Friday, April 12, 2013

ተቃዋሚን ጀግና ደጋፊን ሆዳም ማን አደረገው?


የኛ አገር ቅጥ አንባሩ የጠፋው የፖለቲካ ምህዳርና ሚድያ ጫፍ የረገጠ ተቃዋሚ ወይም አሜን አሜን ባይ የበዛበት ነው$

በዚ መሀል መንገድ አይታየውም$ መሀለኛውን መንገድ መሀል ላይ ያለውን በርካታ አማራጭ ለመመዘን እና ለማቅረብ ግድ አይለውም$ መራገጥ ብቻ ይመስላል ቁምነገሩ$
ነፃነት ለኛ ሀገሩ ሚድያ መዋሸት መረጃ መፍጠር መሳደብ ያዙኝ ልቀቁኝ እንጂ የበሰለ እና ሀብት መፍጠር የሚችል መረጃ ማቅረብ ይሳነዋል$

ከዚህ የራቀው ሌላኛው አማራጭ ደግሞ አጨብጫቢ አድርባይ የበዛበት ለሰከኑ ውይይቶች እና የሀሳብ ልውውጥ ሳይሆን ለመሞጋገስ የተፈጠረ የሚመስል በአመዛኙ አስመሳዮች ለወቅታዊ ትርፍ የሚሰበሰቡበት ጎራ ነው$

ወዲያ ተሳዳቢ ወዲህ ደግሞ አድናቂ$ ያኛው የፈጠጡ ስኬቶች የማይታዩት ከሀዲ ይሄኛው ደግሞ የዋሉ ያደሩ እጥረቶችንና ችግሮችን የሚክድ ልብ አውልቅ$ ያኛው በስድቡ ጋጋታ ጀግና ሆኖ ለመታየት የሚጥር አድርባይ$ ይሄኛው ደግሞ በማሞካሸት ጥቅም ማግበስበስ የሚሻ አድርባዮች ናቸው$

አንዱ ጀግና መባል ሆዱን ብልት አድርጎት የቆመውን ሁሉ ለመጣል በመሞከርና በማዋረድ ጀግና ሆኖ ለመገኘት የሚጥር ጅብ$ ሀገራዊ ግቦቹን ዳር በማድረስ ሳይሆን የሚቃወማቸውን የመጣል ብቻ ጂኒ ያለበት አተያይ ባለቤት$ ለሱ እሱና እንደሱ ያሉ ተሳዳቢዎች ካልሆኑ በቀር ጀግና የለም$

የሚቃወመውን አካልና ደጋፊዎቹን የመርገምት ጨርቅ ያክል ያረክሳቸዋል$ እሱ የሚቃወመውን የደገፉ ሁሉ እውራን ሆዳሞች ሌቦች ለጥቅም የተረቱ ጅቦች ናቸው$ ላለመሆናቸው ማረጋገጫው እንደሱ መሳደብ ብቻ ነው$

ሌሎች መሳደብም ማስመሰልም ጠልተው የተቀመጡት ደግሞ ፈሪዎች ናቸው በዚህ ሰው የቃላት ማውጫ ዝርዝር መሰረት$ መንገዱ ወይ መሳደብ ወይ መሰደብ ብቻ ነው$ በመሀሉ ምንም የለም$ ልክ እንደ አንድነት ወይም ሞት$ ይሄ እንግዲህ ተሳድቦ አድናቆትን መሸመት የሚፈልገው አድርባይ ነው$

ሌሎቹ አድናቂ አድርባዮች ደግሞ ለቆመና ለተሾመ ሁሉ ማቃጠር የሚወዱ እርሶ እንዳሉት እያሉ ማቆለማመጥ የሚያምርባቸው ቃጭሎች ናቸው$ በነዚህ የአስተሳሰብ አድማስና ቃላት ማውጫ ላይ ስህተት እጥረት ችግር የሚባል ነገር አለቃ ፊት አይነሳም$

በርሶ አመራር ምን ያልተፈጠረ አለ የሚሉ ዋሾዎች ናቸው$ ራሳቸው ተሿሚዎቹ እስኪታዘቧቸው ድረስ የሆነ ያልሆነውን የሚቀባጥሩ አጀንዳቸው ተሙለጭልጮ ማደግ ብቻ እንጂ አባል የሆኑበት ድርጅት ሀገራዊ ራእይ ማሳካት አለማሳካቱ ወይም የሚሰሩበት ተቋም አላማ መሳካት አለመሳካቱ አደለም$

የተባለ ያልተባለውን ለሀላፊያቸው በማቅረብ ተወዳጅ ለመሆን የሚጥሩ ለዚሁ አስተዋጿቸው ስልጣን ወይም የውጭ ጉዞ ምናምን እንዲቦጨቅላቸው የሚሹ ሰብአዊ ክብራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ያሳነሱ ውራጆች ናቸው$ መርጠው በወረደው መንገድ የሚጓዙ ደካሞች$
ወዳጆቼ በመሀሉ ሌላ መንገድ አለ$ በርካታ መንገድ$ 

ትልቁ ነገር በተሰለፍንበት የስራ መስክ የሚሻለውን አስተዋጾ ለማበርከት መጣር ነው$ ሲቀጥል ከዛም በተጨማሪ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሀላፊነት መሸከም የሚመርጥ ሰው ደግሞ በመረጠው ድርጅት አባል በመሆን በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙርያ መሰለፍና የሚያምንበትን ሀገር የሚመጥን ለውጥ ለማበርከት መጣር ይችላል$

ይሄ ጥረት ግን በምንም ሚዛን መሳደብና ማጣጣልን በሁነኛ አማራጭነት እንድንይዝ ወይም ማቆለማመጥና ጥገኝነትንም በመሸከፍ ሆዳችንን የሚበላንን የግል ጥቅም እንድናሯሩጥ አይጋብዘንም$

