሄራዊ ማንነቱ የቀረበ ገጸ በረከት ነው ህብረብሄራዊነታችንን ዛሬ በልኩ አክብረነዋል አስከብረነዋልም ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜም ብዝሀነትን በችግርነት የሚረዳው ፖለቲካ ተንድዋል

ብዝሀነት የአንድነት ጸር አደለም አንድነትም ህብረብሄራዊነትን አይጨፈልቅም እንዲያውም ብዝሀነታችን ቀለም አንድነታችን አቅም ይሆኑናልብዝሀነታችንን በዚህ መልኩ በውብ ግብአትነት የማይረዳ ፖለቲካ ከጅምሩ ፈተናውን ስለወደቀ ሲጀመር የሚመራውን ህዝብ ስላላወቀ የቤት ስራውን ጨርሶ መምጣት ይኖርበታል

ቀድሞ የተሰፋልን የአገራዊ አንድነትና ህብረብሄራዊ ብያኔ ተፈጥሮአችንን የሚክድ ስለሆነ የሆነውን የሚመስል እኛነታችንን በቅጡ የሚገልጽ አዲስ ብያኔ ይበጅልን ሲባል የማይመስለን አሮጌው ምስላችን ራሱ ካልቀጠለ አገር ይናዳል ይላሉ ተቃዋሚዎች እቺ አገር የመሪዎቹዋ ብዝሀነትን የመረዳት ችግር እንደተጠበቀ ሆኖም በመቻቻል መኖሩዋን ዘንግተው ህዝብ ስንት በደሎችን የተሻለውን ነገን ተሰፋ አድርጎና ሌሎቹ ኢትዮያዊ ብሄሮች አደጋ የማይፈጥሩበት መሆኑን ጠንቅቆ ስለሚረዳ የመሪዎቹን ባህሪ ቸል ብሎ በመከባበር መኖሩ መረሳት የለበትም

ግዜው ደርሶ የአብራኩ ክፋዮች ተፈጥሮውን የሚያውቅ ብዝሀነቱን የሚጠነቅቅ እውቅና እንዲበጅ እድሉን ሲያመቻቹ  በወግና በባህሉ በቁዋንቁዋና በልማዱ በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም አላቅማም ነባሩን ማንነቱን በአግባቡ የሚረዳው እና ህገመንግስታዊ ጥበቃ ያደረገለት ምርጫም ትክክል መሆኑን ዛሬ ከሀያ አመቱ ጅምር ግን ጉልህ ስኬቱ ይረዳዋል። 

ሌላው ቢቀር ባለፉት 20 አመታት የሙዚቃው ኢንደሰትሪ በተለያዩ ቁዋንቁዋዎችና ባህሎች መተዋወቅ ምን ያህል እንደጎመራ ማየት ይቻላል ትልቁ ነገር የምንከተለው አሰራር ይዘትና ትክክለኝነት እንጂ ያው ይዘት በተለያየ ቁዋንቁዋ መገለጹ ምንም ተጽእኖ የሌለው መሆኑን መረዳት መቻሉ ነው ከሳይንሱ እንጂ ቁምነገሩ ከመባያው ቁዋንቁዋ አይደለምና የፌደራል የስራ ቁዋንቁዋ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ህዝብ አፍ መፍቻ ቁዋንቁውን ከመጠቀም የሚቀል የተሻለ አመራጭ የለውም

ተቃዋሚው እንዲህ ያለውንም ተፈጥሮአችንን መረዳት ተስኖት ይህን በሚክድ መደናበር ከተፈጥሮም ጋር የሚላተመው ለተቃውሞ የቆመ የፖለቲካ ቡድን እንጂ ለችግሮች  ሁነኛ መፍትሄ ማፈላለግ የማይችል ሀይል በመሆኑ ነው

ይህንን ቁመናውን ከማንም በላይ ራሱ ተቃዋሚው ስለሚረዳ ምርጫ በመጣ ቁጥር ገና ምርጫው ሳይካሄድ ተጭበርብሩዋል በሚል ይከሳል አገራዊ ተቁዋሞቹ ምርጫ ማካሄድ አይችሉም በሚል ይለፍፋል በርግጥ ይህ የሚሆነው ተቃዋሚው ያለበት ሁኔታ ከዚህ በዘለለ በሳል አማራጭ የፖለቲካ መፍትሄ ማቅረብ የሚያስችለው ባለመሆኑ ነው

የተቃዋሚው ጎራ ያለፉት አመታት መንገድ ማሳካት የቻለው ነገር ቢኖር በገዛ ባህሪውና ተግባሩ ራሱን እያቀጨጨ እና እያከሰመ መሄዱ ነው ከገዛ ሂደቱ ትምህርት መውሰድ የማይችል መሆኑንም ከተግባርና ከባህሪው ማንም ሊታዘብ የሚችለው ነው

በርግጥ የተቃዋሚው ጎራ ጠንካራ መሆን ለዴሞክራሲው ስር መስደድ ለጠንካራ ተቁዋማት መፈጠር እና ለምርጫ ስርአቱ እየተጠናከረ መሄድ ፋይዳ ስለሚኖረው ነው የተቃዋሚውን ጎራ ስህተቶች ለማሳየት ጥረት የሚደረገው የገውን ፓርቲ ያህል ገንቢ ሚና ተቃዋሚው ተጫውቶ ቢሆን ኖሮ አፍራሽ ሚና በተጫወተበትም ሁኔታ የአፍሪካ ታይገር ኢኮኖሚ መባል የቻለውና  በማህበራዊ ዘርፍ የላቀ ስኬት ያስመዘገበው ህዝብና መንግስት ምንያክል የተሻለ ስኬት ባስመዘገቡ ነበር

ይሁን እንጂ ተቃዋሚው ሚናውን መወጣት ቢሳነውም በአገር ተስፋ አይቆረጥምና ህዝብና ገው ፓርቲ በመተባበር ማስመዝገብ የቻሉት ለውጥ ባለፉት አስር አመታት አገሪቱን በፍጥነት ከሚያድጉ አገሮች ተርታ ያሰለፈ ነው። 

ተቃዋሚዎቻችን ታርጋቸውን ቢቀይሩ በምርጫው ማግስት የሚፈርሱ ግንባሮችን ከሚያቁዋቁሙ ይልቅ መታገያ ግቦቻቸውን እና ዲስፕሊናቸውን ቢከልሱና ሁነኛ አማራጭ ቢሆኑ አገር ብዙ ትጠቀማለች!!!!

No comments:

Post a Comment