Wednesday, April 3, 2013

እነ ስድብ ጌጡ


አንዳንድ ተቃዋሚዎች የሚቃወሙትን ነገር ድክመት ማሳየት ሲገባቸው
የሚደግፉትንና የሚያቀርቡትን አማራጭ በማብራራት ለማሳመን መጣር ሲገባቸው
ልዩነታቸውን በስርአት እንኳ ማቅረብ ሳይችሉ

ይሄ አገር ዲሞክራሲ ስለመራቡ የዛሬዎቹ መሪዎች ሌቦች ስለመሆናቸው እና
ይህን መንግስት በልማታዊ እና ፖለቲካዊ ጥረቶቹ የደገፈውን ሁሉ ለሆዱ ያደረ ሌባ
ስለመሆኑ ይነግሩናል።

እውን በምን መስፈርት ነው ተሳዳቢ ለህዝብና ለፍትህ ለዲሞክራሲያዊ ስርአት
ተቆርቋሪ ነኝ የሚለው።

የምታየውን ወንድምህን ሳታከብርና በስርአት ሳታናግር ጥቅል አገርህን በአግባቡ
ስለመምራትህ ያን የማድረግ ስነምግባሩ ያለህ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለንም።

በቀላሉ ስድብ ተሳዳቢን ያቀላል እንጂ ተሰዳቢን አያሳንስም። ስድብን ትጥቅ ያደረገው
ወገን ነው የሚቀለው እንጂ ስድቡ የተነጣጠረበት ተወቃሽ አይደለም ተዋራጁ።

ወራዳ ብሎ ተሳድቦ ከመዋረድ የተሻለ አማራጭ ይኑረን!

No comments:

Post a Comment