የተሰራውን አዎ ይሄ ተሳክቷል ብሎ በማመን የቀረውን ደግሞ በኔ አተያይ ይሄ ሊሰራ ሲገባው መፈጸም አልቻለም በሚል መከራከር በይዘት ለመሸናነፍ መሞከር ሲገባ እኔ ካለኩት አማራጭ ውጪ የሆነ አተያይ አፈር ድሜ ይብላ በሚል የሚከናወን እሰጥ አገባና አሜን ባይነት ለዚህ አገርና ለዚህ ደሀ ህዝብ ምኑም አደለም$

እንዲህ ያለውን ከአሮጊቶች ተረት ያነሰ ቁምነገር አልባ ዝባዝንኬ በመስማት ህዝብ ግዜውንም ማባከን የለበትም$

ጀግና ተሳዳቢም ጀግና አሜን ባይም አደለም$ ጀግና ተጫባጩን ችግር በተጨባጭ መፍትሄ የሚረታ ነው$ ጀግና ለፈጠጠው ድህነት መፍትሄ የሚሆኑ አተያዮች እና አሰራሮች የሚቀምር አንዳች ድህነት መቅረፊያ መሳሪያ ማዘጋጀት የሚችል የፈጠራ ሰው ነው$

ጀግና የሚያምንበትን አማራጭ እንዲሰሙት የሚሻውን ያክል አምሮ የሚቃወመውን አማራጭ ለመስማት ዝግጁ የሆነ በዚሁ አማራጭ ቢሸነፍ እንኳ ለመቀበል የማያቅማማ ልበ ሙሉ እንጂ  ኦናው ተሳዳቢም ባዶው አሜን ባይ አድርባዮችም አደሉም$ የነዚህ ሁለት ባዶዎች ልዩነት አንዱ ተቃዋሚዎች አዝለው እንዲያሳድጉት የሚሻ መሆኑ ሌላኛው ባለቀን ተጠግቶ ጥቅም ለማጋበስ መሞከሩ ናቸው$

ጀግና እኔ እንጂ ሌላ ማን አለ አይልም$ ጀግና የኔ አስተዋጾ መቅረት የሚፈጥረው ክፍተት ይኖራል በመሆኑም የሚደክሙ ጓዶችን ላግዝ ትግሉን አንድ ጋት ወደፊት ፈቅ ላድርግ የሚል$ ባያደርግ ትግሉ አንድም ጋት ቢሆን እንዳይጓተት በመስጋት ሲያደርግም ትግሉ አንድም ጋት ወደፊት ሲጓዝ ከሌሎች እንደሱ ተፍ ተፍ ከሚሉ ጓዶቹ ውጤት ጋር ሲደመር ሀገራዊ ፋይዳው የላቀ እንደሚሆን በማመኑ ነው$

ጀግና ዛሬዎቹን የሚረታ እንጂ በዛሬዎቹ ርግማንና ስድብ አለያም የዛሬዎቹን ሹማምንት ሲያደንቅ ግዜውን የሚያባክን አደለም$ ጀግና ዛሬዎቹን ለላቀው ጥቅም የሚያውል አሸናፊ ነው$ የሚረታውም ድህነትን የሚያስገኘውም ሀብት እንጂ ሌላ ሰብአዊ ባላንጣዎች የሉትም$

አልሞ የሚመታው ጠላት ስንፍና አልሞ የሚገነባው ሀብት ትጋትና የመቻቻል ፖለቲካ እንጂ ማዋረድም በማዳነቅ ለመጠቀም መሞከርም የአላማው ይዘት አደለም$ ግቡ ሀገራዊ ድሉ ህዝባዊ አቅሙ ህሊናዊና ከውስጥ የሚመነጭ ነው$

ወዳጄ ቁምነገሩ ከመቃወምህም ከመደገፍህም አደለም$ አሰላለፍህ በየትም ይሁን በየት አስተዋጾህ ሀገራዊ አጀንዳን አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስኬድ ይሁን$ ይዘቱ ባለፋይዳ ክርክርህ የበሰለና በጉዳዮች ዙርያ የሚያጠነጥን ይሁን$

እውነት እውነት እልሀለው እንደላው መጻፍ የምር ተሳዳቢም አሜን ባይ አድርባዮችም ቢሆኑ ለዚህ አገር እዚህ ግባ የሚባል ፋይዳ አይኖራቸውም$
ሁሌም በመሀሉ መንገድ አለ$

2 comments:

  1. Very good a ssessment! It gives a sound analysis pinpointing the missing gaps in our political discourse which is ficharacterized by two extremes,i.e., muwartegninet and azmarinet!

    ReplyDelete
  2. This is a well thought reflection.

    It is also good to keep in perspective that poverty itself drives some of this extreme positions in politics. Poor people have the tendency to exchange their dignity to remain functioning under corrupt political position.

    Some take extreme opposing position not only because they believe in it, but also because through such actions they know they benefit better.

    So it could be that poverty itself is the root cause that leads people to follow such extreme political positions. People seek better life, better education for their children, better security during health crisis and so on..

    If the economic system can't easily allow them to access those, they tend to be crooked and find a short way to achieve those economic needs. To achieve those, some choose to flee the country and seek asylum in other countries (obvious situation we are familiar). Under the asylum world, running non-sense opposition opinion pays off better than playing a decent politics.

    On the contrary, other choose or have no choice and stay in country. The short way for them to ensure their economic well-being could be through living in praising their political superiors so that they get a bit share of the cake.

    I understand I'm simplifying things a lot, but my point is -let's keep the role of poverty into perspective to understand those people in the two extreme corners of our politics.

    I thank the blogger for his article.

    ReplyDelete